-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

የብቃት ማረጋገጫ የሚጠየቅባቸው 11 ዋና ዋና መደቦች 📜
እነዚህ መደቦች ከሰው፣ ከእንስሳትና ከዕፅዋት ጤንነት እንዲሁም ከሀገር ደህንነት አንጻር ጥንቃቄ የሚሹ በመሆናቸው የብቃት ማረጋገጫ ይጠየቅባቸዋል።
ዝርዝሩን ለማየት እዚህ ይጫኑ (ተጨማሪ ያንብቡ) 📖
1. የሥጋና የሥጋ ውጤቶች ማቀነባበርና መጠበቅ
2. የእንስሳት መኖ ማምረት
3. መሠረታዊ ኬሚካሎችን ማምረት
4. ለሰው አገልግሎት የሚውሉ የሕክምና መድኃኒቶችና ኬሚካሎች ማምረት
5. የዕፅዋት ዘር አስመጪነት
6. የምግብ ምርቶች አስመጪነት
7. ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎች አስመጪነት
8. የሰው መድኃኒት አስመጪነት
9. የሕክምና መገልገያዎች አስመጪነት
10. የሕክምና መሣሪያዎች አስመጪነት
11. የጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት
🛡️ ማረጋገጫ የሚሰጡ አካላት፦
📍 የግብርና ሚኒስቴር
📍 የኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለሥልጣን (EFDA)
📍 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

ለበለጠ መረጃና ለንግድ ፈቃድ አገልግሎት ድረ-ገጻችንን መከታተልዎን ይቀጥሉ! 💡

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓ.ም የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ መመሪያን በተመለከተ 

 1. ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የማህበራት ስራዎች መንግስት ስራቸው ከማህበራዊ ድጋፍ ጋር የተያያዘ እና ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቀጥታ ውል ያላቸው አካላት ከመንግስት መስሪያ ቤቱ ያገኙትን የክፍያ መረጃ በማቅረብ በሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት ግብር እንዲከፍሉ ተፈቅዶላቸዋል። እነዚህም፦ የትምህርት ቤት እና የምገባ ማዕከል መጋቢ እናቶች። የከተማ ጽዳትና ውበት (ደረቅ ቆሻሻ) ላይ የተሰማሩ። የሸገር ዳቦ ሽያጭ ማህበራት (ተጓዳኝ ንግድ ካላቸው ግን በቤት ለቤት ቅኝት ይገመገማሉ)።

 2. በሙያ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ (ጠበቆች እና ወኪሎች) የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ የሚሰሩ (ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች እና ጉዳት ገማቾች) ግብራቸው የሚሰላው በሚከተለው ቀመር ነው፦ የወጪ ተቀናሽ፦ ከጠቅላላ ገቢው 65% እንደ ወጪ ይያዛል። ግብር የሚከፈልበት ገቢ፦ ቀሪው 35% ላይ በሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት ግብር ይሰላል።

 3. የቤት እና የተሸከርካሪ ኪራይ የመኖሪያ ቤት አከራዮች፦ ልክ እንደ ሙያተኞቹ 65% ወጪ ተቀናሽ ተደርጎላቸው በ 35% ገቢያቸው ላይ ግብር ይከፍላሉ። የኪራይ ተሸከርካሪዎች (ኮድ 02 እና 03)፦ ባላቸው የኪራይ ገቢ መረጃ መሰረት በሰንጠረዥ "ሐ" ይሰላል። 

 4. የትራንስፖርት አገልግሎት (ታክሲዎች) የሜትር ታክሲዎችን ጨምሮ ደረሰኝ የመቁረጥ ግዴታ የሌለባቸው የከተማ ትራንስፖርት ሰጪዎች በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 ሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት ግብራቸው ተወስኖ እንዲሰበሰብ ተወስኗል።

 ማሳሰቢያ፦ ምንም እንኳን እነዚህ መመሪያዎች ለጊዜው በግምት (በቅጣት ጭምር) እንዲስተናገዱ ቢፈቅዱም፣ የገቢ ግብር ህጉ ለማንኛውም የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋይ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታን ቀሪ እንደማያደርግ ቢሮው አጽንኦት ሰጥቷል

ከ ንግድ ስራ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የግብር ምጣኔዎች ምን ይመስላሉ ? 


  የፌዴራል መንግሥት የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017  መሠረት፣ የግለሰቦች የንግድ ገቢ ግብር ስሌት ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወቃል።

 

በፍሪላንስ እና በዲጂታል ገቢ ላይ ግብር ሊጣል ነው!


 የገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ ረቂቅ ደንብ መሠረት፣ በዲጂታል አማካኝነት እና በፍሪላንስ (Freelance) ገቢ በሚያገኙ ግለሰቦች ላይ ግብር ሊጣል መሆኑን አስታውቋል። 


 📌 ዋና ዋና ነጥቦች፦ ግብር ከፋዮች፦ በማንኛውም የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ወይም በፍሪላንስ ሥራ ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦች ግብር የመክፈል ግዴታ ይኖርባቸዋል።


 የመዝገብ ግዴታ፦ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የተሟላ የሂሳብ መዝገብ መያዝ አለባቸው፤ ካልሆነ ግን ግብሩ "በግምት" ይወሰናል። 



 ክትትል፦ ክፍያ የሚያመቻቹ ኩባንያዎች የፈጣሪዎችን ስም፣ አድራሻ፣ ሲም ካርድ እና የአይፒ (IP) አድራሻ ለታክስ ባለሥልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።


 ከግብር ነፃ የሆኑ፦ ከመንግሥት ቦንዶች የሚገኝ ወለድ እና የአውሮፕላን ኪራይ (ሮያሊቲ) ክፍያዎች ከግብር ነፃ ተደርገዋል።

🚫 ከቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) ነፃ የሆኑ አካላት እና ሰነዶች ሁሉም ሰው የቴምብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ የለበትም። 


በሕጉ መሠረት የሚከተሉት አካላት እና ሁኔታዎች ከቀረጥ ነፃ ተደርገዋል፦


 🏢 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፦ በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከቴምብር ቀረጥ ነፃ ናቸው። 


 🚢 አስመጪ ነጋዴዎች፦ የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ ቀረጥ አይከፍሉም። 


 🌐 ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፦ መንግሥት ባጸደቃቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና ኮንቬንሽኖች መሠረት የሚዘጋጁ ሰነዶች ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ። 


 🌍 የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች፦ የገንዘብ ሚኒስቴር ተመሳሳይ መብት መኖሩን ሲያረጋግጥ፤ ኢምባሲዎችን፣ ቆንስላዎችን እና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችን ከቀረጥ ነፃ ሊያደርግ ይችላል።


በኢትዮጵያ የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) የመክፈል ግዴታ የማን ነው? 


የቴምብር ቀረጥ መክፈል በህግ የተጣለ ግዴታ ሲሆን፣ እንደ ውሉ አይነት ክፍያውን የሚፈጽመው አካል ይለያያል። ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ ዋና ዋናዎቹን ግዴታዎች እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦ 📋 ዋና ዋና የክፍያ ግዴታዎች፡ 



🏠 የቤት ወይም የንብረት ኪራይ ውል፦ በውሉ ላይ ሌላ ስምምነት ከሌለ በስተቀር፣ ቀረጡን የመክፈል ግዴታ የተከራይ ነው። 


 💼 የሥራ ቅጥር ውል፦ በቅጥር ውል ላይ የሚከፈለውን የቴምብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ የአሠሪው ነው።


 🚗 የባለቤትነት ስም ማዛወር፦ በንብረት ባለቤትነት ስም ማስመዝገቢያ ሰነድ ላይ (ለምሳሌ የመኪና ወይም የቤት ሽያጭ) ክፍያውን የሚፈጽመው ስሙ የሚመዘገብለት (ገዢው) አካል ነው። 


 🤝 በጋራ ስምምነቶች፦ ውል ወይም ስምምነት የሚመሰርቱ ወገኖች፣ ለቀረጡ አከፋፈል በጋራ እና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናሉ። 


 ⚖️ የግልግል ዳኝነት እና የሕብረት ስምምነት፦ ጉዳያቸውን በግልግል የሚያስወስኑ ወገኖች እንዲሁም አሠሪና ሠራተኞች ለቀረጡ አከፋፈል በጋራ ተጠያቂ ናቸው። 


 🌍 ሰነዱ የተፈጸመበት ቦታ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ፦ ሰነዱን የሚሠራው ወይም የሚሰጠው ሰው ሰነዱ እንደተፈጸመ መክፈል አለበት። 

 ከኢትዮጵያ ውጭ ከሆነ፦ ሰነዱን በኢትዮጵያ ውስጥ መጀመሪያ ያስፈጸመው ሰው ቀረጡን የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል። 


 ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም የሰነድ ተጠቃሚ ሰነዱ ላይ የተተመነውን የቴምብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት በህግ ተደንግጓል።


አዲስ የአፈጻጸም መመሪያ ስለ ስኳር እና አብሽ የታክስ ውሳኔ 


 1. ስኳር (ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ) ውሳኔ፦ የስኳር ምርት አሁንም ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ሆኖ ይቀጥላል።


 ምክንያት፦ በግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም የተላለፈው ውሳኔ በሥራ ላይ በመሆኑ፣ አዲሱ የጥቅምት 2018 ዓ.ም መመሪያ የታሪፍ ማሻሻያን ብቻ የሚመለከት እንጂ በስኳር ላይ ታክስ የሚጭን አይደለም። 


 2. አብሽ (VAT የሚከፈልበት) ውሳኔ፦ አብሽ ወደ አገር ውስጥ ሲገባም ሆነ በአገር ውስጥ ሲገበያይ 15% VAT ይከፈልበታል። ምክንያት፦ አብሽ በታሪፍ አመዳደብ መሠረት በ**"ቅመማ ቅመም"** ምድብ ውስጥ ስለሚመደብ፣ በደንብ ቁጥር570/2017 አባሪ ተራ ቁጥር 7 ከታክስ ነፃ ከተደረጉ እህሎችና ጥራጥሬዎች ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም።


 የጉምሩክ ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴርበተሰጠው ማብራሪያ መሠረት አዲስ የአፈጻጸም መመሪያ አስተላልፏል። የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ/ም





 📊 የንግድ ትርፍ ግብር ቅድመ ክፍያ (Advance Payment)


 "ሀ" ግብር ከፋዮች ላይ። -የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የንግድ ትርፍ ግብር ቅድመ ክፍያ (Advance Payment)። 

 የክፍያው መጠን፦ በ2017 የግብር ዓመት ከተከፈለው ጠቅላላ ግብር ውስጥ 25% (1/4) ያህሉን ቀድሞ መክፈል ግዴታ ነው። የጊዜ ገደብ፦


 ይህ ክፍያ ተጠናቆ መከፈል ያለበት እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው። 


 አከፋፈል፦ በኤሌክትሮኒክስ (Netax) ገጽ ላይ "Tax payer services" በሚለው ሜኑ ውስጥ "Advance Quarterly payment Advice-Schedule C" ተብሎ የተዘጋጀውን ተጠቅመው ማሳወቅና መክፈል ይቻላል።




ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የግብር ምጣኔዎች ምን ይመስላሉ ?

 የፌዴራል መንግሥት የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017
 መሠረት፣ የግለሰቦች የኪራይ ገቢ ግብር ስሌት ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወቃል።