-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

☀️ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግዙፍ የሶላር እና የጋዝ ፋብሪካዎች ተመረቁ

📅 ሚያዚያ 2018 ዓ.ም

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተመረቁት እነዚህ ፋብሪካዎች፣ የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ናቸው።

የፋብሪካዎቹን ዝርዝር የማምረት አቅም እዚህ ያንብቡ 📖

🔋 የሶላር ፋብሪካዎች (ቶዮ ሶላር፣ ኦሪጂን እና ሉሚንቴክ)፦

  • በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው።

💨 የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ፦

በዓመት ለገበያ የሚያቀርባቸው ምርቶች፦

  • 900 ቶን ኦክስጅን
  • 40,000 ቶን ናይትሮጅን
  • 7 ቶን ሃይድሮጅን

"ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የኢነርጂ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የማይበገር ሁለንተናዊ እድገትን ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ነው" — የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

ለሀገራችን ብስራት የሆነውን መረጃ ሼር ያድርጉ! 🇪🇹

📢 ታላቅ ብስራት ለባለሀብቶች፡ በነፃ የንግድ ቀጠና የግብር ነፃ መብት ተፈቀደ

📅 ሚያዚያ 2018 ዓ.ም (የገቢዎች እና የገንዘብ ሚኒስቴር)

መንግስት የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን እና የግብዓት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በነፃ የንግድ ቀጠናዎች (Free Trade Zones) ውስጥ ለሚሳተፉ ባለሀብቶች ልዩ የታክስ ማበረታቻ ማድረጉን አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃውን እዚህ ያንብቡ 📖

ለምን አስፈለገ?

የካፒታል እጥረት እና የግብዓት አቅርቦት ችግር የኢንዱስትሪ እድገታችንን እንዳያደናቅፉት አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ በካፒታላቸው ላይ የሚያሳድረውን ጫና ማቃለል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

✅ ዋና ዋና ማበረታቻዎች፦

  • የግብር ነፃ መብት፦ በነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ ገብተው ዕቃዎችን ከውጭ በማስገባት ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች ከገቢ ግብር ነፃ እንዲሆኑ ተወስኗል።
  • ቀረጥን አዘግይቶ መክፈል፦ ምርቶችን ሳይከፍሉ አስገብተው፣ ለገበያ በሚያቀርቡበት ወቅት ብቻ ቀረጥና ታክስ የሚከፍሉበት አሰራር ተዘርግቷል።
  • የካፒታል እፎይታ፦ ይህ አሰራር ባለሀብቶች ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን ለስራ ማስፋፊያ እንዲጠቀሙበት ዕድል ይሰጣል።

የህግ መሠረት፦ ይህ ውሳኔ በገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ቁጥር ታ500/ሃ/883/18 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 586/2018 መሠረት ተፈጻሚ የሚሆን ይሆናል።

ባለሀብቶች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በነፃ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ ተጋብዘዋል!

መረጃው ለሌሎች ባለሀብቶች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

⚖️ የሙያ ፈቃድ ያላቸው ባለሙያዎች እና አከራዮች የግብር አከፋፈል

📍 አዲስ የአሰራር መመሪያ

የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እና የቤት አከራዮችን በሚመለከት የወጣው መመሪያ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል፦

ዝርዝር መረጃውን ያንብቡ 📖

🔹 ጠበቆች እና የኢንሹራንስ ወኪሎች፦ ከዓመታዊ ገቢያቸው 35% እንደ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎላቸው፣ በቀረው 65% ላይ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብር ይከፍላሉ።

🔹 የመኖሪያ ቤት አከራዮች፦ የንግድ ሥራ ያልሆነ ገቢ ያላቸው አከራዮችም 35% እንደ ወጪ ተይዞላቸው፣ በቀረው 65% ገቢ ላይ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብር ይሰበሰባል።

🔹 የተሽከርካሪ ኪራይ (ኮድ 02 እና 03)፦ በተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችም አጠቃላይ የኪራይ ገቢያቸው በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ተሰልቶ ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል።

🔹 የከተማ ትራንስፖርት (ሜትር ታክሲዎችን ጨምሮ)፦ በህግ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ የሌለባቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብራቸው ተሰልቶ እንዲሰበሰብ ተወስኗል።

💡 ማስታወሻ፦

እነዚህ የግብር አከፋፈል ስሌቶች ለተከፋዮች ምቹ በሆነ መልኩ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት የሚከናወኑ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።

መረጃው ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📞 የታክስ እና የጉምሩክ ነፃ የጥሪ መስመር (8199)

📅 መጋቢት 05/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በታክስ እና በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ግብር ከፋዮች በሙሉ የተዘረጋ ነፃ የጥሪ መስመር መኖሩን ያውቃሉ?

ስለ አገልግሎቱ ዝርዝር መረጃ 📖

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ እና በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ የተሟላ ማብራሪያ ለመስጠት በ 8199 ነፃ የጥሪ መስመር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በዚህ መስመር ምን አይነት መረጃ ያገኛሉ?

  • 👉 ስለ አዳዲስ የታክስ አዋጆች ማብራሪያ
  • 👉 ስለ ጉምሩክ ስነ-ስርዓት ጥያቄዎች
  • 👉 ያጋጠሙዎትን የአሰራር ቅሬታዎች ለማቅረብ

የጥሪ ማዕከል፦ 8199

(ዘወትር በስራ ሰዓት ይደውሉ)

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🚗 የተሽከርካሪዎች ዓመታዊ ግብርና የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ)

📍 ማወቅ ያለብን ዋና ዋና ነጥቦች

ተሽከርካሪ ያላቸው ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ) ለማድረግ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ አለባቸው፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖

የታክስ ክሊራንስ፦ ለተሽከርካሪ ዓመታዊ ምዝገባና ምርመራ (ቦሎ) ለማድረግ የታክስ ከፋዩን ሂሳብ ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ ክሊራንስ ይሰጣል።

የክፍያ ጊዜ፦ የተሽከርካሪ ዓመታዊ ግብር የሚከፈለው እንደ ሰሌዳው ቁጥር መጨረሻ ሆኖ፣ በየዓመቱ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መሆን አለበት።

አስፈላጊ ሰነዶች፦
• የታደሰ የንግድ ፈቃድ (ለንግድ ተሽከርካሪዎች)
• የሊብሬ ኮፒ
• የኢንሹራንስ (መድን) ዋስትና ሰነድ

ቅጣት፦ የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ ለሚከፈል ግብር እንደየ መዘግየቱ መጠን አስተዳደራዊ ቅጣቶችና ወለድ ሊታሰብ ይችላል።

💡 ጠቃሚ ምክር፦

የቦሎ ጊዜዎ ከመድረሱ በፊት የታክስ ክሊራንስዎን በ eTax ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የገቢዎች ቅርንጫፍ በማውጣት እንግልትን ይቀንሱ።

መረጃው ለተሽከርካሪ ባለቤቶች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📊 በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት የገቢ ግብር ምጣኔ

📍 ሠንጠረዥ "መ" - ለሌሎች ገቢዎች የሚከፈል የታክስ መጠን

በአዲሱ የታክስ ማሻሻያ መሠረት ለተለያዩ የገቢ አይነቶች የተወሰነው የግብር ምጣኔ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖
የገቢ ዓይነት ነዋሪ ለሆኑ ነዋሪ ላልሆኑ
ለመድን አረቦን - 15%
ሮያሊቲ (Royalty) 10% 10%
በትርፍ ክፍፍል (Dividend) 15% 15%
በወለድ ገቢ 10% 10%
በስራ አመራር እና ቴክኒክ አገልግሎት 15% 15%
ከመዝናኛ አገልግሎት 15% -
የዕድል ሙከራ (ሎተሪ) 25% -
ሀብት በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም - 15%

💡 ማስታወሻ፦

ይህ ሰንጠረዥ በዋናነት ነዋሪ ለሆኑ እና ላልሆኑ ግብር ከፋዮች የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ ያሳያል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📜 የቴምብር ቀረጥ አከፋፈል መመሪያ

📅 የካቲት 30/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው የቴምብር ቀረጥ ስሌት እና ተመን ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ሙሉ የክፍያ ዝርዝሩን ይመልከቱ 📖
የሰነዱ ዓይነት የክፍያ ልክ
የመመስረቻ ጽሁፍ (አዲስ) ብር 350
የመመስረቻ ጽሁፍ (ማሻሻያ) ብር 100
ውል (Contract) ብር 5.00
የባለቤትነት ስም ማዛወር 2%
የኪራይ ውል 0.5%
የውክልና ስልጣን ብር 35.00
የቅጥር ውል 1% (ከአንድ ወር ደመወዝ)

💡 ማሳሰቢያ፦

ሌሎች ዝርዝር ሰነዶች እንደ ዋጋቸው (Ad Valorem) 1% ወይም እንደ ብዛታቸው (Fixed) ተሰልተው የሚከፈሉ ይሆናል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📢 ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች፦ የትርፍ ግብር ቅድመ ክፍያ (Advance Payment)

📍 የ2018 በጀት ዓመት መረጃ

የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የንግድ ትርፍ ግብር ቅድመ ክፍያን በተመለከተ ማወቅ ያለብን 8 ወሳኝ ነጥቦች፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖

1. የሂሳብ መዝገብ፦ መዝገብ ማቅረብ አያስፈልግም። የምንከፍለው በ2017 ዓ.ም ከከፈልነው ግብር 25% (1/4) ብቻ ነው።

2. አዲስ ነጋዴዎች፦ በ2018 ዓ.ም ስራ የጀመሩትን አይመለከትም

3. የ3% ግብር (Withholding)፦ በመስከረም ወር የተቀነሰባችሁ የ3% ግብር ከሚጠበቅባችሁ 25% በላይ ከሆነ፣ ትርፉ ወደ ቀጣዩ ሩብ ዓመት ይዞርላችኋል።

4. የቅድመ ክፍያው መጨረሻ፦ በየሩብ ዓመቱ የከፈላችሁት ድምር በ2019 ዓ.ም ከሚከፈለው ጠቅላላ ግብር ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።

5. የክፍያ ጊዜ፦ ከመጀመሪያው ሩብ ዓመት ጀምሮ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ተከፍሎ ማለቅ አለበት።

6. ተቀናሽ የሚሆን Withholding፦ ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የተቀነሰባችሁ 3% ብቻ ተቀናሽ ይሆናል።

7. "0" (ዜሮ) ሪፖርት ላደረጋችሁ፦ ባለፈው ዓመት ዜሮ ላሳወቃችሁ፣ በግምት ከዓመታዊ ገቢያችሁ 2.5% እንድትከፍሉ ይደረጋል።

8. የክፍያ መንገድ (eTax)፦ በ "Taxpayer Services" ሜኑ ውስጥ "Advance Quarterly Payment Advice - Schedule C" የሚለውን በመጫን ኦንላይን ማሳወቅ ይቻላል።

⚠️ ማሳሰቢያ፦

ግብርን በወቅቱ በማሳወቅና በመክፈል ካልተፈላጊ ቅጣትና ወለድ ራስዎን ይጠብቁ።

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📋 የታክስ ክሊራንስ ለመስጠት ኦዲት የማያስፈልጋቸው አገልግሎቶች

📅 ጥር 03/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሠረት፣ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ታክስ ከፋዩን ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ የታክስ ክሊራንስ ሊሰጥ ይችላል፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖
  • 👉 የንግድ ሥራ ወይም የሙያ ፈቃድ ለማደስ፤
  • 👉 በጨረታ ለመካፈል ወይም ለመሳተፍ፤
  • 👉 ለተሽከርካሪዎች ወይም ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ዓመታዊ ምርመራ (ቦሎ) ለማድረግ፤
  • 👉 የባንክ ብድር ለማግኘት፤
  • 👉 የመድን ካሳ ለማግኘትና የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ፤
  • 👉 የድርጅት ስም ወይም አድራሻ ለመለወጥ፤
  • 👉 የንግድ ዘርፍ ቅነሳ ለማድረግ (የንግድ ሀብት መቀነስን ሳይጨምር)፤
  • 👉 ድርጅቶች ሲዋሀዱ የታክስ ዕዳን አካቶ ለመቀጠል ለሚቀርብ የፀደቀ ሰነድ፤
  • 👉 የጡረታ መዋጮ ስለመከፈሉ ማረጋገጫ ለማግኘት።

💡 ማስታወሻ፦

እነዚህ አገልግሎቶች የታክስ ከፋዩን ጊዜና ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ።

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡