-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🔌 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል ሙሌት

የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያና መስፈርቶች

፩. የፈቃድ አይነት እና መደቦች

ማንኛውም የህዝብ የሃይል መሙያ አገልግሎት ሰጪ እንዲሁም ለንግድ ላልሆነ ለራስ አገልግሎት ሃይል መሙያ ጣቢያ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል፡፡

የፈቃድ አይነቶች፦
ሀ) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የሃይል መሙያ ፈቃድ (ለህዝብ አገልግሎት)
ለ) ለንግድ ላልሆነ ለራስ አገልግሎት የሚውል የሃይል መሙያ ጣቢያ ፈቃድ

የፈቃድ መደቦች፦
📍 መደብ 1፦ እስከ 100 ኪሎ ዋት (kW) የሃይል የመሙላት አቅም ያለው።
📍 መደብ 2፦ ከ 100 ኪሎ ዋት (kW) በላይ የሃይል የመሙላት አቅም ያለው።
✍️ ማሳሰቢያ፦ ሁሉም ፈቃዶች በሳይት (Site-based) ላይ የተመሰረቱ ናቸው፤ ለእያንዳንዱ ስራ የተለያየ ፈቃድ ያስፈልጋል።

፪. የፈቃድ ማመልከቻ መስፈርቶች

ማንኛውም አመልካች ባለስልጣኑ ያዘጋጀውን ፎርም ሞልቶ የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይኖርበታል፦

1️⃣ መታወቂያና የአመልካቹ ሙሉ አድራሻ፤
2️⃣ የገንዘብ አቅምና ሁኔታን የሚያሳዩ የፋይናንስ ሰነዶች፤
3️⃣ የቴክኒክ ብቃትና የሥራ ልምድ ማስረጃ፤
4️⃣ የባለሙያዎች የኤሌክትሪክ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ (Competency)፤
5️⃣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፤
6️⃣ የአገልግሎት ክፍያ የደረሰኝ ኮፒ።

፫. የህዝብ ኃይል መሙያ ልዩ መስፈርቶች

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ እነዚህ ሰነዶች ያስፈልጋሉ፦
  • ✅ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ምንጭ ማረጋገጫ
  • ✅ የፕሮጀክት ሳይት ካርታ እና አጠቃላይ አቅም (kW/kVA)
  • ✅ የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት (Feasibility Study)
  • ✅ የማከፋፈያ ኔትዎርክ/የግሪድ ሁኔታ መግለጫ
  • ✅ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ (EIA) የምስክር ወረቀት
  • ✅ የመሬት አጠቃቀም ፈቃድ

፬. የፈቃድ ቆይታና እድሳት

📍 የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሌት ፈቃድ ለ2 ዓመት ያገለግላል።
📍 ፈቃዱ ከማብቃቱ ከ3 ወር በፊት እድሳት መጠየቅ ይኖርበታል።

፭. ፈቃድ ስለማገድ እና ስለመሰረዝ

የሚከተሉት ጥፋቶች ፈቃድን ሊያስሰርዙ ይችላሉ፦
❌ ከተፈቀደው ሥራ ውጭ መሥራት
❌ ያለ ባለስልጣኑ እውቅና ፈቃድን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት
❌ በደህንነትና በጥራት ጉድለት አደጋ ማድረስ
❌ የቁጥጥር ስራን ሆነ ብሎ ማሰናከል

✍️ ባለሥልጣኑ ፈቃዱን ከማገዱ ከ30 ቀናት በፊት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።

🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment