-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

⚠️ ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ለታክስ ከፋዮች የቀረበ ማሳሰቢያ

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ የሚከተሉት የገንዘብ ቅጣቶች ይጣሉበታል፦

የቅጣቱን ዝርዝር መመሪያ እዚህ ያንብቡ 📖

ሀ) ለመጀመሪያው ወር፦

ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ) ቅጣት ይከፈላል።

ለ) ለቀጣይ ወራት፦

ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ) ቅጣት ይታሰባል።

📌 ዋና ዋና ደንቦች፦

  • 👉 የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም።
  • 👉 መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል።
  • 👉 ይህ ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ በሚጣል ቅጣት ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።

ታክስን በጊዜ በመክፈል ከትርፍ ወጪ ራስዎን ይጠብቁ!

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🧾 የግዥ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Purchase Voucher) አጠቃቀም

ለግብር ከፋዮች የቀረበ ጠቃሚ መረጃ

የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ታክስ ከፋይ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ከሌለባቸው ታክስ ከፋዮች ጋር ለሚያደርገው ግብይት ከታክስ ባለስልጣኑ በማስፈቀድ የወጭ ማስረጃ የግዥ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Purchase Voucher) አሳትሞ መጠቀም ይችላል።

ስለ Purchase Voucher ዝርዝር መረጃ እዚህ ያንብቡ 📖

Purchase Voucher (የግዥ ማረጋገጫ ደረሰኝ) ምንድነው?

"ገዥው ራሱ አዘጋጅቶ ሽያጭን የሚያስፈርምበት ደረሰኝ" ማለት ነው። ሻጩ ደረሰኝ የሌለው ግለሰብ ሲሆን፣ ገዥው ድርጅት ያወጣውን ወጪ ለታክስ ባለሥልጣን ለማስረዳት ይጠቀምበታል።

1. ለምን ያገለግላል?

  • 👉 ለወጪ ማረጋገጫ፦ ወጪው በኦዲት ጊዜ ተቀባይነት እንዲኖረውና ከገቢ ላይ ተቀንሶ ትክክለኛው ግብር እንዲታሰብ ይረዳል።
  • 👉 ለሕጋዊነት፦ ደረሰኝ ከማይሰጡ ሰዎች ጋር የተደረገን ግብይት ሕጋዊ መልክ ያስይዛል።

2. በደረሰኙ ላይ ምን መያዝ አለበት?

  • የሻጩ ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና TIN (ካለው)
  • የተገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር
  • የግብይቱ ጠቅላላ ዋጋ እና የተፈጸመበት ቀን
  • የሻጩ ፊርማ (በጣም ወሳኝ ነው)

3. የት ይታተማል?

ከገቢዎች ባለሥልጣን ፈቃድ በማግኘት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አሳትሞ መጠቀም ይቻላል።

✅ መጠቀም የተፈቀደላቸው ዋና ዋና ግዢዎች፦

  • ከገበሬዎች የሚገዛ እንስሳ፣ እህል፣ አትክልትና ፍራፍሬ
  • ለኮንስትራክሽን የሚሆኑ ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ኖራና እንጨት
  • በሰው ጉልበት የሚሰራ የጫኝና አውራጅ አገልግሎት
  • ያገለገሉ/የወዳደቁ ዕቃዎች ግዢ
  • ተሸከርካሪ ኪራይ እና ለማገዶ የሚሆን ከሰልና እንጨት

መረጃው ለነጋዴው ማህበረሰብ እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📜 የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሕትመት መመሪያ

አሳትሞ የሕትመት አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገቡ ቅደመ ሁኔታዎች

ማንኛውንም የሕትመት ሥራ (በተለይም ደረሰኞችንና ሕጋዊ ሰነዶችን) ለማሳተም የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ግዴታ ነው፦

ሙሉውን ዝርዝር መመሪያ እዚህ ያንብቡ 📖

1. ሕጋዊ ሰነዶች (Legal Requirements)

  • • የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ።
  • • ልዩ ፈቃድ ለሚፈልጉ ሕትመቶች (ለምሳሌ፦ ደረሰኝ) ከሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት የተሰጠ የፈቃድ ደብዳቤ ማያያዝ።

2. የመረጃ ትክክለኛነት (Accuracy)

  • • ሊታተም የሚፈለገው መረጃ (ጽሑፍ፣ ዲዛይን፣ ፎቶ) ትክክል መሆኑን ደንበኛው በፊርማው ማረጋገጥ ይኖርበታል።
  • • መረጃው በሶፍት ኮፒ (በፍላሽ ወይም በሲዲ) በጥራት ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት።

3. ክፍያና ስምምነት (Payment & Contract)

• እንደ ሥራው ዓይነት የቅድሚያ ክፍያ መፈጸም ወይም በድርጅቶች መካከል የሚደረግ የውል ስምምነት (የእምነት ደብዳቤ) መፈረም ያስፈልጋል።

4. የናሙና ማረጋገጫ (Sample Approval)

• ሕትመቱ ከመጀመሩ በፊት የሚቀርበውን ናሙና (Proof) አይቶ ማጽደቅ የደንበኛው ኃላፊነት ነው። ናሙናውን ለማጽደቅ የሚወሰደው ጊዜ በሥራው ማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ እንደማይታሰብ መገንዘብ ያስፈልጋል።

5. ርክክብ (Delivery)

• ሥራው ተጠናቆ ሲገለጽ በወቅቱ መረከብና ቀሪ ክፍያዎችን መክፈል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

☀️ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግዙፍ የሶላር እና የጋዝ ፋብሪካዎች ተመረቁ

📅 ሚያዚያ 2018 ዓ.ም

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተመረቁት እነዚህ ፋብሪካዎች፣ የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ናቸው።

የፋብሪካዎቹን ዝርዝር የማምረት አቅም እዚህ ያንብቡ 📖

🔋 የሶላር ፋብሪካዎች (ቶዮ ሶላር፣ ኦሪጂን እና ሉሚንቴክ)፦

  • በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው።

💨 የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ፦

በዓመት ለገበያ የሚያቀርባቸው ምርቶች፦

  • 900 ቶን ኦክስጅን
  • 40,000 ቶን ናይትሮጅን
  • 7 ቶን ሃይድሮጅን

"ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የኢነርጂ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የማይበገር ሁለንተናዊ እድገትን ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ነው" — የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

ለሀገራችን ብስራት የሆነውን መረጃ ሼር ያድርጉ! 🇪🇹

📢 ታላቅ ብስራት ለባለሀብቶች፡ በነፃ የንግድ ቀጠና የግብር ነፃ መብት ተፈቀደ

📅 ሚያዚያ 2018 ዓ.ም (የገቢዎች እና የገንዘብ ሚኒስቴር)

መንግስት የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን እና የግብዓት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በነፃ የንግድ ቀጠናዎች (Free Trade Zones) ውስጥ ለሚሳተፉ ባለሀብቶች ልዩ የታክስ ማበረታቻ ማድረጉን አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃውን እዚህ ያንብቡ 📖

ለምን አስፈለገ?

የካፒታል እጥረት እና የግብዓት አቅርቦት ችግር የኢንዱስትሪ እድገታችንን እንዳያደናቅፉት አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ በካፒታላቸው ላይ የሚያሳድረውን ጫና ማቃለል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

✅ ዋና ዋና ማበረታቻዎች፦

  • የግብር ነፃ መብት፦ በነፃ የንግድ ቀጠና ውስጥ ገብተው ዕቃዎችን ከውጭ በማስገባት ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች ከገቢ ግብር ነፃ እንዲሆኑ ተወስኗል።
  • ቀረጥን አዘግይቶ መክፈል፦ ምርቶችን ሳይከፍሉ አስገብተው፣ ለገበያ በሚያቀርቡበት ወቅት ብቻ ቀረጥና ታክስ የሚከፍሉበት አሰራር ተዘርግቷል።
  • የካፒታል እፎይታ፦ ይህ አሰራር ባለሀብቶች ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን ለስራ ማስፋፊያ እንዲጠቀሙበት ዕድል ይሰጣል።

የህግ መሠረት፦ ይህ ውሳኔ በገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ቁጥር ታ500/ሃ/883/18 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 586/2018 መሠረት ተፈጻሚ የሚሆን ይሆናል።

ባለሀብቶች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በነፃ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ ተጋብዘዋል!

መረጃው ለሌሎች ባለሀብቶች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

⚖️ የሙያ ፈቃድ ያላቸው ባለሙያዎች እና አከራዮች የግብር አከፋፈል

📍 አዲስ የአሰራር መመሪያ

የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እና የቤት አከራዮችን በሚመለከት የወጣው መመሪያ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል፦

ዝርዝር መረጃውን ያንብቡ 📖

🔹 ጠበቆች እና የኢንሹራንስ ወኪሎች፦ ከዓመታዊ ገቢያቸው 35% እንደ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎላቸው፣ በቀረው 65% ላይ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብር ይከፍላሉ።

🔹 የመኖሪያ ቤት አከራዮች፦ የንግድ ሥራ ያልሆነ ገቢ ያላቸው አከራዮችም 35% እንደ ወጪ ተይዞላቸው፣ በቀረው 65% ገቢ ላይ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብር ይሰበሰባል።

🔹 የተሽከርካሪ ኪራይ (ኮድ 02 እና 03)፦ በተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችም አጠቃላይ የኪራይ ገቢያቸው በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ተሰልቶ ግብር እንዲከፍሉ ይደረጋል።

🔹 የከተማ ትራንስፖርት (ሜትር ታክሲዎችን ጨምሮ)፦ በህግ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ የሌለባቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብራቸው ተሰልቶ እንዲሰበሰብ ተወስኗል።

💡 ማስታወሻ፦

እነዚህ የግብር አከፋፈል ስሌቶች ለተከፋዮች ምቹ በሆነ መልኩ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት የሚከናወኑ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።

መረጃው ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📞 የታክስ እና የጉምሩክ ነፃ የጥሪ መስመር (8199)

📅 መጋቢት 05/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በታክስ እና በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ግብር ከፋዮች በሙሉ የተዘረጋ ነፃ የጥሪ መስመር መኖሩን ያውቃሉ?

ስለ አገልግሎቱ ዝርዝር መረጃ 📖

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ እና በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ የተሟላ ማብራሪያ ለመስጠት በ 8199 ነፃ የጥሪ መስመር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በዚህ መስመር ምን አይነት መረጃ ያገኛሉ?

  • 👉 ስለ አዳዲስ የታክስ አዋጆች ማብራሪያ
  • 👉 ስለ ጉምሩክ ስነ-ስርዓት ጥያቄዎች
  • 👉 ያጋጠሙዎትን የአሰራር ቅሬታዎች ለማቅረብ

የጥሪ ማዕከል፦ 8199

(ዘወትር በስራ ሰዓት ይደውሉ)

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🚗 የተሽከርካሪዎች ዓመታዊ ግብርና የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ)

📍 ማወቅ ያለብን ዋና ዋና ነጥቦች

ተሽከርካሪ ያላቸው ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ) ለማድረግ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ አለባቸው፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖

የታክስ ክሊራንስ፦ ለተሽከርካሪ ዓመታዊ ምዝገባና ምርመራ (ቦሎ) ለማድረግ የታክስ ከፋዩን ሂሳብ ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ ክሊራንስ ይሰጣል።

የክፍያ ጊዜ፦ የተሽከርካሪ ዓመታዊ ግብር የሚከፈለው እንደ ሰሌዳው ቁጥር መጨረሻ ሆኖ፣ በየዓመቱ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መሆን አለበት።

አስፈላጊ ሰነዶች፦
• የታደሰ የንግድ ፈቃድ (ለንግድ ተሽከርካሪዎች)
• የሊብሬ ኮፒ
• የኢንሹራንስ (መድን) ዋስትና ሰነድ

ቅጣት፦ የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ ለሚከፈል ግብር እንደየ መዘግየቱ መጠን አስተዳደራዊ ቅጣቶችና ወለድ ሊታሰብ ይችላል።

💡 ጠቃሚ ምክር፦

የቦሎ ጊዜዎ ከመድረሱ በፊት የታክስ ክሊራንስዎን በ eTax ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የገቢዎች ቅርንጫፍ በማውጣት እንግልትን ይቀንሱ።

መረጃው ለተሽከርካሪ ባለቤቶች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📊 በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት የገቢ ግብር ምጣኔ

📍 ሠንጠረዥ "መ" - ለሌሎች ገቢዎች የሚከፈል የታክስ መጠን

በአዲሱ የታክስ ማሻሻያ መሠረት ለተለያዩ የገቢ አይነቶች የተወሰነው የግብር ምጣኔ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖
የገቢ ዓይነት ነዋሪ ለሆኑ ነዋሪ ላልሆኑ
ለመድን አረቦን - 15%
ሮያሊቲ (Royalty) 10% 10%
በትርፍ ክፍፍል (Dividend) 15% 15%
በወለድ ገቢ 10% 10%
በስራ አመራር እና ቴክኒክ አገልግሎት 15% 15%
ከመዝናኛ አገልግሎት 15% -
የዕድል ሙከራ (ሎተሪ) 25% -
ሀብት በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም - 15%

💡 ማስታወሻ፦

ይህ ሰንጠረዥ በዋናነት ነዋሪ ለሆኑ እና ላልሆኑ ግብር ከፋዮች የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ ያሳያል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡