የመኪና ባለቤትነት ስም ዝውውርለማድረግ ማሟላት ያለብን ነገሮች +
1. በሰነዶች የተረጋገጠ የሽያጭ ውል
2.የሻጭ እና የገዚ መታወቂያ
3.ሊብሬ
4. ከእዳ እገዳ ነፆ የሚገልፆ ደብዳቤ
5. የሻጭ የመሸጥ የመለወጥ መብት ስልጣን ህጋዊ ሰነድ(ውክልና)
5. የሻጭ የገባ-ያላገባ የገባ ከሆነ የትዳርአጋር የፍቃድ ስምምነት
6. የገዛችሁት ከማህበር ከሆነ የንግድ ምዝነባ መመስረቻ ፁሁፍ እና ቃለጉባኤ
7. 1-3 መኪናው ከቀረፆ ነፅ ከሆነ 10 ቢሞላውም ከግሙሩክ ከቀረፅ ነፆ ማስተላለፍ ደብዳብ ወይም ይህንን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠውን ማረጋገጫ ሰነድ
7. ከመንገድ ትራንስፖርት የሚሰጥ ወቅታዊ የመኪና ግምኝ
8 1-3 ከሆነ ከገቢዎየች የሚሰጥ የግብርክሪላስ (የታደሰ ንግድ ፍቃድ)
9. መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠውን የማረጋገጫ ሰነድ
የመኪና ስጦታ ውል ለመፈፀም በዉል አዋዋይ(ውልና ማስረጃ) ፊት ሲቀርቡ ሟሟላት ያለባቸዉ ሰነዶች +
1. የተዘጋጀ የስጦታ ውል ሰነድ፤
2. እዳ እና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፤
3. የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ ፤
4. የስጦታ አድራጊውና የስጦታ ተቀባይ የነዋሪነት መታወቂያ፤
5. ስጦታ አድራጊው እና ስጦታ ተቀባይ ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
6. ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
7. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
8. የስጦታ አድራጊው ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋርየፈቃድ ስምምነት፤
9. ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የዋጋ ግምት፤
10. ለኮድ 1 እና 3 ከገቢዎች እና ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ ክሊራንስ፤
የንግድ ቤት በሽያጭ ወይም በስጦታ የማስተላለፍ ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ +
የንግድ ቤት በሽያጭ ወይም በስጦታ የማስተላለፍ ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፡
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ መቅረቡን፤
3, የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ መቅረቡን፣
4. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘ ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፡ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልፅ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
8. ሻጭ ግለሰብ ከሆነ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. የሚተላለፈው ንብረት ነባሩ ካርታ ከሆነ የጀርባ ማህተም መመታቱን፣
10 የንግድ ሥራ በተከናወነበት ድርጅት ቤት ስም የወጣ የንግድ ፈቃድ እና የገቢዎች ክሊራንስ መቅረቡን
የማይንቀሳቀስ የጋራ ንብረትን ስለመከፋፈል+
የማይንቀሳቀስ የጋራ ንብረትን ስለመከፋፈል፡
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥርየያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ መቅረቡን፤
3. በጋራ የተመዘገብ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ (ካርታ) መቅረቡን፣
4. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘት ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልፅ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7.ንብረቱ እገዳ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዝገቢው አካል የተሰጠ ማስረጃ ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
8. የተዋዋይ ወገኖች ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳርአጋርየፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. የሚከፈለው የጋራ ንብረት ነባሩ ካርታ ከሆነ የጀርባ ማህተም መመታቱን፣
10. የሚከፈለው የጋራ ንብረት በሽያጭከሆነ የተጋሪው ቅድሚያ የመግዛት መብት መጠበቁን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ።
የውርስ መብት ድርሻ መልቀቅ ውል +
የውርስ መብት ድርሻ መልቀቅ ውል፡
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥርየያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ መቅረቡን፤
3. ከፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ ወይም በፍ/ቤት የጸደቀ የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ መቅረቡን፣
4. ውሉ የሚደረገው በወራሾች መካከል መሆኑን እና የሚለቀቀው የድርሻ መብት ሙሉ በሙሉ
5. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም በፍርድ ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤
6. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
5. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም በፍርድ ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤
6. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
7. ፈራሚው ሌላ ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የዋስትና ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፣ +
የዋስትና ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፣ ፡
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥርየያዘ መሆኑን፣
2. የዋስትና ውሉ የሚመሠረትበት የጸና መብትና ግዴታ የተቋቋመበት ውል መኖሩን፣
3. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ መቅረቡን፤
4. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን
5. ዋሱ የገባው የዋስትና ግዴታ የገንዘብ ልክ ወይም መጠን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑን፣
6. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን ፤
7. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃለፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
8. የተዋዋዮች ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋርየፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. ዋስትናው ንብረት በማስያዝ ከሆነ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ መቅረቡን፣
10. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዘጋቢው አካል ከተሰጠ ማስረጃ እና ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
የብድር ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ +
የብድር ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፡
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የአገልግሎት መስጫ ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይ መከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ መቅረቡን፤
3. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤
4. የብድር ስምምነቱ የውል ጊዜ ሰነዱ ሊረጋግጥ ከቀረበበት ቀን ወደኋላ የተደረገ አለመሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን ፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃለፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7. የተዋዋዮች ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋርየፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
8. የብድር ውሉ በመያዣ ከሆነ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ መቅረቡን፣
9. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዘጋቢው አካል ከተሰጠ ማስረጃ እና ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
10. መያዣው የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት ምስክሮች የቀረቡ መሆኑን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
የቤት ስም ዝውውርለማድረግ የሚያስፈለጉ ሰነዶች +
የቤት ስም ዝውውርለማድረግ የሚያስፈለጉ ሰነዶች፡
1.የሽያጭውል
2.ኦርጅናልካርታ
3.ውክልና ካለውክልና
4.የታደሰ የቀበሌ መታወቅያ
5.ፎቶግራፍ
6.ወራሾች ከሆኑ የፍርድ ቤት የውርስ ወረቀት
የመኪና ሽያጭ ውል ለመፈፀም +
የመኪና ሽያጭ ውል ለመፈፀም፡
1.በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ
2.የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፤
3.የሻጭና የገዥ መታወቂያ፤
4 ከእዳ እገዳ ነፆ መሆኑን የሚያገልፆ ደብደቤ
5. ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ፤
6 .ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ ቃለጉባኤ፤
7. የሻጭ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
8. ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፤
9. ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
10. ለኮድ 1 እና 3 አስር ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
11 . ለኮድ 5 11 እና 35 የመሳሰሉት ከሐይማኖት ተቋማት በስተቀርከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የማስተላለፍ የዕውቅና (የድጋፍ) ደብዳቤ፤
12. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ የምስከር ወረቀት የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ስራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
የመኖሪያ ቤት በሽያጭ ወይም በስጦታ የማስተላለፍ ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ +
የመኖሪያ ቤት በሽያጭ ወይም በስጦታ የማስተላለፍ ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፡
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ መቅረቡን፤
3, የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ መቅረቡን፣
4. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘ ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፡ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልፅ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
8. ሻጭ ግለሰብ ከሆነ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. የሚተላለፈው ንብረት ነባሩ ካርታ ከሆነ የጀርባ ማህተም መመታቱን፣
10. የሚተላለፈው የጋራ ንብረት በሽያጭከሆነ የተጋሪው ቅድሚያ የመግዛት መብት መጠበቁን፣
11. ንብረት ገዢው የውጭ ሃገር ዜጋ ከሆነ የታደሰ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ወይም ቢያንስ አሥር ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በሥራ ላይማዋሉን የሚገልጽ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን (ከሚመለከተው አካል) ማስረጃ እና የኢንቨስትመንት ፈቃድ መቅረቡን፣
12. ንብረት ገዢው የውጭ ሃገር ዜጋ ሌላ የመኖሪያ ቤት በስሙ የሌለ መሆኑን የሚገልጽ ከሚመለከተው የንብረት መዝጋቢ አካል ደብዳቤ መቅረቡን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ።
No comments:
Post a Comment