-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

📊 በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት የገቢ ግብር ምጣኔ

📍 ሠንጠረዥ "መ" - ለሌሎች ገቢዎች የሚከፈል የታክስ መጠን

በአዲሱ የታክስ ማሻሻያ መሠረት ለተለያዩ የገቢ አይነቶች የተወሰነው የግብር ምጣኔ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖
የገቢ ዓይነት ነዋሪ ለሆኑ ነዋሪ ላልሆኑ
ለመድን አረቦን - 15%
ሮያሊቲ (Royalty) 10% 10%
በትርፍ ክፍፍል (Dividend) 15% 15%
በወለድ ገቢ 10% 10%
በስራ አመራር እና ቴክኒክ አገልግሎት 15% 15%
ከመዝናኛ አገልግሎት 15% -
የዕድል ሙከራ (ሎተሪ) 25% -
ሀብት በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም - 15%

💡 ማስታወሻ፦

ይህ ሰንጠረዥ በዋናነት ነዋሪ ለሆኑ እና ላልሆኑ ግብር ከፋዮች የሚኖረውን ልዩነት በግልጽ ያሳያል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📜 የቴምብር ቀረጥ አከፋፈል መመሪያ

📅 የካቲት 30/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው የቴምብር ቀረጥ ስሌት እና ተመን ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ሙሉ የክፍያ ዝርዝሩን ይመልከቱ 📖
የሰነዱ ዓይነት የክፍያ ልክ
የመመስረቻ ጽሁፍ (አዲስ) ብር 350
የመመስረቻ ጽሁፍ (ማሻሻያ) ብር 100
ውል (Contract) ብር 5.00
የባለቤትነት ስም ማዛወር 2%
የኪራይ ውል 0.5%
የውክልና ስልጣን ብር 35.00
የቅጥር ውል 1% (ከአንድ ወር ደመወዝ)

💡 ማሳሰቢያ፦

ሌሎች ዝርዝር ሰነዶች እንደ ዋጋቸው (Ad Valorem) 1% ወይም እንደ ብዛታቸው (Fixed) ተሰልተው የሚከፈሉ ይሆናል።

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📢 ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች፦ የትርፍ ግብር ቅድመ ክፍያ (Advance Payment)

📍 የ2018 በጀት ዓመት መረጃ

የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የንግድ ትርፍ ግብር ቅድመ ክፍያን በተመለከተ ማወቅ ያለብን 8 ወሳኝ ነጥቦች፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖

1. የሂሳብ መዝገብ፦ መዝገብ ማቅረብ አያስፈልግም። የምንከፍለው በ2017 ዓ.ም ከከፈልነው ግብር 25% (1/4) ብቻ ነው።

2. አዲስ ነጋዴዎች፦ በ2018 ዓ.ም ስራ የጀመሩትን አይመለከትም

3. የ3% ግብር (Withholding)፦ በመስከረም ወር የተቀነሰባችሁ የ3% ግብር ከሚጠበቅባችሁ 25% በላይ ከሆነ፣ ትርፉ ወደ ቀጣዩ ሩብ ዓመት ይዞርላችኋል።

4. የቅድመ ክፍያው መጨረሻ፦ በየሩብ ዓመቱ የከፈላችሁት ድምር በ2019 ዓ.ም ከሚከፈለው ጠቅላላ ግብር ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።

5. የክፍያ ጊዜ፦ ከመጀመሪያው ሩብ ዓመት ጀምሮ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ተከፍሎ ማለቅ አለበት።

6. ተቀናሽ የሚሆን Withholding፦ ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የተቀነሰባችሁ 3% ብቻ ተቀናሽ ይሆናል።

7. "0" (ዜሮ) ሪፖርት ላደረጋችሁ፦ ባለፈው ዓመት ዜሮ ላሳወቃችሁ፣ በግምት ከዓመታዊ ገቢያችሁ 2.5% እንድትከፍሉ ይደረጋል።

8. የክፍያ መንገድ (eTax)፦ በ "Taxpayer Services" ሜኑ ውስጥ "Advance Quarterly Payment Advice - Schedule C" የሚለውን በመጫን ኦንላይን ማሳወቅ ይቻላል።

⚠️ ማሳሰቢያ፦

ግብርን በወቅቱ በማሳወቅና በመክፈል ካልተፈላጊ ቅጣትና ወለድ ራስዎን ይጠብቁ።

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📋 የታክስ ክሊራንስ ለመስጠት ኦዲት የማያስፈልጋቸው አገልግሎቶች

📅 ጥር 03/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሠረት፣ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ታክስ ከፋዩን ኦዲት ማድረግ ሳያስፈልግ የታክስ ክሊራንስ ሊሰጥ ይችላል፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖
  • 👉 የንግድ ሥራ ወይም የሙያ ፈቃድ ለማደስ፤
  • 👉 በጨረታ ለመካፈል ወይም ለመሳተፍ፤
  • 👉 ለተሽከርካሪዎች ወይም ለኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ዓመታዊ ምርመራ (ቦሎ) ለማድረግ፤
  • 👉 የባንክ ብድር ለማግኘት፤
  • 👉 የመድን ካሳ ለማግኘትና የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ፤
  • 👉 የድርጅት ስም ወይም አድራሻ ለመለወጥ፤
  • 👉 የንግድ ዘርፍ ቅነሳ ለማድረግ (የንግድ ሀብት መቀነስን ሳይጨምር)፤
  • 👉 ድርጅቶች ሲዋሀዱ የታክስ ዕዳን አካቶ ለመቀጠል ለሚቀርብ የፀደቀ ሰነድ፤
  • 👉 የጡረታ መዋጮ ስለመከፈሉ ማረጋገጫ ለማግኘት።

💡 ማስታወሻ፦

እነዚህ አገልግሎቶች የታክስ ከፋዩን ጊዜና ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ።

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

⚖️ ከታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ጋር የተገናኙ ወንጀሎች

📍 የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008

የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም በህግ ያስቀጣል፦

  • ከአንድ በላይ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር መውሰድ ወይም ለመውሰድ መሞከር።
  • የራስን መለያ ቁጥር (TIN) ሌላ ሰው እንዲጠቀምበት መስጠት።
  • የሌላን ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር መጠቀም።

⚠️ ቅጣቱ፦

💰 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር የገንዘብ ቅጣት እና

⛓️ ከ 1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ያስቀጣል።

ተጨማሪ ያንብቡ 📖

🔹 ስለ ብዛቱ፦ ከአንድ በላይ ቁጥር ለመውሰድ ከተሞከረ፣ ቅጣቱ ለእያንዳንዱ ቁጥር በተናጠል ተፈጻሚ ይሆናል።

🔹 ልዩ ሁኔታ፦ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩ ባለቤት ለታክስ ወኪሉ (Tax Agent) በጽሁፍ ፈቅዶ ወኪሉ ለባለቤቱ ጉዳይ ብቻ ከተጠቀመበት ቅጣቱ ተፈጻሚ አይሆንም።

ምንጭ፦ በበኃይሉ ሺመልስ | መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📅 የ2018 ዓ.ም የቅድመ ግብር ክፍያ የጊዜ ሰሌዳ

በአዲሱ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሠረት፣ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸውን በየሦስት ወሩ 25% አስቀድመው መክፈል ይኖርባቸዋል።

📍 የሂሳብ ሪፖርት እስከ ጥቅምት 30 የሚያቀርቡ (ደረጃ "ሀ")

የክፍያ ዙር የመክፈያ ጊዜ
1ኛ ዙር (ሕዳር - ጥር) የካቲት 1 – 30
2ኛ ዙር (የካቲት - ሚያዝያ) ግንቦት 1 – 30
3ኛ ዙር (ግንቦት - ሐምሌ) ነሐሴ 1 – 30
መጨረሻ (ቀሪው ክፍያ) እስከ ጥቅምት 30
ተጨማሪ ያንብቡ 📖

ተመላሽ መጠየቅ፦ ቅድሚያ የከፈሉት ግብር ከዓመታዊ ግብሩ ከበለጠ ተመላሽ መጠየቅ ይቻላል። ካነሰ ግን ልዩነቱን ይከፍላሉ።

ሌላ የጊዜ አቆጣጠር፦ በሌላ የጊዜ አቆጣጠር ሪፖርት የሚያቀርቡም፣ ሪፖርት ካቀረቡበት ወር ማግስት ጀምሮ በየሦስት ወሩ መክፈል ይኖርባቸዋል።

⚠️ ማሳሰቢያ፦ መነሻው ባለፈው ዓመት (2017 ዓ.ም) የከፈሉት ግብር መጠን ነው።

መረጃው ለሁሉም ግብር ከፋዮች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

📄 የወጪ ማስረጃ ውድቅ ሲደረግ ተቀናሽ ስለሚደረግ ወጪ

አንድ የወጪ ደረሰኝ በቴክኒክ ስህተት ምክንያት ውድቅ ቢደረግም፣ የተወሰኑ መስፈርቶች ከተሟሉ ወጪው ሙሉ በሙሉ አይጣልም፦

ተጨማሪ ያንብቡ 📖

1. የሚፈቀድበት መስፈርቶች፦

• ወጪው ለድርጅቱ ገቢ ለማስገኘት የወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ።

• ለድርጅቱ መደበኛ ስራ የግድ አስፈላጊ ሲሆን።

• ያ ወጪ ባይወጣ ኖሮ ድርጅቱ ስራውን መቀጠል የማይችል ሲሆን።

2. የሚፈቀደው ተቀናሽ መጠን፦

✅ ለቋሚ ንብረት — 70%

✅ ለሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች — 65%

3. 0% የሚሆንበት (ውድቅ የሚደረግበት)፦

❌ ለግል ጥቅም የዋለ ወጪ፦ ከድርጅቱ ስራ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የባለቤቱ ወይም የሰራተኛው የግል ወጪ ከሆነ።

❌ የሀሰት ደረሰኝ (Fictitious/Illegal Receipt)፦ ምንም አይነት እቃ ሳይገዛ ወይም አገልግሎት ሳይገኝ፣ በገንዘብ ተገዝቶ የመጣ ደረሰኝ መሆኑ ከተረጋገጠ።

❌ህገ-ወጥ ሰነድ፦ በንግድ ሚኒስቴር እውቅና በሌለው፣ የንግድ ፈቃዱ በተሰረዘ ወይም በሌለ ድርጅት ስም የተቆረጠ ደረሰኝ።

መረጃው ለንግድ ማህበረሰቡ እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! 💡

🔋 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ አገልግሎት የክፍያ ተመን ይፋ ሆነ

የኃይል መሙያ ጣቢያዎች ግንባታ

የተጠናቀቁ፦ ሳሊተ ምህረት፣ ፒያሳ ኤሌክትሪክ ህንፃ እና የተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል ውስጥ የሚገኙ 3 ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

በቅርብ የሚጠናቀቁ፦ በአዲስ አበባ ውስጥ በተመረጡ 18 ቦታዎች ላይ የግንባታ ሥራቸው በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል።

የረጅም ጊዜ ዕቅድ፦ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ 2,300 ፈጣን የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ታቅዷል።

💰 አዲሱ የክፍያ ተመን (በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት - kWh)

የክፍያ ተመኑ በሰዓት ልዩነት ላይ የተመሠረተ መሆኑ የኃይል ፍላጎትን ለማመጣጠን ታስቦ የተዘጋጀ ነው፦

➡️ ከሰዓት በኋላ (ከምሽቱ 4:00 - ጠዋቱ 12:00) — 14.85 ብር

➡️ በቀን (ከጠዋቱ 4:00 - ከቀኑ 11:00) — 16.57 ብር

➡️ የኃይል ፍላጎት በሚበዛበት (Peak hours) — 18.28 ብር

🚀 የቀጣይ ጉዞ

ወደ ክልል ከተሞች፦ በሁለተኛው ምዕራፍ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ ባቱ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሀዋሳ ከተሞች የጣቢያዎቹ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ለባለሀብቶች፦ መንግስት መሬት በነፃ ወይም በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፤ ይህ ትልቅ ዕድል ነው።

ለተጠቃሚዎች፦ አገልግሎቱን በዝቅተኛ ዋጋ ለማግኘት የሰዓት ልዩነቱን መከታተል ይመከራል።

ኢንጅነር ጌቱ ገረመው (20/07/2018 ዓ.ም)

 

ከ ንግድ ስራ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የግብር ምጣኔዎች ምን ይመስላሉ ? 
  የፌዴራል መንግሥት የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017  መሠረት፣ የግለሰቦች የንግድ ገቢ ግብር ስሌት ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወቃል።