-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 ንግድ ፍቃድ በስልክ ለማደስ

ንግድ ፍቃድ በስልክ ለማደስ

🏢 ንግድ ፍቃድ ለመሰረዝ

ንግድ ፍቃድ ስረዛ

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 ለ ደረጃ ለ'' የግብር ስሌት

የንግድ ገቢ ግብር ለደረጃ ለ ስሌት

🏢 ሀ ደረጃ ለ'' የግብር ስሌት

የንግድ ገቢ ግብር ለደረጃ ሀ ስሌት

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

📦 በጉምሩክ ዕቃ በዋስትና ስለሚለቀቅበት ሁኔታ

ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣ አዲስ መመሪያ

የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለደንበኞች ሥራ ላይ ባሉ ሕጎችና አሠራሮች ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ያወጣው አጭር ማብራሪያ የሚከተለውን ይመስላል፦

የክፍያ ጊዜ ገደቡንና ሙሉ ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ 📖

📌 ዋስትና ማለት ምን ማለት ነው?

ዋስትና ማለት አስመጪው የቀረጥና ታክስ ክፍያን በተወሰነ ጊዜ ለመክፈል ስምምነት በመግባት የሚያቀርበው የባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ነው።

👤 በዋስትና ዕቃ እንዲያወጡ የሚፈቀድላቸው አስመጪዎች፦

  • 🔹 የተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች
  • 🔹 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች
  • 🔹 አምራች አስመጪዎች
  • 🔹 በሌሎች በልዩ ሁኔታ በኮሚሽኑ የሚፈቀድላቸው አስመጪዎች

💡 ቅድመ ሁኔታ፦ ከላይ የተጠቀሱት አካላት ዕቃ ከመልቀቃቸው በፊት መክፈል ከሚገባቸው የቀረጥና ታክስ መጠን ውስጥ ቅድሚያ 25% መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

📅 የቀረጥ ክፍያ የጊዜ ገደብ መመሪያ፦

ከብር 1 ሚሊዮን እስከ ብር 5 ሚሊዮን፦ በሶስት (3) ወር ጊዜ ውስጥ መክፈል ይቻላል።

ከብር 5,000,001 እስከ ብር 10,000,000፦ በስድስት (6) ወር ጊዜ ውስጥ መክፈል ይቻላል።

ከብር 10,000,000 በላይ፦ በዘጠኝ (9) ወር ጊዜ ውስጥ መክፈል ይቻላል።

• ⚠️ ልዩ ማሳሰቢያ፦ የሚከፈለው ቀረጥና ታክስ (የቅድሚያ ክፍያውን ጨምሮ) ከብር 1,000,000 በታች ከሆነ የክፍያ ማራዘሚያ (ዋስትና) አይፈቀድም!

🤝 የክፍያ ስምምነት ሁኔታዎች፦

  • 🔹 የክፍያ ስምምነቱን የሚፈርመው የአስመጪው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም ሕጋዊ ወኪል ነው።
  • 🔹 ክፍያው የሚፈጸመው በየሩብ ዓመቱ (በየ 3 ወሩ) ሲሆን፣ ከብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበት የጥናት ተመን ተነስቶ የወለድ ምጣኔ ተጨምሮበት የሚከፈል ይሆናል።
  • 🔹 በስምምነቱ መሠረት ክፍያ ያልፈጸመ አስመጪ፣ የያዘው ዋስትና ወዲያውኑ ወደ መንግሥት ገቢ ይደረጋል።
  • 🔹 በልዩ ሁኔታ ጊዜን ማራዘም ቢቻልም፣ ዋስትናው ከታደሰበት የጊዜ ገደብ በላይ ማራዘም አይፈቀድም።
  • 🔹 የክፍያ ስምምነቱ ማብቂያ ቀን በሕዝብ በዓል ላይ ከዋለ፣ ክፍያው በሚቀጥለው የመጀመሪያው የሥራ ቀን ይፈጸማል።

© 2026 Heena Digital Market | መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📜 በትራንዚት ዕቃ ማጓጓዣ ላይ የወጣው የጉምሩክ ቅጣት!

በትራንዚት ዕቃ ማጓጓዝ ላይ የተጣሉ ከባድ ቅጣቶችና ሕጎች ማብራሪያ።

ዝርዝር የቅጣት መመሪያዎችን እዚህ ያንብቡ 📖

💰 የገንዘብ ቅጣት፦

የጉምሩክ የትራንዚት ሥነ-ሥርዓትን ያላከበረ ማንኛውም ሰው ከብር 5,000 ያላነሰ እና ከብር 20,000 የማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል።

🛑 የዋስትና መወረስ፦

ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጠመ በስተቀር፣ ተላላፊ የትራንዚት ዕቃ የጫነ ማጓጓዣ በተወሰነለት ጊዜና መስመር ተጉዞ ከአገር መውጣቱ ካልተረጋገጠ፣ የተያዘው ዋስትና ሙሉ በሙሉ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል!

📦 የዕቃ መወረስ፦

በትራንዚት ማጓጓዣው ላይ ከተመዘገበው ውጭ ተጨማሪ ወይም ተደብቆ የተገኘ ዕቃ ካለ፣ ዕቃው ሙሉ በሙሉ በጉምሩክ ይወረሳል።

⚠️ "ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት" (Force Majeure) የሚባሉት ምንድን ናቸው?

ዕቃው የዘገየው በሚከተሉት ምክንያቶች ከሆነ እንደ ማስተካከያ ይወሰዳል፦

  • 🛠️ በማጓጓዣው ላይ በደረሰ ድንገተኛ ብልሽት ወይም አደጋ
  • 🩺 በሹፌሩ ላይ በደረሰ ከባድ ሕመም
  • 🚧 የመንገድ መዘጋት ወይም በድንገተኛ የመንግሥት ክልከላዎች

➡️ የጉምሩክ ትራንዚት ስነ-ስርዓት አፈፃፀም መመሪያን ለማግኘት አሁኑኑ ድረ-ገጻችንን "መመሪያ" ክፍል ውስጥ ያገኙታል።

© 2026 Heena Digital Market | መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ቅጣት

⚠️ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽንን በወቅቱ አለማሳደስ ቅጣቱ ምንድን ነው?

ለነጋዴዎች የሚሰጥ ወሳኝ የጥንቃቄ መረጃ

የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽንን በሕጉ መሠረት በየዓመቱ አለማሳደስና የቴክኒክ ምርመራ አለማድረግ ከባድ የአስተዳደር ቅጣትና የንግድ መስተጓጎል ያስከትላል። ዝርዝር መመሪያው የሚከተለውን ይመስላል፦

የገንዘብ ቅጣቱንና ዝርዝር እርምጃዎቹን እዚህ ያንብቡ 📖

💵 1. የገንዘብ ቅጣት (የአስተዳደር ቅጣት)፦

ወቅቱን ጠብቆ አለማሳደስ፦ ማሽኑ በየዓመቱ መታደስ (የአገልግሎት ውል መታደስና የቴክኒክ ምርመራ መደረግ) ያለበት ሲሆን፣ ይህንን በወቅቱ ሳያደርጉ ቀርተው ማሽኑ አገልግሎት መስጠት ካቆመ ወይም ፍቃዱ ካለፈ እስከ ብር 25,000 የገንዘብ ቅጣት ሊጣል ይችላል።

ማሽኑ ሳይታደስ ሽያጭ መቀጠል፦ ማሽኑ ሳይታደስ ወይም የቴክኒክ ምርመራ ሳይደረግለት ሽያጭ ማካሄድ እና ደረሰኝ መቁረጥ ተጨማሪ የአሠራር ጥሰት ተደርጎ ስለሚወሰድ ቅጣቱን ይበልጥ ሊያባብሰው ይችላል።

🚫 2. ሊወሰዱ የሚችሉ ሌሎች ከባድ እርምጃዎች፦

  • 🔹 የማሽኑ መዘጋት (Block መሆን)፦ ማሽኑ በወቅቱ ካልታደሰ ከገቢዎች ሲስተም ጋር ያለው ትስስር በራሱ ጊዜ ሊዘጋ (Block ሊሆን) ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ደረሰኝ መቁረጥ ስለማይችሉ ንግድዎ ላይ ቀጥተኛ መስተጓጎል ይፈጥራል።
  • 🔹 ደረሰኝ አለመስጠት በሚል መታየት፦ ማሽኑ ባለመታደሱ ምክንያት ደረሰኝ ሳይቆርጡ ለደንበኛ ሽያጭ ካከናወኑ፣ ድርጊቱ እንደ "ደረሰኝ አለመስጠት" ተቆጥሮ የብር 25,000 ተጨማሪ ቅጣት እና የወንጀል ክስ ሊያስከትል ይችላል።

💡 ማጠቃለያ ምክር፦ በቅጣትና በማሽን መዘጋት ምክንያት ስራዎ እንዳይስተጓጎል ሁልጊዜ የማሽንዎ የማደሻ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ለፈቃድ ሰጪው አካል በማቅረብ ማሳደስዎን ያረጋግጡ!

መረጃው ለሌሎች ነጋዴዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

የዊዝሆልዲንግ ታክስ አሰላል

📊 የ3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ አሰላል ደንብ

ተቀናሽ የሚደረገው 3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ በቪኤቲ (VAT) ላይ ይታሰባልን?

ተቀናሽ የሚደረገው ሦስት በመቶ ዊዝሆልዲንግ ታክስ የሚሰላበት የእቃ ወይም የአገልግሎት የክፍያ መጠን የተጨማሪ እሴት ታክሱን ይጨምራል ወይስ አይጨምርም? እንዴት ነው የሚሰላው?

ዝርዝር መመሪያውንና ምሳሌውን እዚህ ያንብቡ 📖

⚠️ ዋናው ደንብ፦

አይጨመርም! 3% የዊዝሆልዲንግ ታክስ (Withholding Tax) የሚሰላው የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ሳይጨምር በዕቃው ወይም በአገልግሎቱ ዋና ዋጋ ላይ ብቻ ነው።

የክፍያ ሰነድ (ኢንቮይስ) መሠረታዊ ክፍሎች፦

  • 🔹 የዕቃው ወይም አገልግሎቱ ዋና ዋጋ፦ ይህ 3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ የሚሰላበት መነሻ ሂሳብ ነው።
  • 🔹 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፦ በዋናው ዋጋ ላይ ብቻ ተሰልቶ የሚቀመጥ።
  • 🔹 የሁለቱ ድምር፦ ጠቅላላ የኢንቮይስ ዋጋ።

🧮 ተግባራዊ ምሳሌ፦

አንድ ድርጅት የብር 10,000 ዕቃ ወይም አገልግሎት ቢገዛ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ቢሆን፦

• የዕቃው/አገልግሎቱ ዋና ዋጋ፦ ብር 10,000

• ተጨማሪ እሴት ታክስ (15% VAT)፦ ብር 1,500

• ጠቅላላ የክፍያ ሰነድ (ኢንቮይስ) ድምር፦ ብር 11,500


📌 የዊዝሆልዲንግ ታክስ አሰላል፦
3% ዊዝሆልዲንግ የሚሰላው በዋናው ዋጋ (ብር 10,000) ላይ ብቻ ስለሆነ፦
Withholding Tax = 10,000 × 3% = ብር 300


💰 ለአቅራቢው የሚከፈለው ጠቅላላ የተጣራ ሂሳብ፦
ስለዚህ ዊዝሆልዲንግ ታክስ በሚቀነስበት ጊዜ የቪኤቲ (VAT) ሂሳቡ መደመር የለበትም። ክፍያ ፈጻሚው አካል ለባለአገልግሎቱ/ለአቅራቢው የሚከፍለው ጠቅላላ ሂሳብ፡
ጠቅላላ ድምር (ብር 11,500) - ዊዝሆልዲንግ ታክስ (ብር 300) = ብር 11,200 ይሆናል ማለት ነው።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🚫 ያለ አስመጪነት ንግድ ፈቃድ ዕቃ ማምጣት ይቻላል?

ስለ ግል መገልገያና የንግድ ዕቃዎች ግልጽ መረጃ

ብዙዎች ዕቃዎችን ያለ አስመጪነት ንግድ ፈቃድ ለአንድ ጊዜ ብቻ ማምጣት እንደሚቻል ያስባሉ፤ ነገር ግን ሕጉ የሚለው የሚከተለውን ነው፦

ዝርዝር መመሪያውን እዚህ ያንብቡ 📖

⚠️ ዋናው ደንብ፦

ያለ ንግድ ፈቃድ ማንኛውንም ዕቃ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት አይቻልም

ከዚህ ደንብ ውጭ የሚስተናገዱ (ልዩ ሁኔታዎች)፦

  • 🔹 የንግድ ባህሪ የሌላቸው ዕቃዎች፦ በስጦታ መልክ የሚላኩ ዕቃዎች።
  • 🔹 ለመንገደኞች፦ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚገቡ የግል መገልገያዎች።
  • 🔹 ለተመላሽ ኢትዮጵያውያን፦ በገንዘብ ሚኒስቴር የግል መገልገያ መመሪያ ዝርዝር ላይ የተቀመጡ ዕቃዎች።

ማጠቃለያ፦ በመመሪያው ላይ ከሰፈሩት "የግል መገልገያ" ዕቃዎች ውጭ ማንኛውም አይነት ዕቃ ለማስገባት የአስመጪ የንግድ ፈቃድ መኖሩ ግዴታ ነው!

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

💰 የዕቃዎች ቀረጥና ታክስ አወሳሰን (CIF Value)

ዕቃዎች ወደ ሀገር ሲገቡ ቀረጥ እንዴት ይሰላል?

የዕቃዎች ቀረጥና ታክስ የሚወሰነው በዕቃው አጠቃላይ የCIF ዋጋ እና በዕቃው የታሪፍ ምጣኔ ላይ ተመስርቶ ነው፡:

የCIF ዝርዝር እና አሰላስል እዚህ ያንብቡ 📖

CIF ማለት ምን ማለት ነው?

CIF (Cost, Insurance, and Freight) ማለት የሚከተሉት ወጪዎች ድምር ውጤት ነው፦

  • 🔹 C (Cost)፦ የዕቃው መግዣ ዋጋ።
  • 🔹 I (Insurance)፦ የኢንሹራንስ ወይም የመድን ዋስትና ወጪ።
  • 🔹 F (Freight)፦ የማጓጓዣ ወይም የጭነት ዋጋ።
  • 🔹 ሌሎች ወጪዎች፦ ከዕቃው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች።

ቀመር (Formula)

CIF = የመግዣ ዋጋ + ኢንሹራንስ + ማጓጓዣ

ቀረጥ የሚወሰንባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

  • 👉 የታሪፍ ምጣኔ፦ እንደ ዕቃው ዓይነት (ለምሳሌ የቤት ዕቃ፣ የኢንዱስትሪ መሣሪያ፣ አልባሳት) የሚቀመጥ የመቶኛ ስሌት ነው።
  • 👉 የምንዛሬ ተመን፦ ስሌቱ የሚሠራው ዕቃው ጉምሩክ በደረሰበት ቀን ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ወደ ብር ተቀይሮ ነው።

ማስታወሻ፦ ትክክለኛውን የCIF ዋጋ ማሳወቅ ከቅጣት ነፃ ያደርጋል፤ የጉምሩክ ሂደቱንም ያፋጥነዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ብሎጋችንን ይከታተሉ! 💡

🚢 ለአስመጪና ላኪዎች፦ ለጉምሩክ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች

የጉምሩክ ስነ-ስርዓትን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መረጃዎች

በፅሁፍ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የእቃ ዲክላራሲዮን ለጉምሩክ ሲቀርብ የሚከተሉት ሰነዶች ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፦

የሰነዶቹን ዝርዝር እዚህ ያንብቡ 📖
  • የታደሰ የንግድ ፍቃድ፦ በዘመኑ የታደሰና ለስራው ብቁ መሆኑን የሚያረጋግጥ።
  • የማጓጓዣ ሰነዶች (Shipping Documents)፦ ዕቃው የተጫነበትን መንገድና ሁኔታ የሚያሳዩ።
  • የዋጋና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ (Invoice & Packing List)፦ የዕቃው አይነት፣ ብዛትና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር የያዘ።
  • የባንክ ፍቃድ (Bank Permit)፦ ከባንክ የተገኘ የክፍያ ወይም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ።
  • የስሪት ሀገር ማረጋገጫ (Certificate of Origin)፦ ዕቃው የት ሀገር እንደተመረተ የሚያሳይ ምስክር ወረቀት።
  • ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች፦ በመመሪያ የሚወሰኑና እንደ ዕቃው አይነት የሚጠየቁ ተጨማሪ ሰነዶች።

💡 ማሳሰቢያ፦

እነዚህ ሰነዶች ተሟልተው መቅረባቸው የጉምሩክ ሂደቱን ፈጣን ከማድረጉም በላይ አላስፈላጊ መዘግየቶችን ያስቀራል።

መረጃው ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

⚖️ ታክስን አሳንሶ ማሳወቅ የሚያስከትለው ቅጣት

መረጃው ለታክስ ከፋዮች ሁሉ ይድረስ!

በታክስ ማስታወቂያ የተገለጸው የታክስ መጠን ታክስ ከፋዩ ሊከፍል ከሚገባው ትክክለኛ የታክስ መጠን ያነሰ ሆኖ ከተገኘ (የታክስ ጉድለት) የሚከተሉት ቅጣቶች ይጣላሉ፦

የቅጣቱን ደረጃዎች እዚህ ያንብቡ 📖

1. ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት፦

በታክስ ጉድለቱ መጠን ላይ 10% (አሥር በመቶ) ቅጣት ይከፈላል።

2. ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት፦

ጥፋቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሲደገም የቅጣቱ መጠን ወደ 30% (ሰላሳ በመቶ) ከፍ ይላል።

3. ለሦስተኛ ጊዜ እና ከዚያ በላይ፦

ጥፋቱ ለሦስተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ሲደገም የቅጣቱ መጠን ወደ 40% (አርባ በመቶ) ከፍ ይላል።

📢 ማወቅ ያለብዎት ተጨማሪ ነጥቦች፦

  • 👉 ምክንያታዊ አቋም፦ ጉድለቱ የተፈጠረው ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ባልሰጠበት አከራካሪ ሕግ ላይ በተወሰደ ምክንያታዊ አቋም ከሆነ ቅጣቱ ተፈጻሚ አይሆንም።
  • 👉 የጥፋት ብዛት አቆጣጠር፦ የጥፋቱ መጠን የሚቆጠረው አዋጁ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለየታክስ ዓይነቱ ተለይቶ እና ጥፋት በተገኘባቸው የታክስ ማስታወቂያዎች ብዛት ነው።

ትክክለኛ መረጃን በማቅረብ ከከባድ የገንዘብ ቅጣት ይዳኑ!

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

አክሲዮን ትርፍ ድርሻ (Dividend) የታክስ መመሪያ

አንድ ትርፍ ያገኘ ድርጀት ሁለት መርጫ አለው ካፒታል ማሳደግ ወይም የትርፍ ድርሻ ግብር መክፈል


1. የግብር መጠን፦

ማንኛውም የትርፍ ድርሻ ያገኘ ሰው (ነዋሪም ሆነ ነዋሪ ያልሆነ) በገቢው ላይ 15% የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት።

2. ግብሩ መቼ መከፈል አለበት?

የትርፍ ድርሻ ግብር የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ 14 ወራት ውስጥ መከፈል አለበት።

3. ካፒታል ማሳደግ (ታክስ ላለመክፈል)፦

ትርፉን ለባለቤቱ ከመስጠት ይልቅ ካፒታል ለማሳደግ ከተፈለገ፣ ዓመቱ ባለቀ በ 12 ወራት ውስጥ ካፒታሉ ማደግ አለበት።

ካፒታል አደገ የሚባለው፦ በውልና ማስረጃ የጸደቀ ቃለ-ጉባኤ ሲኖር፣ በ e-trade ካፒታሉ ሲሻሻል እና ሰነዶቹ ለገቢዎች ቀርበው ከፋይሉ ጋር ሲያያዙ ነው።

4. በጊዜው ካልተከፈለ የሚመጣ ቅጣት፦

ትርፉ ሳይከፈል ወይም ካፒታል ሳይሳደግ ቢቀር የፍሬ ግብር፣ የወለድ እና የአስተዳደር መቀጫ ይጣልባቸዋል።


ድርጅቱ የትርፍ ድርሻ መከፈል የሚጠበቅበት ትርፍ ካገኘ ብቻ ነው
ታክስ ከመወሰኑ በፊት ከታወቀ፦ የ 10,000 ብር መቀጫ ብቻ።

ታክስ ከተወሰነ በኋላ ከሆነ፦ ከፍሬ ግብሩ በተጨማሪ ከ 5% እስከ 25% የሚደርስ ቅጣት ይጣልበታል።