-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

💼 ባለአንድ አባል ኃ/የግ/ማኅበር (One-Person PLC) ከመመስረትዎ በፊት ማወቅ ያለብዎት 10 ነጥቦች

💡 የንግድ ሕጉ ባስተካከለው መሠረት በአንድ ሰው ብቻ የሚመሰረት የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (One-Person PLC) መመስረት ተችሏል። ይህንን ማኅበር ከመመስረትዎ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ብቸኛ ባለቤትነት

ድርጅቱ በአንድ ሰው ብቻ ይመረታል፤ ሸሪክ ወይም ሌላ ሁለተኛ ሰው መፈለግ አያስፈልግዎትም።

2. የተወሰነ ተጠያቂነት

ልክ እንደ መደበኛ የንግድ ማህበር (PLC)፣ ድርጅቱ ዕዳ ውስጥ ቢገባ የሚጠየቀው ድርጅቱ ራሱ እንጂ የባለቤቱ የግል ንብረት (ቤት፣ መኪና ወይም የባንክ አካውንት) አይነካም።

3. መነሻ ካፒታል እና የባንክ ሂሳብ

ዝቅተኛው መነሻ ካፒታል 15,000 ብር ነው። ይህ ገንዘብ በማህበሩ ስም በሚከፈት ዝግ የባንክ ሂሳብ (Blocked Account) ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት። ምዝገባው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅና የንግድ ምዝገባ ካወጡ በኋላ ብሩን ወጪ በማድረግ ማንቀሳቀስ ይቻላል።

4. የውሳኔ ሰጪነት ነፃነት

ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ወይም የሌላ ሰውን ፈቃድ መጠበቅ አያስፈልግም። ብቸኛው አባል የጠቅላላ ጉባኤውን ሥልጣን በሙሉ በግሉ ይይዛል።

5. የሥራ አስኪያጅ ምርጫ

ባለቤቱ ራሱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሆን ይችላል፤ ወይም ሌላ ውጭ ሰው በቅጥር ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾም ይችላል።

6. የመመስረቻ ጽሁፍ (Memorandum of Association)

ምንም እንኳን ድርጅቱ የአንድ ሰው ቢሆንም፣ የድርጅቱን ዓላማና መዋቅር የያዘ ሕጋዊ የመመስረቻ ጽሁፍ ማዘጋጀት እና በውልና ማስረጃ ማፅደቅ ግዴታ ነው።

7. የድርጅቱ ስም አሰያየም

በስሙ መጨረሻ ላይ "ባለአንድ አባል ኃ/የግ/ማ" የሚል ሐረግ መጨመር ግዴታ ነው። (ለምሳሌ፦ ሄና ባለአንድ አባል ኃ/የግ/ማ ወይም ሄና ትሬዲንግ ባለአንድ አባል ኃ/የግ/ማ)።

8. የእጩ ንብረት ጠባቂ ግዴታ

ባለቤቱ ብቻውን ስለሆነ፣ መመስረቻ ጽሁፉ ውልና ማስረጃ ሲጸድቅ አብሮ የሚቀርብ እና የሚፈርም "የእጩ ንብረት ጠባቂ" (Nominee) ያስፈልጋል። ይህ ሰው የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ሊኖረው ይገባል።

9. በዓይነት የሚደረግ መዋጮ

የመጀመሪያው መዋጮ በጥሬ ገንዘብ ሳይሆን በዓይነት (በንብረት) ከሆነ፣ የንብረቱ ግምት ትክክል መሆኑ በምሥረታ ወቅት በተሾመ ገለልተኛ ኦዲተር ሪፖርት መረጋገጥ አለበት።

10. ራሱን የቻለ ሕጋዊ ሰውነት

ማኅበሩ ከአባሉ የተለየና የተነጠለ የራሱ የሕግ ሰውነት አለው። ባለቤቱ ቢሞት እንኳ ድርጅቱ ሳይፈርስ በወራሾች ሊቀጥል ይችላል። እንዲሁም በየዓመቱ የሂሳብ ምርመራ በገለልተኛ ኦዲተር የማስመርመር ግዴታ አለበት።

📋 የምስረታ እና የፍቃድ አወጣጥ ቅደም-ተከተል (Steps)


1️⃣ የስም ስያሜ ማውጣት፦ የንግድ አድራሻዎ (ኪራይ ውልዎ) በሚገኝበት ክፍለ ከተማ በመሄድ የድርጅት ስም ያስመዝግቡ። የኪራይ ውል ከመዋዋልዎ በፊት የስም ስያሜ ማውጣቱ ግዴታ ነው፤ ምክንያቱም የኪራይ ውሉ በማህበሩ አዲስ ስም መፈረም ስላለበት።

2️⃣ የመመስረቻ ጽሁፍ ማዘጋጀት፦ ሊሰሩበት ያሰቡትን የንግድ ዘርፍ (ዓላማ) በመጥቀስ መመስረቻ ጽሁፍ ያዘጋጁ።

3️⃣ የባንክ አካውንት መክፈት፦ በማህበሩ ስም ዝግ አካውንት በመክፈት መነሻ ካፒታሉን ያስቀምጡ።

4️⃣ ውልና ማስረጃ ማጽደቅ፦ ባለቤቱ እና እጩ ንብረት ጠባቂው የፋይዳ መታወቂያቸውን ይዘው ውልና ማስረጃ በመቅረብ የመመስረቻ ጽሁፉን ያጽድቁ።

5️⃣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት፦ መመስረቻው ከጸደቀ በኋላ የቲን ቁጥር ያውጡ። (ማሳሰቢያ፦ ቀደም ሲል የግል ንግድ ፈቃድ የነበረዎት ከሆነ፣ የዕዳ ክሊራንስ ደብዳቤ ከገቢዎች ይዘው መምጣት ይኖርብዎታል)

6️⃣ የንግድ ፈቃድ ማውጣት፦ በመጨረሻም በ etrade.gov.et ሲስተም ላይ በመግባት የንግድ ፈቃድዎን በቀላሉ ያውጡ።

➡️ ስለ ባለአንድ አባል ኃ/የግ/ማኅበር ይበልጥ ማወቅ ይፈልጋሉ?

ዝርዝር የአገልግሎት ማውጫ መመሪያውን እዚሁ ድረ-ገጻችን ላይ ማንበብ ይችላሉ።

🛍️ ለምስረታ የሚሆን ዝግጁ "ባለአንድ አባል ኃ/የግ/ማኅበር የመመስረቻ ጽሑፍ ሰነድ" ለመግዛት ከፈለጉ ዌብሳይታችን ላይ ያገኛሉ።

No comments:

Post a Comment