-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

Heena Digital Market

🎯 PLC ለመመስረት መታለፍ
የሌለባቸው 10 ስህተቶች

1
የአላማ (Object) ስህተት፦ አላማ ስናስገባ ከእኛ ጋር የማይሄድና ከሰው የተገለበጠ አላማ መጻፍ ትልቅ ስህተት ነው። አላማው በግልጽ ካልተጻፈ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት እንቸገራለን። መጀመሪያ አሁን የምንሰራውንና ወደፊት ያሰብናቸውን አላማዎች መጥቀስ አለብን።
2
የካፒታል መጠን አለመመጣጠን፦ ከሚሰሩት ስራ አንጻር በጣም ትንሽ ወይም በጣም ግዙፍ ካፒታል መጥቀስ ለግብር ወይም ለብድር እንቅፋት ይሆናል።
3
የባንክ ማረጋገጫ (Bank Letter)፦ ካፒታሉን በዝግ አካውንት በPLC ስም ገቢ የተደረገበት ደብዶቤ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ ምዝገባ ማውጣት አይቻልም፤ ስለዚህ መጀመሪያ የምናስመዘግበውን ካፒታል ማወቅ አለብን።
4
የስራ አስኪያጅ ስልጣን አለመገደብ፦ ስራ አስኪያጁ ያለ መሥራቾች ፈቃድ ንብረት እንዳይሸጥ ወይም ውል እንዳይገባ መገደብ አለበት።
የንብረት ሽያጭ ገደብ፦ መኪና፣ ህንጻ ወይም መሬት ለመሸጥ የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ግዴታ መሆን አለበት።
የብድር ገደብ፦ ከአንድ የተወሰነ መጠን በላይ ብድር ለመበደር የመሥራቾች የጽሁፍ ፈቃድ ያስፈልጋል።
የባንክ ሂሳብ፦ በድርጅቱ አባላት በጣምራ ፊርማ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ይቻላል።
5
የኪሳራ ክፍፍል ቀመር አለመኖር፦ ብዙዎች ትርፍ ላይ ብቻ ያተኩራሉ፤ ኪሳራ እንዴት እንደሚጋራ በመተዳደሪያ ደንብ ላይ በአባላት በሚገባው መልኩ በግልጽ መቀመጥ አለበት።
6
የመሥራቾች መታወቂያ፦ ሁሉም አባላት "ፋይዳ" እና የግል "ቲን" (TIN) ማዘጋጀት እንዳለባቸው ቀድመን ማሳወቅ አለብን።
7
የቤት ኪራይ ውል ህጋዊነት፦ መጀመሪያ የኪራይ ውል ማዘጋጀት አለብን። TIN ለማውጣት መመስረቻው ላይ ያለው አድራሻና የኪራይ ውሉ አድራሻ መመሳሰል አለበት።
8
የስብሰባ ስነ-ስርዓት አለመጥቀስ፦ አንድን ውሳኔ ለማሳለፍ በትንሹ ስንት አባላት መገኘት እንዳለባቸው (Quorum) በዝርዝር ካልተቀመጠ ጥቂት አባላት የሁሉንም እጣ ፈንታ ሊወስኑ ይችላሉ።
9
የአክሲዮን ዝውውር ስነ-ስርዓት፦ "ቅድሚያ የመግዛት መብት" ካልተጠቀሰ፣ አንዱ መሥራች ድርሻውን ለድርጅቱ ጠላት ለሆነ ሰው ሊሸጥ ይችላል። ማንኛውም አባል ድርሻውን ከመሸጡ በፊት መጀመሪያ ለአባላቱ ማቅረብ እንዳለበት በሕግ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
10
የድርጅቱ መፍረሻ ሁኔታ፦ ድርጅቱ ቢከስር ወይም አባላቱ ቢጣሉ ንብረቱ እንዴት እንደሚከፋፈል፣ ንብረት አጣሪ እንዴት እንደሚሰየም አስቀድሞ በመመሪያው ላይ በግልጽ መቀመጥ አለበት።

No comments:

Post a Comment