-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🏠 የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በተመለከተ ትኩረትና ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ነጥቦች

1
በስጦታ፣ በሽያጭ ወይም በሌላ መንገድ ተገልጋዮች ንብረት ለማስተላለፍ ሲመጡ ካርታው ከጀርባው የተረጋገጠ መሆን አለበት። ካርታው ዲጂታል ከሆነ ግን የጀርባ ማህተም አያስፈልገውም።
2
በካርታው ከጀርባ ላይ ንብረቱ በውርስ የተገኘና የወራሾች ዝርዝር የተጻፈበት ከሆነ ተጨማሪ ማስረጃ ማየት ሳያስፈልግ ማስተናገድ ይቻላል። ሆኖም የንብረቱ መለያ ተጠቅሶ ወራሾች መሆናቸው በደብዳቤ ከተገለጸ አገልግሎቱን መስጠት ይቻላል።
3
በውርስ ወይም በስጦታ የተገኘ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም ለማከራየት የጋብቻ ማስረጃ አይጠየቅም
4
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ የተመዘገቡ የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይነቀሳቀሱ ንብረቶችን የማስተላለፍ ወይም ለማከራየት አገልግሎት ማግኘት የሚቻለው ንብረቱ በሚገኝበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ነው። ስለዚህም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የቋሚ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሊስተናገዱ አይችሉም።
5
ከጋብቻ በፊት በቋሚነት ቀርበው የንብረት ማግለያ ውል ያደረጉ ወይም በፍርድ ቤት ያጸደቁ ተጋቢዎች ንብረታቸውን ለማስተላለፍ ወይም ለማከራየት ሲመጡ የትዳር አጋራቸው ስምምነት አያስፈልጋቸውም። ሆኖም የንብረት ማግለያ ስምምነቱ አሁን ካለው ጋብቻ ጋር የተደረገ መሆን አለበት።
6
አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆች ንብረት ለመግዛት ቢቻል ሁለቱም ወላጆች ሊገኙ ይገባል። ካልሆነ አባት ወይም እናት ቀርበው መግዛት ይችላሉ። ሆኖም ከእናትና አባት ውጭ የሆነ ሞግዚት አካለ መጠን ላልደረሰው ልጅ ስም ንብረት ለመግዛት በፍርድ ቤት የተሰጠ ተጨማሪ ስልጣን ሊቀርብ ይገባል።
7
አካለ መጠን ባልደረሰው ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ሞግዚቱ እናትና አባትም ቢሆኑ በፍርድ ቤት የተሰጠ ተጨማሪ ስልጣን ሊቀርብ ይገባል።
8
ያለጋብቻ ማስረጃ ላይ ቀደም ሲል ጋብቻ ስለመኖሩ የሚጠቁም የጊዜ መረጃ ሲኖር ንብረቱ በጋብቻ ወቅት የተፈራ ሊሆን ስለሚችል ንብረቱ የተፈራበትን ጊዜ የሚያመላክት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ተጨማሪ ማስረጃ ሊቀርብ ይገባል።
9
ተነጻጻሪ ካርታ፦ ማለት በአንድ የቦታ ስፋት ውስጥ የተለያዩ ቤቶችና ባለቤቶች ያሉበትና በተለያዩ ሰዎች ሊያዙ የሚችል ነው። ነገር ግን በዚህ ይዞታ ላይ የባለቤትነት መብት ያለው ሰው የራሱን ካርታ በመያዝ ድርሻውን ጠቅሶ መሸጥ ይችላል።
10
ካርታ ላይ የሚጠቀሰው ቀን ካርታው የተሰጠበትን ቀን እንጂ ንብረቱ የተፈራበትን ቀን በቀጥታ ላያመለክት ይችላል። ስለሆነም ንብረቱ የተፈራበትን ቀን ለማወቅ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የንብረቱ ባለቤት ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያቀርብ መደረግ አለበት። (ለምሳሌ፦ ከመሬት አስተዳደር፣ ከገቢዎች እና ለካርታው ባለቤት የሚሰጡ ደብዳቤዎችን አያይዞ መስራት ይቻላል።)
11
የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ ለማስተላለፍ የፍርድ ውሳኔ ይዘው የሚቀርቡ ባለጉዳዮች ንብረቱ የጋራ ወይም የግል ስለመሆኑ በፍርድ ቤት የጸደቀ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ወይም ውሳኔ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12
ንብረት በስጦታ ለማስተላለፍ የተሰጠ የውክልና ስልጣን ለስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና ንብረቱ ምን አይነት እንደሆነ በውክልናው ላይ በግልጽ መቀመጥ አለበት። ነገር ግን በውክልና ስጦታ ለመቀበል ሲሆን "ስጦታ ይቀበልልኝ" የሚለው አገላለጽ በቂ ነው።
13
የጋራ ንብረት በሽያጭ በሚተላለፍበት ጊዜ ገዢው ከንብረት ተጋሪው ውጭ የሆነ ከሆነ የተጋሪው የቅድሚያ መግዛት መብት መጠበቁን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በመሆኑም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን ተጋሪውን ምስክር በማድረግ፣ ለሚንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን ተጋሪው ማረጋገጫ እንዲሰጥ በማድረግ ይቻላል።
15
የማይንቀሳቀስ ንብረት ገዢው የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ የታደሰ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ወይም በኢንቨስትመንት አዋጁ መሰረት ቢያንስ አስር ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በስራ ላይ ማዋሉን የሚገልጽ ማስረጃ እና የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሊቀርብ ይገባል።
16
የማይንቀሳቀስ ንብረት ገዢው የውጭ ሀገር ዜጋ ሌላ የመኖሪያ ቤት በስሙ የሌለ መሆኑን የሚገልጽ ከሚመለከተው የንብረት መዝጋቢ አካል ማስረጃ መቅረብና ከተቋሙ የመረጃ ቋት መጣራት ይኖርበታል።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment