-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

ሳይታደስ 2 አመት ያለፈው ንግድ ፍቃድ ጠቅላላ መረጃ እና ንግድ ፍቃድ መች ነው ተዘጋ የሚባለው?

ለግል ነጋዴዎች (አንቀጽ 94)

• ማንኛውም ነጋዴ የንግድ ሥራውን በማንኛውም ምክንያት የተወ ወይም የንግድ መደብን ያከራየ እንደሆነ፣ ሥራውን ከተወበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመዝገብ እንዲሰረዝ ማመልከት አለበት።
• ከአንድ በላይ የንግድ መደቦች ካሉት እና የተወሰኑትን ብቻ የተወ ከሆነ፣ አስፈላጊው ማስተካከያ በንግድ መዝገብ ውስጥ እንዲገባ ማመልከት አለበት።
✍️ ማለትም 2 ወይም ከዛ በላይ ንግድ ፍቃድ ያለው ሰው በከፊል ያልፈለገውን ንግድ ፍቃድ መዝጋት ይችላሉ።

የነጋዴው ሞት (አንቀጽ 95)

• ነጋዴው በሞተ በ30 ቀናት ውስጥ የሟች ሚስት ወይም ባል ወይም ወራሾች ምዝገባው እንዲሰረዝላቸው ማመልከት አለባቸው። ወራሾቹ ንግዱን በጋራ ለመቀጠል ከፈለጉ ግን በአዲስ መልክ መመዝገብ ይችላሉ።

ምዝገባን በስልጣን ስለመሰረዝ (አንቀጽ 96)

• መዝጋቢው አካል ነጋዴው የንግድ ሥራውን ለማካሄድ ችሎታ እንደሌለው ወይም እንደቆመ ካወቀ፣ በራሱ ተነሳሽነት ምዝገባውን ሊሰርዝ ይችላል።
✍️ የሕግ አንቀጽ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 30(2)(3) መሰረት አንድ ነጋዴዎች ወይም ድርጀት በራሱ ፍላጓት ንግድ ፍቃዱን የመሰረዝ መብት አለው።

የንግድ ማህበር ስለሚፈርስበት ሁኔታ

የንግድ ማህበር በሚከተሉት ምክንያቶች ይፈርሳል፦
• የተቋቋመበት ዓላማ ሲፈጸም ወይም ሊፈጸም ሳይችል ሲቀር።
• የማህበሩ አባላት እንዲቀጥል ካልተስማሙ በስተቀር የማህበሩ ጊዜ ሲያበቃ።
• ማህበርተኞች እንዲፈርስ ሲስማሙ።
• በአባላት መካከል በቂ የሆነ አለመግባባት ሲኖር በፍርድ ቤት ውሳኔ።
• ማህበሩ መክሰሩ በፍርድ ቤት ሲወሰን።

ፈቃድን ባለመመለስ የሚመጡ አደጋዎች

✍️ ተጠያቂነት፦ ፈቃዱ ክፍት እስከሆነ ድረስ በየዓመቱ የሚታሰብ ግብር፣ እየቀጠለ ላልተከፈለው ግብር እና ቅጣት ሁሉ ተጠያቂ እንሆናለን።
• የብድር ተጠያቂነት፦ በግልም ሆነ በድርጅት ስም ብድር ተበድረህ ከሆነ፣ ንግድ ፍቃዱ ሳይታደስ 2 ዓመት ስለሞላው ፍቃዱ ቢታገድም ለብድር፣ ለንግድ ፍቃዱም ተጠያቂነቱ የማይቀር ነው።

የንግድ ፈቃድ ዕድሳትና ህጋዊ እውነታዎች

✍️ 2 አመት ያለፈው ንግድ ፍቃድ አይታደሰም።
• የህግ እውነታው፦ የንግድ ፈቃድ ሳይታደስ 2 ዓመት ሲያልፈው በአዋጅ ይታገዳል እንጂ በራሱ ጊዜ ከሲስተም አይጠፋም።
• አክቲቭ (Active) መሆኑ፦ ፈቃዱ ካለተዘጋ በ eTrade ሲስተም ላይ ሁሌም 2-10 አመት ከእዚያም በላይ ቢሆነውም Active ሆኖ ስለሚቆይ፣ መንግስት እየሰራህ እንደሆነ ሊያሰብ ይችላሉ።
ሌላ ፈቃድ የማውጣት መብት በአንድ ዘርፍ ያልታደሰ ፈቃድ ቢኖርህም፣ በሌላ አዲስ የንግድ ዘርፍ አዲስ ፈቃድ ማውጣት ትችላለህ።

2 አመት ያለፈው ንግድ ፍቃድ መፍትሔ ምንድን ነው?

➡️ መታደስ ስለማይቸል ንግድ ፍቃዱን መዝጋት።

ትክክለኛው የንግድ ፈቃድ መዝጊያ መንገድ

• ከገቢዎች ክሊራንስ ብቻ አይበቃም፦ ብዙ ሰው ከገቢዎች ክሊራንስ ሲያመጣ ፈቃዱ የተዘጋ ይመስለዋል። ይህ ስህተት ነው።
• የመዝጊያ ደብዳቤ፦ ንግድ ፍቃድ ተዘጋ የሚባለው በ eTrade ሲስተም ላይ የመዝጊያ ደብዳቤ ወስደን ስንጨርስ ብቻ ነው።

የንግድ ፈቃድ ያለበትን ደረጃ እንዴት ማወቅ ይቻላል?

• በ Google ላይ etrade.gov.et ብለው ይግቡ።
• "የንግድ ፈቃድ ማጣሪያ" የሚለውን ይጫኑ።
• የቲን (TIN) ቁጥር በማስገባት ንግድ ፍቃዱ ወቅታዊ ሁኔታ ማወቅ ይቻላል።

ለማዘጋት ምን ያስፈልጋል?

• ለግል ነጋዴ፦ ከገቢዎች የሚሰጥ የመዝጊያ ደብዳቤ።
• ለማህበር፦ ከገቢዎች የመዝጊያ ክሊራንስ፣ ኦዲት እና ማህበሩ መፍረሱን የሚገልጽ ቃለ-ጉባኤ።
• ማሳሰቢያ፦ የንግድ ፈቃድ ተዘጋ የሚባለው በ etrade.gov.et ገብተን 52 ብር ከፍለን የመዝጊያ ደብዳቤ ከወሰድን ብቻ ነው። የገቢዎች ክሊራንስ ብቻውን በቂ አይደለም።

በስልክ እንዴት እንዘጋለን?

➡️ etrade.gov.et ብለው ይግቡ።
➡️ የቲን (TIN) ቁጥር በማስገባት
➡️ ስረዛ አገልግሎት መጠየቅ
➡️ የሚጠይቀን ክሊራንስ ማስገባት
➡️ 52 ብር ከፍለን የስረዛ ደብዳቤ መውሰድ።

መልእክት

• 102 ብር ከፍለን ማደስ ስትችሉ አላስፈላጊ ቅጣት ውስጥ አንግባ።
• ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ 2 አመት ሲሞላው ፍቃድ በራሱ ጊዜ ይዘጋል '' ሲስተሙ በራሱ ጊዜ አይዘጋም '' እኛ እስካለዘጋነው ድረስ።

ንግድ ፍቃድ ካልሰራንበት የመዝጋት ጥቅም

1. ከዕድሜ ልክ የግብር ዕዳ መገላገል
2. አዲስ ንግድ የመጀመር መብት
3. ከሕጋዊ ኪሳራ እና ክስ መከላከል
4. የባንክ እና የብድር ታሪክን ማስተካከል
4. የመኪና ንግድ ፍቃድ የመዝጋት ጥቅም፦ መኪናውን የገዛው ሰው ሊብሬውን ወደ ራሱ ስም ለማዞር ሲሄድ፣ የንግድ ፈቃዱ በሥርዓት መዘጋቱን የሚያሳይ ማስረጃ ይጠየቃል።

ማሳሰቢያ

✍️ አሁን ስራ ላይ ያላችሁ ወይም ወደፊት ስራ ለመጀመር ሀሳብ ያላችሁ ንግድ ፍቃድ ካወጣችሁ የማትሰሩበት ከሆነ መዝጋት/መመለስ እንዳትረሱ።
✍️ etrade.gov.et website ወይም ንግድ ፍቃድ በስልክ ለመሰረዝ video ከፈለጉ bio ላይ ወይም chrome ላይ google ላይ heena digital market ብለው ይጎብኙን።
✍️ ማንኛውም በአዲስ ንግድ ፍቃድ፣ በስረዛ፣ በማሻሻል፣ በእድሳት ጥያቄ ወይም ችግር ካጋጠመዎት በetrade (የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር) በነፃ የጥሪ ማዕከል 8588 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

No comments:

Post a Comment