-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🏠 የደረጃ "ለ" የኪራይ ግብር መመሪያ (ለመካከለኛ ግብር ከፋዮች)

በተሻሻለው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት የተዘጋጀ

💡 በኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት፣ በደረጃ "ለ" ምድብ ውስጥ የሚካተቱት ዓመታዊ ጠቅላላ የኪራይ ገቢያቸው ከ 500,001 እስከ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር የሆኑ አከራዮች ናቸው። ይህ ደረጃ ከደረጃ "ሐ" በተለየ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ሲሆን፣ ከደረጃ "ሀ" ደግሞ ቀለል ያለ የሪፖርት አቀራረብ ይከተላል።

📌 1. የደረጃ "ለ" ዋና ዋና ግዴታዎች

የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ግዴታ፦ የደረጃ "ለ" የቤት ኪራይ ግብር ከፋዮች የተረጋገጠ የገቢና የወጪ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ሙሉ ሕጋዊ ግዴታ አለባቸው።
የግብር ስሌት መሠረት፦ ግብሩ የሚታሰበው በቀጥታ ከጠቅላላ ገቢው ላይ ሳይሆን፣ ከጠቅላላ ገቢው ላይ ሕጋዊና ሰነድ ያላቸውን ወጪዎች በመቀነስ በሚገኘው "የተጣራ ትርፍ" ላይ ብቻ ነው።

📋 2. ከኪራይ ገቢ ላይ ተቀናሽ የሚሆኑ ሕጋዊ ወጪዎች

የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለባቸው የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች፣ ገቢውን ለማግኘት ያወጧቸው የሚከተሉት ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ ይደረጉላቸዋል፦

አጠቃላይ ወጪዎች፦ ገቢውን ለማግኘት፣ ዋስትና ለመስጠት እና ሥራውን ለማስቀጠል የወጡ ማናቸውም አስፈላጊ ወጪዎች ተቀናሽ ይደረጋሉ።

የመሬት ኪራይና ግብር፦ ቤቱ ያረፈበት የመሬት ኪራይ (ሊዝ)፣ የጥገና ወጪ የእርጅና ቅናሽ፣ የወለድና የሕንጻ ኢንሹራንስ ወጪዎች። እንዲሁም ታክስን ሳይጨምር ለሕንጻው ወይም ለተከራየው ቤት በተገናኘ ለከተማ አስተዳደር የተከፈሉ ማናቸውም ክፍያዎች።

የመገልገያ ወጪዎች (ውሃ፣ ስልክ፣ መብራት)፦ በነፃ ወይም በኪራይ በተያዘው ቤት ስም የሚከፈሉ የውሃ የስልክ እና የመብራት ወጪዎች በውሉ ላይ ተከራይ እንዲከፍል ካልተገለጸና ሕጋዊ ደረሰኝ ከቀረበ ሙሉ በሙሉ በወጪነት ይያዛሉ።

የጋራ ቆጣሪ (75% ቅናሽ)፦ የኪራይ ቤቱ እና የመኖሪያ ቤቱ በአንድ የጋራ መብራት፣ ስልክ ወይም የውሃ ቆጣሪ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ለእነዚህ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 75 በመቶው (75%) ለኪራይ ሥራው እንደወጣ ተቆጥሮ በወጪነት ተቀናሽ ይደረጋል።

የብድር ወለድ ክፍያ፦ ለኪራይ አገልግሎት ለሚውል ሕንጻ መሥሪያ ወይም መግዣ ከባንክ ለተገኘ ብድር የተከፈለ ወለድ፣ ለኪራይ አገልግሎት ከዋለው ወጪ መጠን ልክ ጋር እየተሰላ በወጪነት ይያዛል።

ያልተከራየ ሕንጻ የእርጅና ቅናሽ፦ ለኪራይ የተገነባ ሕንጻ ለሌላ ዓላማ እስካልዋለ ድረስ幕 አከራዩ ሕንጻውን ለኪራይ አገልግሎት ዝግጁ አድርጎት ከሆነ ሕንጻው ባይከራይም እንኳ ለኪራይ እንደዋለ ተቆጥሮ "የእርጅና ቅናሹ" በወጪነት ይያዝለታል።

የማስታወቂያና የማስተዋወቅ ወጪ፦ ሀ) በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚደረግ የቤት ኪራይ ማስታወቂያ ከሆነ ከጠቅላላው የኪራይ ገቢ 3 በመቶ (3%) ባልበለጠ መጠን በወጪነት ይያዛል። ለ) ለኮሙኒኬሽን፣ ብዙኃን መገናኛ (ሚዲያ) ወይም ለማስታወቂያ ድርጅት በሕጋዊ መንገድ የተከፈለ ከሆነ ግን ሙሉ በሙሉ (100%) ተቀናሽ ወጪ ይሆናል።

💰 3. አዲሱ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ምጣኔ ሰንጠረዥ (ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ)

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች ወጪያቸው ተቀንሶ በሚቀረው የተጣራ የዓመት ትርፍ ላይ ግብራቸውን በቅናሽ ቀመር (Deduction Method) ለማስላት ይህንን ይከተላሉ፦
ዓመታዊ የንግድ ሥራ ገቢ (ብር) የታክስ ምጣኔ (%) ተቀናሽ (ብር)
0 - 24,000 0% 0
24,001 - 48,000 15% 3,600
48,001 - 84,000 20% 6,000
84,001 - 120,000 25% 10,200
120,001 - 168,000 30% 16,200
ከ 168,000 በላይ 35% 24,600

📅 4. ግብር የማሳወቂያና የመክፈያ ጊዜ

የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች በየዓመቱ የበጀት ዓመቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት ወራት ውስጥ ግብራቸውን ማሳወቅ አለባቸው። በአዲሱ አዋጅ በተዘረጋው አሠራር መሠረት፣ ግብር ከፋዮች ግዴታቸውን በየ 3 ሩብ ዓመት (Quarterly) ክፍያዎችን እየፈጸሙ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።

⚠️ 5. መዝገብ ላልያዙ ነጋዴዎች የሚጣል ከባድ የግብር ቅጣት!

የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ እያለባቸው መዝገብ ላልያዙ ግብር ከፋዮች፣ በሕጉ መሠረት ከጠቅላላው ዓመታዊ ገቢያቸው ላይ 65% (ስልሳ አምስት በመቶ) ቀጥታ የገቢ ግብር የሚታሰብበት የተጣራ ገቢ ተደርጎ ይወሰዳል። ለነጋዴው እንደ ወጪ የሚታሰብለት 35% ብቻ ይሆናል።

No comments:

Post a Comment