-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

በኢትዮጵያ የቴምብር ቀረጥ (Stamp Duty) የመክፈል ግዴታ የማን ነው? 


የቴምብር ቀረጥ መክፈል በህግ የተጣለ ግዴታ ሲሆን፣ እንደ ውሉ አይነት ክፍያውን የሚፈጽመው አካል ይለያያል። ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ ዋና ዋናዎቹን ግዴታዎች እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦ 📋 ዋና ዋና የክፍያ ግዴታዎች፡ 



🏠 የቤት ወይም የንብረት ኪራይ ውል፦ በውሉ ላይ ሌላ ስምምነት ከሌለ በስተቀር፣ ቀረጡን የመክፈል ግዴታ የተከራይ ነው። 


 💼 የሥራ ቅጥር ውል፦ በቅጥር ውል ላይ የሚከፈለውን የቴምብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ የአሠሪው ነው።


 🚗 የባለቤትነት ስም ማዛወር፦ በንብረት ባለቤትነት ስም ማስመዝገቢያ ሰነድ ላይ (ለምሳሌ የመኪና ወይም የቤት ሽያጭ) ክፍያውን የሚፈጽመው ስሙ የሚመዘገብለት (ገዢው) አካል ነው። 


 🤝 በጋራ ስምምነቶች፦ ውል ወይም ስምምነት የሚመሰርቱ ወገኖች፣ ለቀረጡ አከፋፈል በጋራ እና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናሉ። 


 ⚖️ የግልግል ዳኝነት እና የሕብረት ስምምነት፦ ጉዳያቸውን በግልግል የሚያስወስኑ ወገኖች እንዲሁም አሠሪና ሠራተኞች ለቀረጡ አከፋፈል በጋራ ተጠያቂ ናቸው። 


 🌍 ሰነዱ የተፈጸመበት ቦታ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ፦ ሰነዱን የሚሠራው ወይም የሚሰጠው ሰው ሰነዱ እንደተፈጸመ መክፈል አለበት። 

 ከኢትዮጵያ ውጭ ከሆነ፦ ሰነዱን በኢትዮጵያ ውስጥ መጀመሪያ ያስፈጸመው ሰው ቀረጡን የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል። 


 ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም የሰነድ ተጠቃሚ ሰነዱ ላይ የተተመነውን የቴምብር ቀረጥ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት በህግ ተደንግጓል።


No comments:

Post a Comment