-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

📜 የንግድ ፈቃድ ከመሰረዛችን በፊት
ሊታሰቡ የሚገቡ 18 ነጥቦች

1. ማንኛውም ነጋዴ የንግድ ሥራውን በማንኛውም ምክንያት የተወ እንደሆነ በ30 ተከታይ ቀናት ውስጥ እንዲሰረዝለት ማመልከት አለበት።
2. የግብር እና የታክስ ክሊራንስ፡ የንግድ ፈቃድ ለመሰረዝ ከፈለገ እስከ ተሰረዘበት ቀን ድረስ ያለውን ግብር መክፈልና ከገቢዎች መሥሪያ ቤት የክሊራንስ ደብዳቤ ማግኘት አለበት።
3. የሰራተኞች ስንብት እና ክፍያ፡ ሰራተኞች ካሉን በሥራ ሕጉ መሠረት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠት፣ ያልተጠቀሙበትን የዓመት ዕረፍት እና የሚገባቸውን የጥቅማጥቅም ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል።
4. የውል ግዴታዎችን ማጠናቀቅ፡ ከደንበኞች ወይም ከአቅራቢዎች ጋር የገባነው ውል ካለ ሥራውን ከማቆማቸን በፊት ውሉን ማቋረጥ ወይም ንግድ ፍቃዳችን እንዳለ ማጠናቅቀን ማስረከብ አለብን።
✍️ ስማችንን ከመጠበቅና ኃላፊነት ከመወጣት ጋር ስለሚገናኘ መጠንቀቅ አለብን። በተጨማሪም ወደፊት ሊመጣ የሚችልን የሕግ ክርክር ያስቀራል።
5. የባንክ ዕዳ እና ብድር፡ በንግድ ፍቃዳችን ሆነ በድርጅቱ ስም የተወሰደ የባንክ ወይም ከተለያዩ ፋይናንስ ተቋማት ብድር ካለ መከፈል ይኖረብናል።
6. የቤት ኪራይ ውል፡ በውሉ መሠረት ለባለቤቱ በወቅቱ ማሳወቅና ቦታውን በስምምነት ማስረከብ አለብን።
✍️ አስረክበን ባዶ አድርገን ገቢዎች መተወ መዘጋቱን ያረጋግጡልናል።
7. የማኅበራዊ ዋስትና (Pension) ክፍያ፡ የሰራተኞች የነበሩ ከሆነ የጡረታ መዋጮ ለሚመለከተው አካል ገቢ መደረጉንና ከጡረታ ፈንድ ክሊራንስ መያዝዎን ያረጋግጡ ይህ ካለተረጋገጥ ገቢዎች ክሪላስ አይሰጠንም።
8. ማህበር ከሆነ የጋዜጣ ማስታወቂያ፡ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ አበዳሪዎች ተቃውሞ እንዳላቀረቡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ። ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት "ይህ ማህበር እዳ አለበት፣ ሳይከፍለኝ መዘጋት የለበትም" ለንግድ ቢሮ አቤቱታ እንዲያቀርብ ዕድል ይሰጣል።
የመጨረሻ ውሳኔ፦ የ30 ቀኑ የጊዜ ገደብ ካለቀ በኋላ ማህበሩ በይፋ እንዲሰረዝ ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማመልከቻ ይቀርባል።
9. የንግድ ዕቃዎችን እና ንብረቶችን ማጣራት፡ የቀሩ የንግድ ዕቃዎች (Stock) ካሉ መሸጥ ወይም በሕጋዊ መንገድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል።
✍️ ስንዘጋ ፍቃዳችንን ሳንዘጋ ባለን ህጋዊ ደረሰኝ እቃችንን መሸጥ ተገቢወን ጥቅም እንድናገኝ ያደረጋል። ምክንያት በተዘጋ ንግድ ፍቃድ ምንም አይነት ግዥ እና ሽያጭ የለም።
10. የቫት (VAT) መዝገብ እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን፡ የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ማሽኑን (Cash Register) ለገቢዎች ማስረከብ ማጠናቀቅ ግዴታ ነው።
11. ኦዲት፡ የኦዲት ማደረግ ካለበል ለኦዲት ማዘጋጀት።
12. የባንክ አካውንት ዝውውር፡ የድርጅቱን ወይም ለንግድ ስንጠቀም የነበረውን የባንክ አካውንት መዝጋት። ✍️ ንግድ ፍቃድ ከዘጋን በኃላ አካውንቱን አለመጠቀም ጥሩ ነው።
13. ማስታወቂያ (ባነር)፡ በድርጅቱ ስም የተሰቀሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን ማውረድ ያስፈልጋል። ማስታወቂያ በካሬ ስለሚታሰብ ሳይነሳ ሲቀር ድጋሚ ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል።
14. የውጭ አገር ንግድ (Export/Import)፡ በብሔራዊ ባንክ በኩል መዘጋት ያለባቸውን ነገሮች ካሉን ማቋረጥ።
15. የቴሌኮም አገልግሎት፡ በግለሰብ ወይም በድርጅቱ ስም ያሉ ስልኮችን እና የኢንተርኔት መስመሮችን ካሉ መዝጋት።
16. የፍርድ ቤት ክርክሮች፡ በግለሰብ ወይም በድርጅቱ ላይ የቀረበ ወይም ድርጅቱ የመሰረተው ክስ ካለ በህግ ባለሙያ እንዲታይ ማደረግ።
17. የስረዛ ቃለ-ጉባኤ፡ ድርጅቱ PLC ከሆነ፣ ባለአክሲዮኖቹ ተስማምተው የፈረሙበትና በሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ የስረዛ ቃለ-ጉባኤ ያስፈልጋል።
18. ማህደርንና ሰነዶችን በጥንቃቄ መያዝ፡ የቆዩ የሂሳብ ሰነዶችንና ደረሰኞችን በጥንቃቄ ማስቀመጥ ይኖርብናል። እንደ ማስረጃ ይተቅመናል ለወደፊት ኦዲት ሊፈለጉ ይችላሉ።
📊 የሁሉም መጨረሻ የገቢዎች የመዝጊያ ክሪላንስ ይሆናል።

🔐 በስልክ ንግድ ፍቃድ እንዴት እንሰረዛለን?

1. ወደ ድህረ ገጹ ግቢ፦ etrade.gov.et ላይ እንገባለን።

2. Login የሚለውን፦ "Login" ወይም "ግባ" የሚል በተን እንነካለን።

3. Sign in፦ TIN ቁጥር እና የይለፍ ቃል እናስገባለን።

✍️ Password ከረሳን "Forgot password" በመንካት በTIN ቁጥርና በስልክ በሚላክ ኮድ መቀየር ይቻላል። (ከ 6 ቁምፊ ማነስ የለበትም)

4. የስረዛ አገልግሎት፦ "የንግድ ፈቃድ ስረዛ" (License Cancellation) የሚለውን እንነካለን።

5. ሰነዶችን ጫኑ (Upload)፦ ክሊራንስ፣ ቃለ-ጉባኤ እና ኦዲት ሪፖርት በግልጽ ፎቶ አንስተን እናስገባለን።

6. ክፍያ፦ የተጠየቀውን 52 ብር በትእዛዝ ቁጥሩ እንከፍላለን።

7. ሰርተፍኬት፦ "የስረዛ ምስክር ወረቀት" ሲላክልን አውርደን Print እናደርጋለን።

⚠️ ማሳሰቢያ
ንግድ ፍቃድ ካወጣቹ የማሰሩበት ከሆነ እቃ ማውጣት ብቻ ሳይሆን ንግድ ፍቃዳችሁን ሳታዘጉ አትተው። ✍️ የስረዛ Video እና መረጃዎችን በ Profile -> Heena Digital Market ማግኘት ይቻላል።
✍️ ማንኛውም በአዲስ ንግድ ፍቃድ፣በስረዛ፣በማሻሻል ፣በእድሳት ጥያቄ ወይም ችግር ካጋጠመዎት በetrade (የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር )በነፃ የጥሪ ማዕከል 8588 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። በተጨማሪ heena digital market አለን።
የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!! 😉😉😉
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment