-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 ንግድ ፍቃድ በስልክ ለማደስ

ንግድ ፍቃድ በስልክ ለማደስ

🏢 ንግድ ፍቃድ ለመሰረዝ

ንግድ ፍቃድ ስረዛ

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 ለ ደረጃ ለ'' የግብር ስሌት

የንግድ ገቢ ግብር ለደረጃ ለ ስሌት

🏢 ሀ ደረጃ ለ'' የግብር ስሌት

የንግድ ገቢ ግብር ለደረጃ ሀ ስሌት

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓ.ም የግብር አወሳሰንና አሰባሰብ መመሪያን በተመለከተ 

 1. ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የማህበራት ስራዎች መንግስት ስራቸው ከማህበራዊ ድጋፍ ጋር የተያያዘ እና ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቀጥታ ውል ያላቸው አካላት ከመንግስት መስሪያ ቤቱ ያገኙትን የክፍያ መረጃ በማቅረብ በሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት ግብር እንዲከፍሉ ተፈቅዶላቸዋል። እነዚህም፦ የትምህርት ቤት እና የምገባ ማዕከል መጋቢ እናቶች። የከተማ ጽዳትና ውበት (ደረቅ ቆሻሻ) ላይ የተሰማሩ። የሸገር ዳቦ ሽያጭ ማህበራት (ተጓዳኝ ንግድ ካላቸው ግን በቤት ለቤት ቅኝት ይገመገማሉ)።

 2. በሙያ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ (ጠበቆች እና ወኪሎች) የንግድ ስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ የሚሰሩ (ጠበቆች፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች እና ጉዳት ገማቾች) ግብራቸው የሚሰላው በሚከተለው ቀመር ነው፦ የወጪ ተቀናሽ፦ ከጠቅላላ ገቢው 65% እንደ ወጪ ይያዛል። ግብር የሚከፈልበት ገቢ፦ ቀሪው 35% ላይ በሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት ግብር ይሰላል።

 3. የቤት እና የተሸከርካሪ ኪራይ የመኖሪያ ቤት አከራዮች፦ ልክ እንደ ሙያተኞቹ 65% ወጪ ተቀናሽ ተደርጎላቸው በ 35% ገቢያቸው ላይ ግብር ይከፍላሉ። የኪራይ ተሸከርካሪዎች (ኮድ 02 እና 03)፦ ባላቸው የኪራይ ገቢ መረጃ መሰረት በሰንጠረዥ "ሐ" ይሰላል። 

 4. የትራንስፖርት አገልግሎት (ታክሲዎች) የሜትር ታክሲዎችን ጨምሮ ደረሰኝ የመቁረጥ ግዴታ የሌለባቸው የከተማ ትራንስፖርት ሰጪዎች በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 ሰንጠረዥ "ሐ" መሰረት ግብራቸው ተወስኖ እንዲሰበሰብ ተወስኗል።

 ማሳሰቢያ፦ ምንም እንኳን እነዚህ መመሪያዎች ለጊዜው በግምት (በቅጣት ጭምር) እንዲስተናገዱ ቢፈቅዱም፣ የገቢ ግብር ህጉ ለማንኛውም የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋይ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታን ቀሪ እንደማያደርግ ቢሮው አጽንኦት ሰጥቷል

No comments:

Post a Comment