-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🚗 የመኪና ቀብድ ውል ሲያደርጉ ማወቅ ያለብዎት 6 ነጥቦች

💡 መኪና ለመግዛት ተስማምተው የቀብድ ገንዘብ ከመክፈልዎ በፊት፣ ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ለመጠበቅ እና ሕጋዊ ዋስትና እንዲኖርዎት እነዚህን 6 ነጥቦች በጥንቃቄ መተግበር አለብዎት!

1. ውሉ በጽሁፍ መሆኑን ያረጋግጡ

በቃል የሚደረግ ስምምነትን ወደፊት ችግር ቢፈጠር በማስረጃነት ለማቅረብ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ የመኪና ቀብድ ስምምነት ውሉ በግልጽ በወረቀት ላይ ሰፍሮ፣ በሁለቱም ወገኖች እና በምስክሮች ፊት መፈረም አለበት።

2. የተሸከርካሪው ዝርዝር መረጃ

በውሉ ላይ ስለ መኪናው የሚከተሉት ነጥቦች በግልጽ ሊቀመጡ እና ሊሰፍሩ ይገባል፦
• የመኪናውን የሰሌዳ ቁጥር፣ የሻሲ (Chassis) ቁጥር እና የሞተር ቁጥር በአካል ከአይን ጋር ማመሳከር እና በትክክል ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ።
• የመኪናው ዓይነት፣ ሞዴል እና የተመረተበት የዘመን ማጠቃለያ።

3. የገንዘብ ክፍያ ዝርዝር

የቀብዱ መጠን፦ በአካል የተከፈለው የገንዘብ መጠን በዝርዝር በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለበት።
ቀሪ ክፍያ፦ ቀሪው ገንዘብ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እና እንዴት እንደሚከፈል በግልጽ ማስቀመጥ።
ደረሰኝ፦ ቀብዱን ሲከፍሉ የባንክ ማስተላለፊያ (Transfer) መጠቀም ወይም ሕጋዊ ደረሰኝ ወዲያውኑ መቀበል ለደህንነትዎ ይመከራል።

4. የጊዜ ገደብ እና ርክክብ

• ቀሪው ክፍያ ተከፍሎ መኪናው ለገዢው ሙሉ በሙሉ የሚረከብበት የመጨረሻ ቀን በውሉ ላይ መጠቀስ አለበት።
• በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያው ካልተፈጸመ ወይም ሻጭ መኪናውን በተባለው ቀን ካላስረከበ የሚወሰደው አስተዳደራዊ ወይም የገንዘብ ቅጣት እርምጃ (Penalty) መገለጽ አለበት።

5. የባለቤትነት እና ከዕዳ ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ

መኪናው ላይ የባንክ ዕዳ፣ የፍርድ ቤት እገዳ ወይም ያልተከፈለ የትራፊክ መቀጫ (እገዳ) አለመኖሩን ውል ከመፈረምዎ በፊት ከሚመለከተው አካል የሰነድ ማጣሪያ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።

6. መኪናው የንግድ ከሆነ ፈቃዱን ማረጋገጥ

መኪናው የንግድ ከሆነ፣ ሻጭ የንግድ ፈቃዱ የታደሰ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት። ፈቃዱ ባለመታደሱ ምክንያት ገዢ የስም ዝውውር ማድረግ ስለማይችል ገዢ ይህንን በጥንቃቄ ማየት አለበት። ፈቃዱን ለማረጋገጥ የሚከተለውን መንገድ መከተል ይችላሉ፦

📱 በዲጂታል መንገድ የማረጋገጫ ዘዴ፦

ወደ ድረ-ገጹ etrade.gov.et ላይ በመግባት የሻጩን የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በማስገባት የንግድ ፈቃዱን ሁኔታ (Status) እና የታደሰ መሆኑን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። ይህንን በማድረግ ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቃሉ።

✍️ ነፃ የመኪና ቀብድ ውል ሰነድ ይፈልጋሉ?

Profile Bio ላይ ያለውን የድር ጣቢያ ሊንክ በመንካት "የአገልግሎት ማውጫ" ውል ውስጥ ዝግጁ የሆነውን ነፃ ውል ወስደው መዋዋል ይችላሉ!

No comments:

Post a Comment