-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 ንግድ ፍቃድ በስልክ ለማደስ

ንግድ ፍቃድ በስልክ ለማደስ

🏢 ንግድ ፍቃድ ለመሰረዝ

ንግድ ፍቃድ ስረዛ

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 ለ ደረጃ ለ'' የግብር ስሌት

የንግድ ገቢ ግብር ለደረጃ ለ ስሌት

🏢 ሀ ደረጃ ለ'' የግብር ስሌት

የንግድ ገቢ ግብር ለደረጃ ሀ ስሌት

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🏠 የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር መመሪያ

በከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 መሠረት የተዘጋጀ

💡 የሕግ ማዕቀፍ፦ በስመ ንብረት ዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2 አንፃር የተቃኙ ሲሆን፣ ዝርዝር መስፈርቶቹ ከዚህ በታች በቀረቡት ዋና ዋና ክፍሎች ተደራጅተዋል።

ሀ/ በዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው አጠቃላይ መረጃዎች

የከተማ ቤትና ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር ለመፈጸም የሚከተሉት ዋና ዋና ማስረጃዎች/ሰነዶች መሟላት ይኖርባቸዋል፦

✍️ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ፦ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ።
✍️ የግንባታ ፕላን፦ ጸድቆ የተሰጠ የግንባታ ፕላን፣ የስራ ዝርዝር ግምት ወይም የጸደቀ የነባር ግንባታ ፕላን።
✍️ የግንባታ ደረጃ (50%+)፦ ጸድቆ በተሰጠው የግንባታ ፕላን መሰረት ስለመገንባቱ እና ግንባታው ያለበት ደረጃ የተረጋገጠበት ማስረጃ (50 በመቶ እና ከዚያ በላይ)።
✍️ የሊዝ ዕዳ ማረጋገጫ፦ ውዝፍ የሊዝ ኪራይ ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ወይም ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳውን ገዥው ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጠበት የስምምነት ደብዳቤ።
✍️ ከዕገዳ ነፃ መሆኑ፦ በንብረቱ ላይ የባንክ እዳ ወይም የፍርድ ቤት ዕግድ የሌለበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሲቀርብ።
✍️ የሕግ ባለመብትነት ማስረጃ፦ የቤትና ይዞታ ስም ዝውውር ጥያቄው የቀረበው በህግ ባለመብት/በውርስ/በፍርድ አፈጻጸም ወይም በውክልና ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ።
✍️ የውልና ማስረጃ ሰነድ፦ በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ ወይም ስጦታ ስምምነት ከሆነ በውልና ማስረጃ በአካል ቀርቦ በእማኞች የተፈረመ የስምምነት የውል ማስረጃ ሲቀርብ።

ለ/ በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሚተላለፍ ይዞታ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

በሽያጭ ወይም በስጦታ የሚተላለፍ ቤትና ይዞታ ስም-ዝውውር በሚፈጸምበት ጊዜ የሚከተሉት ነጥቦች በተግባር መረጋገጥ አለባቸው፦

✍️ ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱ ሲረጋገጥ።
✍️ የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በፍትህ ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ ሲጸድቅ።
✍️ ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ።
✍️ በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማረጃ ሲቀርብ።
✍️ የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ሲረጋገጥ።

💡 ዝውውሩ የሚፈፀመው በሊዝ በተገኘ ይዞታና ግንባታ ላይ ከሆነ፦

• የሊዝ ይዞታ ባለቤትነት ኦሪጅናል ካርታና ውል ሲቀርብ።
• በሊዝ ውል መሰረት ክፍያው የተጠናቀቀና ሌሎች ግዴታዎቹን የተወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ፤ ወይም የሊዝ እዳው ያልተጠናቀቀ ከሆነ ስም የሚዞርለት ወገን እዳውን ለመክፈል እና ነባሩን የሊዝ ውል ግዴታዎች የተቀበለ ስለመሆኑ ከከተማው በጽሁፍና በፊርማ አረጋግጦ ሲያቀርብ።
• በሊዝ የተገዛን የመሬት ይዞታ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በቅድሚያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን የግንባታ ደረጃ ያሟላ መሆኑ ወይም የግንባታ ፈቃድ የጊዜ ገደብ ያላለፈ ወይም የግንባታ ማራዘሚያ የተፈቀደለት መሆኑ ሲረጋገጥ።
• የከተማ ቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በውልና ማስረጃ ቀርቦ ሲጸድቅ ይሆናል።

ሐ/ በውርስ የተገኘ ይዞታና ቤት የባለቤትነት ስመ-ንብረት ዝውውር

(ሀ) በውርስ የተላለፈ ነባር ይዞታ ዝውውር ለመፈፀም፦

• የሚዛወረው የመሬት ይዞታ ወይም ቤት ህጋዊ የባለቤትነት ማስረጃ/ካርታ ሲኖረው።
• ወራሾች የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስረጃ ሲያቀርቡ።
• ወራሾች በውርስ ያገኙትን ይዞታ ወይም ቤት በየግላቸው የባለቤትነት ማስረጃ ለመያዝ ሲፈልጉ ለእያንዳንዳቸው ድርሻ መጠን በፍርድ ቤት የፀደቀ ማስረጃ ሲያቀርቡ ወይም የሁሉም ወራሾች የጋራ ስምምነት በውል አፅዳቂ አካል ጸድቆ ሲቀርብ።
• የእያንዳንዱ ወራሽ የድርሻ መጠን በፍርድ ቤት ያልተረጋገጠ ከሆነ የስም ዝውውሩ በሁሉም ወራሾች ስም በጋራ የሚፈፀም ይሆናል።

⚠️ የፍርድ ቤቱ የውርሱ ውሳኔ የይዞታ ክፍፍልን የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ የሚፈፀመው የወቅቱን አነስተኛ የይዞታ መጠን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ካልሆነም በተነፃፃሪ የመሬት ይዞታ ድርሻ ህግ ወይም በጋራ ሰነድ/ካርታ መሰረት ይስተናገዳል።

(ለ) በሊዝ የተያዘ ይዞታ ለህጋዊ ወራሽ የሚተላለፍበት ሁኔታ፦

• አውራሹ በገባው የሊዝ ውል ግዴታ መሰረት አመታዊውን የሊዝ ክፍያ የፈፀመና ሌሎች የሊዝ ግዴታዎችን በተገቢው መንገድ የተወጣ ሲሆን።
• ወራሽ አውራሽ የገባቸውን የውል ስምምነቶች (የሊዝ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት) ሙሉ በሙሉ የተቀበለ መሆኑን በፊርማው ሲያረጋግጥና ውዝፍ ክፍያ ካለ ከፍሎ ደረሰኝ ሲያቀርብ ይሆናል።

⚠️ ግንባታ ስላልተጀመረበት ቦታ የሚጣል ገደብ

ይዞታው በውሉ መሰረት ግንባታ ለመጀመር የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ያለፈበት እና ግንባታው ያልተጀመረ ከሆነ በውርስ ሊተላለፍ አይችልም! ውሉ ተቋርጦ ቦታው ለከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ተመላሽ ይሆናል።
💡 ነገር ግን አውራሽ በይዞታው ላይ ግንባታ ያልጀመረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ከተረጋገጠ፣ ለአውራሽ ሊፈቀድ የሚችለው የግንባታ መጀመሪያ የማራዘሚያ ጊዜ ለወራሽ ሊፈቀድለት ይችላል።

መ/ በባንክ ሐራጅ የሚሸጥ እና የሚወረስ ቤት የባለቤትነት ዝውውር

በባንክ የሐራጅ ጨረታ አሸናፊ ለሆኑ ወይም ንብረቱ ለሚተላለፍላቸው ወገኖች መሟላት ያለባቸው ዝርዝሮች፦

✍️ የባንክ ህጋዊ ደብዳቤ፦ በባንክ የተሸጠ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር ለመፈፀም በሐራጅ ጨረታው አሸናፊ የሆነው ሰው ያሸነፈበትን ዋጋና ለዝውውሩ በውል የገባቸው ግዴታዎች ተገልፀው ከባንኩ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤና ውል ሲቀርብ።
✍️ የሰነድ ማረጋገጫ፦ በባንክ ዋስትና ተይዞ የነበረው ይዞታ የባለቤትነት ማረጋገጫ/ካርታ በማህደሩ ውስጥ ካለው ሰነድ ጋር ተገናዝቦ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ።
✍️ ከሌላ ዕዳ ነፃ መሆኑ፦ ይዞታው በሌላ ባንክ ብድርና ዋስትና ያልተያዘ ወይም እገዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ።
✍️ የደረጃ ዋስትና ፈቃድ፦ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዋስትና የተመዘገበ ዋስትና ያለው ባንክ መኖሩ ከተረጋገጠ ባንኩ ስለ ይዞታው መሸጥ ሲፈቅድ።
✍️ ሰነድ አልባ ይዞታዎች፦ በባንክ ሐራጅ ሽያጭ እንዲዞር የተጠየቀው ቤትና ይዞታ የተሟላ ሰነድ የሌለው/ሰነድ አልባ ከሆነ በቅድሚያ በሥራ ላይ ባለው የሰነድ አልባ መመሪያ መሰረት ሰነድ ተሰጥቶት ሲቀርብ።
✍️ የአገልግሎት ክፍያ፦ ባንኩ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ የሚረከብ ከሆነ የቤቱና ይዞታው ግምት እንደማንኛውም ቋሚ ንብረት ግምት ተሰልቶ ተገቢውን የአገልግሎትና የገቢ ክፍያ ሲፈጸም።
✍️ የጨረታ መነሻ ግምት፦ ቤቱና ይዞታው ባንኩ በሚያወጣው ጨረታ የሚሸጥ ከሆነ ባንኩ ያቀረበው የጨረታ መነሻ ዋጋ በከተማው በኩል ተገቢ መሆኑ ተረጋግጦ በጨረታ ሲሸጥ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን ስለመፈጸሙ የክፍያ ደረሰኝ ማስረጃ ሲያቀርብ የስመ-ንብረት ዝውውሩ የሚፈጸም ይሆናል።

🎯 የ Heena Digital Market መረጃዎችን ለማግኘት

No comments:

Post a Comment