-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🏠 የደረጃ "ሐ" የኪራይ ግብር መመሪያና ማብራሪያ

💡 በኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት፣ በደረጃ "ሐ" ምድብ ውስጥ የሚካተቱት ዓመታዊ ጠቅላላ የኪራይ ገቢያቸው ከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ አከራዮች ናቸው። ይህ የግብር ከፋይ ክፍል የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የለበትም፤ ነገር ግን ግብሩን በየዓመቱ ማሳወቅና መክፈል ይኖርበታል።

📌 1. ማን በደረጃ "ሐ" ይካተታል?

አንድ ግለሰብ ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ቤቶች የሚያገኘው ዓመታዊ የኪራይ ገቢ ተደምሮ እስከ 500,000 ብር የሚደርስ ከሆነ በደረጃ "ሐ" ይመደባል።

📝 2. የግብር አከፋፈል ሂደት

የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ስለማይይዙ፣ ግብራቸው የሚሰላው በሁለት መንገድ ሊሆን ይችላል፦

በውል ስምምነት መሠረት፦ በገቢዎች ሚኒስቴር የታወቀና የተመዘገበ ሕጋዊ የኪራይ ውል ካለ፣ በውሉ ላይ ባለው የገቢ መጠን መሠረት ግብሩ ቀጥታ ይታሰባል።

በግምት (Assessment)፦ የተመዘገበ ውል ከሌለ ወይም የቀረበው የገቢ መጠን ከወቅቱ የገበያ ዋጋ በጣም ያነሰ ሆኖ ሲገኝ፣ የግብር ባለሥልጣኑ በግምት ግብር ሊጥል ይችላል።

💰 3. የኪራይ ግብር ስሌት (Tax Rates)

የኪራይ ግብር የሚሰላው ከጠቅላላ ገቢው ላይ የተወሰኑ ሕጋዊ ወጪዎች ተቀንሰው ነው። ለደረጃ "ሐ" የሚከተሉት ነጥቦች ግምት ውስጥ ይገባሉ፦
⚙️ የጥገና ወጪ ማቅለያ፦
ለመኖሪያ ቤት ከሆነ 50% የሚሆነው ገቢ ለጥገናና ለሌሎች ወጪዎች ታሳቢ ተደርጎ በነፃ ይለቀቃል። ግብር የሚታሰበው በቀረው 50% ገቢ ላይ ብቻ ነው!

📅 4. ግብር የሚከፈልበት ጊዜ

የደረጃ "ሐ" የኪራይ ግብር ከፋዮች በአዱሱ በተሻሻለው አዋጅ 2017ዓ.ም የከፈሉትን ግብር በየ 3 ሩብ አመት ግብራቸውን መከፈል አለባቸው 4ኛ ሩብ አመት ላይ የከፈሉት ግብር ብልጫ ካለው ተመላሽ ይሆናል ያነሰ ከሆነ ልዩነቱን ይከፍላሉ።

⚠️ 5. ግብር አለመክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ግብርን በወቅቱ አለማሳወቅ ወይም ዘግይቶ መክፈል ለአስተዳደራዊ ቅጣት እና ለከፍተኛ ወለድ ይዳርጋል። ስለዚህ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታን በአግባቡ መወጣት እጅግ ተገቢ ነው።

💡 ጠቃሚ ምክር

ለበለጠ መረጃ እና ትክክለኛውን የቤት ኪራይ ግብርዎን በቀላሉ ለማስላት የኛን ግብር ማስያ የሚለውን ጠቅላላ አመታዊ ገቢ በማስገባት የኪራይ ግብር ይወቁ [ደረጃ "ሐ" የኪራይ ግብር ማስያ] ይጠቀሙ!

No comments:

Post a Comment