-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

☕ የቡና ንግድ ፈቃድ መመሪያ

የኤክስፖርት ቡና ብቃት ማረጋገጫና መስፈርቶች

1. መሰረታዊ የሰነድ መስፈርቶች

ማመልከቻ ደብዳቤ፦ በባለቤቱ ወይም በዋና ሥራ አስኪያጁ የተፈረመ።
ዲጂታል መታወቂያ፦ የሥራ አስኪያጁ/ባለቤቱ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ።
ከወንጀል ነጻ ማስረጃ፦ ከወንጀል ምርመራ ቢሮ የጣት አሻራ ውጤት።
TIN እና ንግድ ምዝገባ፦ ህጋዊ የግብር ከፋይነትና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት።
ቢሮ፦ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተርና አስፈላጊ የቢሮ ቁሳቁሶች የተሟሉበት ቢሮ (ካርታ ወይም የጸደቀ ውል)።

2. የካፒታልና የፋይናንስ መስፈርት

እንደ ተቋሙ አይነት የሚፈለገው የመነሻ ካፒታል ዝርዝር፦
💰 ለግለሰብ አመልካች፦ ቢያንስ 15,000,000 (አስራ አምስት ሚሊየን ብር) የባንክ ደብዳቤ እና የአንድ ዓመት ባንክ ስቴትመንት።
💰 ለንግድ ማህበራት (PLC)፦ ቢያንስ 20,000,000 (ሃያ ሚሊየን ብር) የባንክ ደብዳቤ እና የከፍተኛ አክሲዮን ድርሻ ያላቸው አባላት የባንክ ስቴትመንት።
💰 ለባለአንድ አባል PLC፦ ቢያንስ 20,000,000 (ሃያ ሚሊየን ብር) በማህበሩ ስም ያለ የባንክ ደብዳቤ እና የባለቤቱ ባንክ ስቴትመንት።

3. የኢንዱስትሪና የላቦራቶሪ ብቃት

📍 ማዘጋጃና ማከማቻ፦ የቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ብቃት ማረጋገጫ (የባለቤትነት ወይም የጸደቀ ውል)።
📍 የጥራት ምርመራ፦ በድርጅቱ ባለቤትነት የተደራጀ መሠረታዊ የቡና ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ።
📍 ቋሚ ንብረት፦ ከሚመለከተው ተቋም የተሰጠ ቋሚ ንብረት (የቤት ካርታ)።
📍 መልካም አፈጻጸም፦ ነባር ድርጅት ከሆነ የራሱን፣ አዲስ ከሆነ የባለቤቱን መልካም አፈጻጸም ምስክር ወረቀት።

4. አስፈላጊ የቅጥር ሰራተኞች

የቅጥር ውልና የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚገባቸው ባለሙያዎች፦
👥 ኤክስፖርት ሥራ አስኪያጅ፦ ዲፕሎማና ከዚያ በላይ።
👥 ሒሳብ ሠራተኛ፦ በአካውንቲንግ ዲፕሎማና ከዚያ በላይ።
👥 ፀሐፊ፦ በጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ዲፕሎማና ከዚያ በላይ።
👥 የቡና ጥራት ባለሙያ፦ የታደሰ የቡና ቀማሽነት ብቃት ማረጋገጫ ያለው።

⚠️ ማሳሰቢያ፦ አንድ የቡና ጥራት መርማሪ ለአንድ የቡና ላኪ ብቻ ነው ማገልገል የሚችለው።

🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment