-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🚀 አዲስ ነጋዴዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ

የንግድ ፈቃድ ከማውጣታችን በፊት መታሰብ ያለባቸው 8 ነጥቦች

1. ግብር (Taxation)
ብዙዎች "ንግድ ፈቃድ ካወጣሁ ብዙ ብር እከፍላለሁ" ብለው ለመክፈት ይፈራሉ። ነገር ግን ግብር የምንከፍለው ከአገኘነው ትርፍ ላይ ነው። ስራ ከሌለን እንኮን ግብር የሱቅ ኪራይ መክፈል ከባድ ነው ብዙ ነገር ሲደራረብ ወደ መዝጋት እንሄዳለን።
✍️ ስለዚህ ስራ ስንጀምር አዋጪ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። የስራ ሱቅ ለመከራየት ወይም ንግድ ፍቃድ ለማውጣት መቸኮል የለብንም። ስራውን ብናውቀውና ልምድ ቢኖረን ከኪሳራ ይጠብቀናል።
✍️ በተጨማሪም የገቢዎች ቢሮ የጣለብዎት ግብር ቅሬታ ካለዎት በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ አልፎም እስከ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ድረስ በማመልከት እንዲቀነስ የማድረግ ህጋዊ መብት አለዎት።

🏙 ስራ ካለ ግብር መከፈል ቀላል ነው፤ ይህንን ስኬታማ ነጋዴዎች ይንገሯችሁ!

2. መረጃ (Information)
ከንግድ ቢሮ እና ከገቢዎች ቢሮ የሚወጡ መረጃዎችን ለማወቅ ዝግጁ መሆን አለብዎት። መቼ ንግድ ፈቃድ እንደሚታደስ፣ መቼ ግብር እንደሚከፈል እና መቼ ሪፖርት እንደሚደረግ ካላወቁ ያላስፈላጊ ቅጣት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። መረጃ ባለማወቅ ብቻ ከንግድ ውጪ ሊሆኑ ስለሚችሉ መብትና ግዴታዎን ይወቁ።
3. ህጋዊነት (Legality)
ህጋዊነት የነፃነት እና የእድገት መመሪያ ነው። ህጋዊ ነጋዴ ሲሆኑ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛሉ፦
✔️ ከባንክ ብድር መውሰድ ይችላሉ። ✔️ ከትልልቅ ኩባንያዎች ጋር ውል መፈራረም ይችላሉ። ✔️ ለንግድዎ ህጋዊ ጥበቃ ስላለዎት ያለ ስጋት በነፃነት መስራት ይችላሉ።
4. ደረሰኝ (Invoicing)
አዲስ ነጋዴዎች ስለ ደረሰኝ በቂ መረጃ ላይኖራቸው ይችላል። ደረሰኝ መቁረጥ ግዴታ በሆነባቸው ነጋዴዎች ላይ "ሽያጩ ትንሽ ናት" ብሎ ሳይቆርጡ መቅረት በኋላ ላይ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል። ስለዚህ በአግባቡ ደረሰኝ መቁረጥን መልመድ ይኖርብናል።
5. ተከታታይነት ያለው ክትትል
ንግድ አንድ ቀን ተከፍቶ የሚተው ሳይሆን የየቀኑ ክትትል የሚፈልግ ስራ ነው። የገበያ ሁኔታን ማጥናት፣ የደንበኞችን ፍላጎት መረዳት እና ህጋዊ አሰራሮችን መከተል ለዘላቂ ስኬት ወሳኝ ናቸው።
6. የሂሳብ መዝገብ አያያዝ
የሂሳብ መዝገብ መያዘ ግዴታ ያለባችሁ ማለትም ደረጃ 'ሀ' ነጋዴዎች የሂሳብ ባለሙያ መጠበቅ የለባችሁም። አሁን ላይ ብዙ አማራጮች አሉ፤ ለምሳሌ በዩቲዩብ (YouTube) ላይ የሚለቀቁ መረጃዎችን በመከታተል በቀላሉ የሂሳብ አያያዝን ማወቅና ስራችንን መቆጣጠር እንችላለን።
✍️ ስራውን ሳንጀምር በየቀኑ በራሳችን ሂሳብ አያያዝ ብናውቅ የተሻለ ነው። አውቀን ሰው ስንቀጥር ለመቆጣጠርና ስራውን ለመረከብ ቀላል ይሆንልናል።
7. የንግድ እና የግል ብርን መለየት
ብዙ አዳዲስ ነጋዴዎች የሚሳሳቱት የንግዱን ብር እና የራሳቸውን የግል ብር ባለመለየታቸው ነው። በንግዱ ስም የገባውን ብር ሁሉ እንደ ትርፍ ቆጥሮ ለግል ጉዳይ ማዋል ንግዱን ያከስራል። ስለዚህ ለራስዎ ደመወዝ በመቁረጥ የንግዱን ካፒታል ሳይነኩ መስራት ይለማመዱ።
8. የንግድ ዘርፍ ምርጫ
ፈቃድ ከማውጣታችሁ በፊት የምትሰሩበትን ዘርፍ በጥንቃቄ ምረጡ። በአንድ ፈቃድ ላይ ተያያዥ የሆኑ ስራዎችን መጨመር ለወደፊት ስራችሁን ለማስፋት ይረዳችኋል።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment