-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

የዊዝሆልዲንግ ታክስ አሰላል

📊 የ3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ አሰላል ደንብ

ተቀናሽ የሚደረገው 3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ በቪኤቲ (VAT) ላይ ይታሰባልን?

ተቀናሽ የሚደረገው ሦስት በመቶ ዊዝሆልዲንግ ታክስ የሚሰላበት የእቃ ወይም የአገልግሎት የክፍያ መጠን የተጨማሪ እሴት ታክሱን ይጨምራል ወይስ አይጨምርም? እንዴት ነው የሚሰላው?

ዝርዝር መመሪያውንና ምሳሌውን እዚህ ያንብቡ 📖

⚠️ ዋናው ደንብ፦

አይጨመርም! 3% የዊዝሆልዲንግ ታክስ (Withholding Tax) የሚሰላው የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ሳይጨምር በዕቃው ወይም በአገልግሎቱ ዋና ዋጋ ላይ ብቻ ነው።

የክፍያ ሰነድ (ኢንቮይስ) መሠረታዊ ክፍሎች፦

  • 🔹 የዕቃው ወይም አገልግሎቱ ዋና ዋጋ፦ ይህ 3% ዊዝሆልዲንግ ታክስ የሚሰላበት መነሻ ሂሳብ ነው።
  • 🔹 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፦ በዋናው ዋጋ ላይ ብቻ ተሰልቶ የሚቀመጥ።
  • 🔹 የሁለቱ ድምር፦ ጠቅላላ የኢንቮይስ ዋጋ።

🧮 ተግባራዊ ምሳሌ፦

አንድ ድርጅት የብር 10,000 ዕቃ ወይም አገልግሎት ቢገዛ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ቢሆን፦

• የዕቃው/አገልግሎቱ ዋና ዋጋ፦ ብር 10,000

• ተጨማሪ እሴት ታክስ (15% VAT)፦ ብር 1,500

• ጠቅላላ የክፍያ ሰነድ (ኢንቮይስ) ድምር፦ ብር 11,500


📌 የዊዝሆልዲንግ ታክስ አሰላል፦
3% ዊዝሆልዲንግ የሚሰላው በዋናው ዋጋ (ብር 10,000) ላይ ብቻ ስለሆነ፦
Withholding Tax = 10,000 × 3% = ብር 300


💰 ለአቅራቢው የሚከፈለው ጠቅላላ የተጣራ ሂሳብ፦
ስለዚህ ዊዝሆልዲንግ ታክስ በሚቀነስበት ጊዜ የቪኤቲ (VAT) ሂሳቡ መደመር የለበትም። ክፍያ ፈጻሚው አካል ለባለአገልግሎቱ/ለአቅራቢው የሚከፍለው ጠቅላላ ሂሳብ፡
ጠቅላላ ድምር (ብር 11,500) - ዊዝሆልዲንግ ታክስ (ብር 300) = ብር 11,200 ይሆናል ማለት ነው።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🚫 ያለ አስመጪነት ንግድ ፈቃድ ዕቃ ማምጣት ይቻላል?

ስለ ግል መገልገያና የንግድ ዕቃዎች ግልጽ መረጃ

ብዙዎች ዕቃዎችን ያለ አስመጪነት ንግድ ፈቃድ ለአንድ ጊዜ ብቻ ማምጣት እንደሚቻል ያስባሉ፤ ነገር ግን ሕጉ የሚለው የሚከተለውን ነው፦

ዝርዝር መመሪያውን እዚህ ያንብቡ 📖

⚠️ ዋናው ደንብ፦

ያለ ንግድ ፈቃድ ማንኛውንም ዕቃ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት አይቻልም

ከዚህ ደንብ ውጭ የሚስተናገዱ (ልዩ ሁኔታዎች)፦

  • 🔹 የንግድ ባህሪ የሌላቸው ዕቃዎች፦ በስጦታ መልክ የሚላኩ ዕቃዎች።
  • 🔹 ለመንገደኞች፦ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚገቡ የግል መገልገያዎች።
  • 🔹 ለተመላሽ ኢትዮጵያውያን፦ በገንዘብ ሚኒስቴር የግል መገልገያ መመሪያ ዝርዝር ላይ የተቀመጡ ዕቃዎች።

ማጠቃለያ፦ በመመሪያው ላይ ከሰፈሩት "የግል መገልገያ" ዕቃዎች ውጭ ማንኛውም አይነት ዕቃ ለማስገባት የአስመጪ የንግድ ፈቃድ መኖሩ ግዴታ ነው!

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

💰 የዕቃዎች ቀረጥና ታክስ አወሳሰን (CIF Value)

ዕቃዎች ወደ ሀገር ሲገቡ ቀረጥ እንዴት ይሰላል?

የዕቃዎች ቀረጥና ታክስ የሚወሰነው በዕቃው አጠቃላይ የCIF ዋጋ እና በዕቃው የታሪፍ ምጣኔ ላይ ተመስርቶ ነው፡:

የCIF ዝርዝር እና አሰላስል እዚህ ያንብቡ 📖

CIF ማለት ምን ማለት ነው?

CIF (Cost, Insurance, and Freight) ማለት የሚከተሉት ወጪዎች ድምር ውጤት ነው፦

  • 🔹 C (Cost)፦ የዕቃው መግዣ ዋጋ።
  • 🔹 I (Insurance)፦ የኢንሹራንስ ወይም የመድን ዋስትና ወጪ።
  • 🔹 F (Freight)፦ የማጓጓዣ ወይም የጭነት ዋጋ።
  • 🔹 ሌሎች ወጪዎች፦ ከዕቃው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች።

ቀመር (Formula)

CIF = የመግዣ ዋጋ + ኢንሹራንስ + ማጓጓዣ

ቀረጥ የሚወሰንባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

  • 👉 የታሪፍ ምጣኔ፦ እንደ ዕቃው ዓይነት (ለምሳሌ የቤት ዕቃ፣ የኢንዱስትሪ መሣሪያ፣ አልባሳት) የሚቀመጥ የመቶኛ ስሌት ነው።
  • 👉 የምንዛሬ ተመን፦ ስሌቱ የሚሠራው ዕቃው ጉምሩክ በደረሰበት ቀን ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ወደ ብር ተቀይሮ ነው።

ማስታወሻ፦ ትክክለኛውን የCIF ዋጋ ማሳወቅ ከቅጣት ነፃ ያደርጋል፤ የጉምሩክ ሂደቱንም ያፋጥነዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ብሎጋችንን ይከታተሉ! 💡

🚢 ለአስመጪና ላኪዎች፦ ለጉምሩክ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች

የጉምሩክ ስነ-ስርዓትን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መረጃዎች

በፅሁፍ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የእቃ ዲክላራሲዮን ለጉምሩክ ሲቀርብ የሚከተሉት ሰነዶች ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፦

የሰነዶቹን ዝርዝር እዚህ ያንብቡ 📖
  • የታደሰ የንግድ ፍቃድ፦ በዘመኑ የታደሰና ለስራው ብቁ መሆኑን የሚያረጋግጥ።
  • የማጓጓዣ ሰነዶች (Shipping Documents)፦ ዕቃው የተጫነበትን መንገድና ሁኔታ የሚያሳዩ።
  • የዋጋና የዕቃ ዝርዝር መግለጫ (Invoice & Packing List)፦ የዕቃው አይነት፣ ብዛትና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር የያዘ።
  • የባንክ ፍቃድ (Bank Permit)፦ ከባንክ የተገኘ የክፍያ ወይም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ።
  • የስሪት ሀገር ማረጋገጫ (Certificate of Origin)፦ ዕቃው የት ሀገር እንደተመረተ የሚያሳይ ምስክር ወረቀት።
  • ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች፦ በመመሪያ የሚወሰኑና እንደ ዕቃው አይነት የሚጠየቁ ተጨማሪ ሰነዶች።

💡 ማሳሰቢያ፦

እነዚህ ሰነዶች ተሟልተው መቅረባቸው የጉምሩክ ሂደቱን ፈጣን ከማድረጉም በላይ አላስፈላጊ መዘግየቶችን ያስቀራል።

መረጃው ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

⚖️ ታክስን አሳንሶ ማሳወቅ የሚያስከትለው ቅጣት

መረጃው ለታክስ ከፋዮች ሁሉ ይድረስ!

በታክስ ማስታወቂያ የተገለጸው የታክስ መጠን ታክስ ከፋዩ ሊከፍል ከሚገባው ትክክለኛ የታክስ መጠን ያነሰ ሆኖ ከተገኘ (የታክስ ጉድለት) የሚከተሉት ቅጣቶች ይጣላሉ፦

የቅጣቱን ደረጃዎች እዚህ ያንብቡ 📖

1. ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት፦

በታክስ ጉድለቱ መጠን ላይ 10% (አሥር በመቶ) ቅጣት ይከፈላል።

2. ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት፦

ጥፋቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሲደገም የቅጣቱ መጠን ወደ 30% (ሰላሳ በመቶ) ከፍ ይላል።

3. ለሦስተኛ ጊዜ እና ከዚያ በላይ፦

ጥፋቱ ለሦስተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ሲደገም የቅጣቱ መጠን ወደ 40% (አርባ በመቶ) ከፍ ይላል።

📢 ማወቅ ያለብዎት ተጨማሪ ነጥቦች፦

  • 👉 ምክንያታዊ አቋም፦ ጉድለቱ የተፈጠረው ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ባልሰጠበት አከራካሪ ሕግ ላይ በተወሰደ ምክንያታዊ አቋም ከሆነ ቅጣቱ ተፈጻሚ አይሆንም።
  • 👉 የጥፋት ብዛት አቆጣጠር፦ የጥፋቱ መጠን የሚቆጠረው አዋጁ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለየታክስ ዓይነቱ ተለይቶ እና ጥፋት በተገኘባቸው የታክስ ማስታወቂያዎች ብዛት ነው።

ትክክለኛ መረጃን በማቅረብ ከከባድ የገንዘብ ቅጣት ይዳኑ!

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

አክሲዮን ትርፍ ድርሻ (Dividend) የታክስ መመሪያ

አንድ ትርፍ ያገኘ ድርጀት ሁለት መርጫ አለው ካፒታል ማሳደግ ወይም የትርፍ ድርሻ ግብር መክፈል


1. የግብር መጠን፦

ማንኛውም የትርፍ ድርሻ ያገኘ ሰው (ነዋሪም ሆነ ነዋሪ ያልሆነ) በገቢው ላይ 15% የገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት።

2. ግብሩ መቼ መከፈል አለበት?

የትርፍ ድርሻ ግብር የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ 14 ወራት ውስጥ መከፈል አለበት።

3. ካፒታል ማሳደግ (ታክስ ላለመክፈል)፦

ትርፉን ለባለቤቱ ከመስጠት ይልቅ ካፒታል ለማሳደግ ከተፈለገ፣ ዓመቱ ባለቀ በ 12 ወራት ውስጥ ካፒታሉ ማደግ አለበት።

ካፒታል አደገ የሚባለው፦ በውልና ማስረጃ የጸደቀ ቃለ-ጉባኤ ሲኖር፣ በ e-trade ካፒታሉ ሲሻሻል እና ሰነዶቹ ለገቢዎች ቀርበው ከፋይሉ ጋር ሲያያዙ ነው።

4. በጊዜው ካልተከፈለ የሚመጣ ቅጣት፦

ትርፉ ሳይከፈል ወይም ካፒታል ሳይሳደግ ቢቀር የፍሬ ግብር፣ የወለድ እና የአስተዳደር መቀጫ ይጣልባቸዋል።


ድርጅቱ የትርፍ ድርሻ መከፈል የሚጠበቅበት ትርፍ ካገኘ ብቻ ነው
ታክስ ከመወሰኑ በፊት ከታወቀ፦ የ 10,000 ብር መቀጫ ብቻ።

ታክስ ከተወሰነ በኋላ ከሆነ፦ ከፍሬ ግብሩ በተጨማሪ ከ 5% እስከ 25% የሚደርስ ቅጣት ይጣልበታል።

⚠️ ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ለታክስ ከፋዮች የቀረበ ማሳሰቢያ

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ የሚከተሉት የገንዘብ ቅጣቶች ይጣሉበታል፦

የቅጣቱን ዝርዝር መመሪያ እዚህ ያንብቡ 📖

ሀ) ለመጀመሪያው ወር፦

ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ) ቅጣት ይከፈላል።

ለ) ለቀጣይ ወራት፦

ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ) ቅጣት ይታሰባል።

📌 ዋና ዋና ደንቦች፦

  • 👉 የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም።
  • 👉 መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል።
  • 👉 ይህ ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ በሚጣል ቅጣት ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።

ታክስን በጊዜ በመክፈል ከትርፍ ወጪ ራስዎን ይጠብቁ!

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🧾 የግዥ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Purchase Voucher) አጠቃቀም

ለግብር ከፋዮች የቀረበ ጠቃሚ መረጃ

የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ታክስ ከፋይ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ከሌለባቸው ታክስ ከፋዮች ጋር ለሚያደርገው ግብይት ከታክስ ባለስልጣኑ በማስፈቀድ የወጭ ማስረጃ የግዥ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Purchase Voucher) አሳትሞ መጠቀም ይችላል።

ስለ Purchase Voucher ዝርዝር መረጃ እዚህ ያንብቡ 📖

Purchase Voucher (የግዥ ማረጋገጫ ደረሰኝ) ምንድነው?

"ገዥው ራሱ አዘጋጅቶ ሽያጭን የሚያስፈርምበት ደረሰኝ" ማለት ነው። ሻጩ ደረሰኝ የሌለው ግለሰብ ሲሆን፣ ገዥው ድርጅት ያወጣውን ወጪ ለታክስ ባለሥልጣን ለማስረዳት ይጠቀምበታል።

1. ለምን ያገለግላል?

  • 👉 ለወጪ ማረጋገጫ፦ ወጪው በኦዲት ጊዜ ተቀባይነት እንዲኖረውና ከገቢ ላይ ተቀንሶ ትክክለኛው ግብር እንዲታሰብ ይረዳል።
  • 👉 ለሕጋዊነት፦ ደረሰኝ ከማይሰጡ ሰዎች ጋር የተደረገን ግብይት ሕጋዊ መልክ ያስይዛል።

2. በደረሰኙ ላይ ምን መያዝ አለበት?

  • የሻጩ ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና TIN (ካለው)
  • የተገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር
  • የግብይቱ ጠቅላላ ዋጋ እና የተፈጸመበት ቀን
  • የሻጩ ፊርማ (በጣም ወሳኝ ነው)

3. የት ይታተማል?

ከገቢዎች ባለሥልጣን ፈቃድ በማግኘት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አሳትሞ መጠቀም ይቻላል።

✅ መጠቀም የተፈቀደላቸው ዋና ዋና ግዢዎች፦

  • ከገበሬዎች የሚገዛ እንስሳ፣ እህል፣ አትክልትና ፍራፍሬ
  • ለኮንስትራክሽን የሚሆኑ ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ኖራና እንጨት
  • በሰው ጉልበት የሚሰራ የጫኝና አውራጅ አገልግሎት
  • ያገለገሉ/የወዳደቁ ዕቃዎች ግዢ
  • ተሸከርካሪ ኪራይ እና ለማገዶ የሚሆን ከሰልና እንጨት

መረጃው ለነጋዴው ማህበረሰብ እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📜 የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሕትመት መመሪያ

አሳትሞ የሕትመት አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገቡ ቅደመ ሁኔታዎች

ማንኛውንም የሕትመት ሥራ (በተለይም ደረሰኞችንና ሕጋዊ ሰነዶችን) ለማሳተም የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ግዴታ ነው፦

ሙሉውን ዝርዝር መመሪያ እዚህ ያንብቡ 📖

1. ሕጋዊ ሰነዶች (Legal Requirements)

  • • የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ።
  • • ልዩ ፈቃድ ለሚፈልጉ ሕትመቶች (ለምሳሌ፦ ደረሰኝ) ከሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት የተሰጠ የፈቃድ ደብዳቤ ማያያዝ።

2. የመረጃ ትክክለኛነት (Accuracy)

  • • ሊታተም የሚፈለገው መረጃ (ጽሑፍ፣ ዲዛይን፣ ፎቶ) ትክክል መሆኑን ደንበኛው በፊርማው ማረጋገጥ ይኖርበታል።
  • • መረጃው በሶፍት ኮፒ (በፍላሽ ወይም በሲዲ) በጥራት ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት።

3. ክፍያና ስምምነት (Payment & Contract)

• እንደ ሥራው ዓይነት የቅድሚያ ክፍያ መፈጸም ወይም በድርጅቶች መካከል የሚደረግ የውል ስምምነት (የእምነት ደብዳቤ) መፈረም ያስፈልጋል።

4. የናሙና ማረጋገጫ (Sample Approval)

• ሕትመቱ ከመጀመሩ በፊት የሚቀርበውን ናሙና (Proof) አይቶ ማጽደቅ የደንበኛው ኃላፊነት ነው። ናሙናውን ለማጽደቅ የሚወሰደው ጊዜ በሥራው ማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ እንደማይታሰብ መገንዘብ ያስፈልጋል።

5. ርክክብ (Delivery)

• ሥራው ተጠናቆ ሲገለጽ በወቅቱ መረከብና ቀሪ ክፍያዎችን መክፈል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡