-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

📜 አዲስ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት

ማወቅ ያለብን 7 ወሳኝ ቅደም-ተከተሎች

፩. አስፈላጊ ሰነዶችና ዝግጅት

1. ፋይዳ መታወቂያ፦ ዲጂታል መታወቂያ መያዝ የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ ነው።

2. ህጋዊ የቤት ኪራይ ውል፦ ለስራው የሚሆን ቢሮ ወይም ሱቅ ህጋዊ የኪራይ ውል ሊኖረን ይገባል። ውሉ የግድ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ መሆን አለበት።

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፦ የኪራይ ውሉን ወደ ገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፍ በማቅረብ የቲን (TIN) ቁጥር ማውጣት።

4. ለማህበራት (PLC)፦ የምናወጣው ለ PLC፣ ለባለአንድ አባል ማህበር ወይም ለተለያዩ ማህበራት ከሆነ በውልና ማስረጃ የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ መያዝ ግዴታ ነው።

5. የማህበር አባላት መረጃ፦ ማህበር ከሆኑ የሁሉም አባላት ፋይዳ መታወቂያ እና የግል TIN ማቅረብ ይኖርብዎታል።

6. የካፒታል ምዝገባ፦ ማህበር ከሆነ እንደ ስራው አይነት ያስመዘገቡትን የመነሻ ካፒታል የባንክ ዝግ ሂሳብ ማስረጃ (Bank Letter) ከባንክ ማፃፍ አለባቸው። ምዝገባው እስኪያልቅ ድረስ ሂሳቡ ዝግ ሆኖ ይቆይና ከዚያ በኋላ ተመላሽ ይሆናል።

7. የብቃት ማረጋገጫ (Competency)፦ አንዳንድ የስራ ዘርፎች (ለምሳሌ፦ ህክምና፣ ምግብ አስመጪ ወዘተ...) ንግድ ፈቃድ ለማውጣት የብቃት ማረጋገጫ ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ አስቀድሞ ማውጣት ያስፈልጋል።

፪. በስልክዎ በ eTrade ለማውጣት

ከላይ የተጠቀሱትን 7 ነጥቦች ካሟሉ በኋላ፣ ወደ ቢሮ መሄድ ሳያስፈልግዎ በኢትዮጵያ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኦንላይን ሲስተም (eTrade) በስልክዎ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
1. ወደ ድረ-ገጹ ይግቡ፦ በስልክዎ etrade.gov.et ብለው ይጻፉ። 2. መመዝገብ፦ etrade.gov.et ከከፈተ በኋላ የመዝገብ / Register የሚለውን ይጫኑ። 3. የቲን ቁጥር፦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርዎን በምናስገባበት ሰዓት መረጃዎን በራሱ ይዞልን ይመጣል። 4. ህጋዊ ተቋም፦ የሚለው ላይ በጥንቃቄ ሙሉ የራሳችሁን ህጋዊ ተቋም ያስገቡ (የግል ከሆነ የግል፣ PLC ከሆነ PLC፣ ባለአንድ አባል ከሆነ ባለአንድ PLC)።
✍️ ይህ ካልሆነ ሳይቱን ለማዞር ሌላ ጣጣ ነው፤ ስለዚህ በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልጋል።
5. ክልል እና ቋንቋ፦ የሚኖሩበትን ክልል እና የሚፈልጉትን ቋንቋ ያስገቡ። 6. ይለፍ ቃል (Password)፦ የማይረሱትን Password ያስገቡ። ለምሳሌ፦ ምልክቶች ($&@#), ትላልቅና ትናንሽ ፊደላት እንዲሁም ቁጥሮችን ይጠቀሙ። ከ 6 ማነስ የለበትም፤ በሁለት የይለፍ ቃል በማስገባት ያረጋግጡ። 7. ስልክ ቁጥር፦ የሚሰራ ስልክ ቁጥር ያስገቡ። የይለፍ ቃል መቀየር ቢፈልጉ እንዳይቸገሩ የሚሰራ ስልክ መሆኑን ያረጋግጡ።

፫. ሰነዶችን መጫንና ማጠናቀቅ

ከተመዘገቡ በኋላ የ eTrade መመሪያ ይመጣል፤ "እስማማለሁ" ብለው መግባት ነው። "ያስፈልገናል" የሚለው ቦታ ላይ መረጃዎችን ማስገባት ግዴታ ነው።
✍️ ለግል ነጋዴዎች፦ ፋይዳ መታወቂያ፣ ፎቶ (3x4) እና ቲን (TIN)።
✍️ ለማህበራት (PLC)፦ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የስራ አስኪያጅ ፋይዳ መታወቂያ፣ የስራ አስኪያጅ ፎቶ (3x4)፣ ከባንክ የተፃፈ ዝግ የባንክ ደብዳቤ እና ቲን (TIN)።

ያዘጋጇቸውን ሰነዶች ካስገቡ በኋላ ይጫኑ (Upload) አድርገው ወደ eTrade ይላኩ። ሰነዶቹ ትክክለኛ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በስልክዎ ወይም በ eTrade "ጸድቋል" የሚል መልእክት ይላክልዎታል። ከዚያ አገልግሎቱን መጠየቅ ነው።

⚠️ ማሳሰቢያ

ንግድ ምዝገባ እና ንግድ ፈቃድ ስታወጡ በጥንቃቄና በኃላፊነት አውጡ።

✍️ የአዲስ ንግድ ፈቃድ አወጣጥ ቪዲዮ፣ የስራ ዘርፍን መለየት እና የ eTrade ዌብሳይት ለማግኘት በፕሮፋይላችን ያለውን የ Heena Digital Market ሊንክ ይጫኑ።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment