✅ፋይዳ፡
✅የቤት ኪራይ ውል
✅የአመልካች መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ፡
✅የአመልካቹ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች፡
✅አመልካቹ የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ የኢንቨስትመንት ፍቃድ፡
✅የሚሰማራበት ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ከሆነ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት፡
✅etrade.gov.et ላይ ተመዝግቦ ምዝገባ እና ፍቃድ ማውጣህ፡
✅ከንግድ ሚኒስቴር የሥም ስያሜ፡
✅የፀደቀ መመስረቻና፡
✅ቲን፡
✅የሥራ አስኪያጅ 6 ወር ወዲህ የተነሳዉ 2 ጉርድ ፎቶ፡
✅የሥራአስኪያጅ ፡
የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፡
✅የአባላት/የባለአክሲዮኖች ፋይዳ ቁጥርእና የግል ቲን ቁጥር ለሁሉም አባላት፡
✅ባለ አንድ አባል ኃላ/የተ/የግ/ማ ተመዝጋቢዎች የግል ንግድ ከነበሮት ዕዳ እንደሌለብዎት ከ ኢአ ገቢዎች ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይኖርቦታል፡፡፡
✅የዉጭ አገር ዜጋ ከሆነ የሥራ ፈቃድ/workpermit/፡
✅አመልካች ወኪል ከሆነ ዉክልናዉ በድርጅቱ በማህበሩ ስም ሆኖ በሰነዶች የፀደቀ፡
✅ለሀይማኖት ተቋማት ኤምባሲ NGO፡
አግባብ ካለዉ የመንግስት አካል የተሰጠ የምዝገባ ወረቀት(ስርተፊኬት) ኮፒ፡
✅መተዳደሪያ ደንብ ኦርጅናል እና ኮፒ፡
✅የቢሮ ኪራይ ዉል እና ውልና ማስረጃ የከፈሉበት ደረሰኝ ዋናውንና ኮፒ፡
ተቋሙን የሚወክለዉ ስዉ (ስራ አስከያጅ የሹመት ቃለ-ጉባኤ) አመልካች ወኪል የፀደቀ ማስረጃ ፓስፖርት/ የታደስ መታወቂያ/ዋናና ኮፒ ህጋዊ ዉክልና፡
✅etrade.gov.et ላይ ተመዝግቦ፡
✅ 1. ፈይዳ
✅ 2. የመዝጊያ ክሪላስ(Clearance)
✅ 3. etrade አገልገሎት መጠየቅ
✅ 4. 52 የአገልግሎት ክፍያ ከተከፈለ በኃላ የስረዛ ሰርተፍኬት ደብዳቤ መውረጃ::
✅ 1. ፈይዳ
✅ 2. የመዝጊያ ክሪላስ(Clearance)
✅ 3. ኦዲት
✅ 4. የመዝጊያ ቃለ ጉባኤ
✅ 5. etrade አገልገሎት መጠየቅ
✅ 6. 52 የአገልግሎት ክፍያ ከተከፈለ በኃላ የስረዛ ሰርተፍኬት ደብዳቤ መውረጃ::
1. ደረሰኝ (ከባንክ ማህተም ጋር tt ካልሆነ ለቁጥር ካልሆነ ለቁጥር. 5፣:6፣7፣8እና9)
2.ከባንክ እና አስመጪ ማህተም ጋር የመጫኛ ሂሳብ
3. ከባንክ ማህተም ጋር የመነሻ የምስክር ወረቀት
4. ከባንክ ማህተም ጋር የቴክኒክ የምስክር ወረቀት
5.የማሸጊያ ዝርዝር በባንክ ማህተም
6.የኢንሹራንስ ደረሰኝ ከአስመጪ ማህተም ጋር
7. የጭነት ደረሰኝ ደረሰኝ እና የባንክ ምክር
8. ስምምነት
9. ቫት
10. ቲን
11.የንግድ ፈቃድ
1. የምግብ እና ምግብ አቅራቢ ስራዎች
✅የምግብ አስመጪ
2. የመድኃኒት እና የጤና ምርት
✅መድኃኒት ሽያጭ (Pharmacy & Drug Retail)
✅የጤና ስራዎች (Health Service Providers)
3. ኮንስትራክሽን
✅ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የህንጻ ስራዎች
ለግል ነጋዴዎች የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
✅ፋይዳ
✅የቤት ኪራይ ውል
✅የአመልካች መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ
✅የአመልካቹ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸው ፎቶ ግራፎች
✅አመልካቹ የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ የኢንቨስትመንት ፍቃድ
✅የሚሰማራበት ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ከሆነ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት
✅etrade.gov.et ላይ ተመዝግቦ ምዝገባ እና ፍቃድ ማውጣህ
1.ከንግድ ሚኒስቴር የሥም ስያሜ ኦሪጅናል
2.የፀደቀ መመስረቻና ኮፒ
3. የቢሮ ኪራይ ዉል እና ውልና ማስረጃ የከፈሉበት ደረሰኝ ዋናውንና ኮፒ
4. የሥራ አስኪያጅ 6 ወር ወዲህ የተነሳዉ 2 ጉርድ ፎቶ
5. የሥራአስኪያጅ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ
6. የአባላት/የባለአክሲዮኖች ፋይዳ ቁጥር እና የግል ቲን ቁጥር ለሁሉም አባላት
7. ባለ አንድ አባል ኃላ/የተ/የግ/ማ ተመዝጋቢዎች የግል ንግድ ከነበሮት ዕዳ እንደሌለብዎት ከ ኢአ ገቢዎች ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይኖርቦታል፡፡
8. ኢሜል አድራሻ
9. የዉጭ አገር ዜጋ ከሆነ የሥራ ፈቃድ/workpermit/
10. አመልካች ወኪል ከሆነ ዉክልናዉ በድርጅቱ በማህበሩ ስም ሆኖ በሰነዶች የፀደቀ
✍️ለሀይማኖት ተቋማት ኤምባሲ NGO 1. አግባብ ካለዉ የመንግስት አካል የተሰጠ የምዝገባ ወረቀት(ስርተፊኬት) ኮፒ
2. መተዳደሪያ ደንብ ኦርጅናል እና ኮፒ
3.የቢሮ ኪራይ ዉል እና ውልና ማስረጃ የከፈሉበት ደረሰኝ ዋናውንና ኮፒ
4.ተቋሙን የሚወክለዉ ስዉ (ስራ አስከያጅ የሹመት ቃለ-ጉባኤ) አመልካች ወኪል የፀደቀ ማስረጃ ፓስፖርት/ የታደስ መታወቂያ/ዋናና ኮፒ ህጋዊ ዉክልና
5. የተቋሙ የበላይ ኃላፊ ወይም ተወካይ-ከ 6 ወር ወዲህ የተነሳዉ 2 ጉርድ ፎቶ-የታደሰ መታወቂያ ኮፒ- የግል TIN እና የፋይዳ ቁጥር
1.አዲስ የንግድ አድራሻ የተቀየረ የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፣
2.ለታክስ ባለ ስልጣኑ የአድራሻ ለውጥን ማሳወቅ
3.የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል ከግብርከፋዪ የታክስ ማዕከል የተጻፈ
4.የአድራሻ ለውጥ ደብዳቤ ለአቅራቢው መውሰድ፣
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣
3. ድርጅቱ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣
1. በተፈቀደላቸው ሒሳብ አዋቂ የተሰራ እንደሆነ የሒሳብ ሰራተኛው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቅጅ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፣
2. በድርጅቱ ሒሳብ ሠራተኛ የተሰራ እንደሆነ የሒሳብ ሰራተኛው የትምህርት መረጃ፤ በድርጅቱ ማህተም የተረጋገጠ የቅጥር ደብዳቤ ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
3. የገቢ ክፍፍል ቅፅ ተሞልቶ ከዓመታዊ ሪፖርት ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፣
4. ዓመታዊ ሽያጭ ከ5ዐዐ ሺህ በላይ ከሆነ የዋጋ ትልልፍ ቅጽ መረጃ ተሞልቶ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፣
5. የተሰራው ዓመታዊ ሪፖርት (የትርፍና ኪሳራ መግለጫ እንዲሁም ሀብትና ንብረት መግለጫ) በገቢዎች ቅጽ ተገልብጦ መቅረብ ይኖርበታል፣
6. የዓመታዊ ሽያጭ ማጠቃለያ (z-report) ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
7. ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ውጪ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ተጠቅመው እንደሆን የexcel Summary Report ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፣
8. የኦዲት ቦርድ የተመዘገቡበት ምስክር ወረቀት ቅጅ ተያይዞ ማቅረብ፣
9. ዓመታዊ ሪፖርት ውስጥ እርጅና ቅናሽ የተያዘ ንብረት ካለ በሠንጠረዥ የተሰላ ቅጽ አያይዞ ማቅረብ፣
10. ትርፍና ኪሳራ መግለጫ (Profit/Loss)፤ ሀብትና ንብረት መግለጫ (Balance Sheet)፤ የገንዘብ ፍሰት ማሳያ (Cash Flow)፤ የባለቤቶች ሁኔታ(Owners' Equity Position) እና የመረጃ ቋት መያዝ ይኖርበታል፣ (Ledger)
11. Withholding Tax Excel Summary ደረሰኝ ይዘዉ ይቅረቡ፣
12. ኦንላይን ያሳወቁበትን ማያያዝ ይኖርበዎታል፡፡
1.ከባለጉዳይ የሚጠበቅ የፅሁፍ እና የተግባር ፈተና ያለፈ። 2. ዕጩ አሽከርካሪው የቀጠሮ ወረቀት ማቅረብ
3. ከማሰልጠኛ ተቋሙ የሰልጣኝነት መታወቂያ ማቅረብ
4.የዕጩ አሽከርካሪው የመታወቂያ ኮፒ
5.ዕጩ አሽከርካሪው በአካል መገኘት
6.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
1. ከባለጉዳይ የድሮውን የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃው መንጃ ፈቃድ
2.የጤና ማስረጃ ከተፈቀደላቸው ተቋማት
3.የአገልግሎት ክፍያ
4. ባአቅራቢያው ባለው የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርቧ ማደስ ይችላል ።
1. የባለጉዳዩመታወቂያ 2.መንጃ ፈቃዱ ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ::
3.የአገልግሎት ክፍያ
4. ባአቅራቢያው ባለው የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርቧ የጠፍውን መንጃ ፍቃድ መውሰድ ይችላል ።
3.የአገልግሎት ክፍያ።
ተሽከርካሪ ሠሌዳ ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ለማሳተም ወደ ፐብሊክሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሄዱበት ጊዜ ምን መረጃ ማሟላት አለቦት?
✍️የተበላሸ ሰሌዳ|ታርጋ | ለመለወጥ የሚመጡ ከሆነ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፦ 1. የተሽከርካሪ ዋና ሊብሬ እና ኮፒ
2. የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ኮፒ
3. አገልግሎቱ በውክልና የሚሰጥ ከሆነ ዋናው ውክልና እና ኮፒ እንዲሁም የተወካይ መታወቂያ።
4. ከአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ሰሌዳ ምትክ እንዲታተም የተፈቀደበት ደብዳቤ።
5. ሊብሬውበባንክ በዕዳ የተያዘ ከሆነ የባንክ ደብዳቤና ሊብሬ ኮፒ በያዘው አካል በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ።
✍️የጠፋ ሰሌዳ /ታርጋ| ምትክ ለማሳተም የሚመጡ ተገልጋዬች ማሟላት የሚገባቸው መረጃዎች፦ 1. ከአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ሰሌዳ ምትክ እንዲታተም የተፈቀደበት ደብዳቤ።
2. ሊብሬ ዋናና ኮፒ
3. የታደሰ መታወቂያ ዋናና ኮፒ
4. አገልግሎቱ በውክልና የሚሰጥ ከሆነ ዋናው ውክልና እና ኮፒ እንዲሁም የተወካይ መታወቂያ፡፡
5. ስለመጥፋቱ የተመዘገበበት የፖሊስ ደብዳቤ
6. ኘሬስ የተከፈለበት ዋናው ደረሰኝ
7. ሊብሬውበባንክ በዕዳ የተያዘ ከሆነ የባንክ ደብዳቤና ሊብሬ ኮፒ በያዘው አካል በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ።
1. ባለቤት ከሆነ መታወቂያ ከሆነ ተወካይ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ::
2.ሊብሬው ስለመጥፋቱ የሚገልፆ የፖሊስ ደብዳቤ::
3. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
4. ክፍያ እና ሂደት በመፈፀም ሊብሬው ስለመጥፋቱ በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ማስወጣት::
5.ማስታወቂያው አየር ላይ ለ15 ቀን ከቆየ በኋላ ጋዜጣውን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማቅረብ::
6. የተበላሸ ከሆነ የተበላሸውን ሊብሬ 7.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም። 8. ፋይላችን ባለበት አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበን መስተናገድ እንችላለን።
1የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ!
2ባለንብረት ወይም ህጋዊ ተወካይ
3. የምርመራ በሰርተፊኬት የቆይታ ጊዜ ተሽከርካሪው ከተመረመረበት ቀን ጀምሮ ቦሎ ለኢት ሰሌዳ 30 ቀን ለሎሌች ክልል ወይም ከተማ መስተዳድር 20 ቀን ያላለፈው
4.ምርመራ ቦታ መጥቶ የተመረመረ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ሙሉ ሰነድ እና ሲስተም ላይ ያለፈ መሆኑ ሲረጋገጥ
5.የመንገድ ፈንድ የከፈለበት ደረሰኝ
6.የ3ኛ ወገን እንሹራንስ የገባበት ዉል
7.ለኮድ ) እና 3 በሰሌዳ፣ ሞተርና ሻንሲ ቁጥሩ ተለይቶ የተፃፈ የግብር ክሊራንስ ፣ አዲስ ወይም የታደስ ንግድ ፍቃድ
8.(ለግለሰብ) ለድርጅት አገልግሎት ከሆነ በሰሌዳ : ሞተርና ሻንሲ ቁጥሩ ባይጠቀስም የግብር ክሊራንስና የንግድ ፈቃድ በድርጅቱ ስም ተጽፎ ከመጣ መስተናገድ
9.የመንገድ ፈንድ ክፋያ ማንኛውም ተሽከርካሪ ለቦሎ አድሳት ከመቅረቡ በፊት በታሪፉ መሰረት የመድን ደረሰኝ ይዞ መቅረብ አለበት። ተቋማት ይህንን ሳያረጋግጉ አገልግሎት መስጠት የለባቸውም።
10.የአገልግሎት ክፍያዎችን የመክፈሉ ተረጋግጦ
11.የታደሰ መታወቂያ በመያዝ የተሽከርካሪ ፋይል ባለበት ቅርንጫፍ አገልግሎት ያግኙ
የባለቤትነት መብቱን ከቀድሞው ባለንብረት ወደ አዲሱ መብቱ ወደተላለፈለት ሰው ስመንብረቱን መዝግበን የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ለመስጠት የባለቤትነት መብቱ እንዲተላለፍ ያደረገው ሰው ወይም አካል ህጋዊ የሆነ መብት ያለው መሆኑን መረጋገጥ አለብት።
ማንኛውም ሰው አንድን ተሽከርካሪ ለመሸጥ ለመለወጥ ወይም በስጦታ ወደ ሌላኛው ሰው ማስተላለፍ የሚችለው ተሽከርካሪው በስሙ ተመዝግቦ ሲገኝ ወይም ተሽከርካሪውን በተመለከተ ከባለንብረቱ ህጋዊ የሆነ ሙሉ ውክልና ሲኖረው ነው።
በተጨማሪም ፍ/ቤቶች አንድን ተሽከርካሪ በሃራጅ እንዲሸጥ ወይም ያለ ሃራጅ ሽያጭ ወደ ሌላ ሰው ወገን እንዲተላለፍ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
ባንኮች በዋስትና የያዙትን ለመሸጥ ወይም ወደ ራሳቸው ስም ለማዞር የሚችሉበት ህጋዊ ስልጣን አላቸው።
የስም ዝውውር ወይም የባለቤትነት መብት የሚተላለፍባቸው ህጋዊ መንገዶች
1.ሽያጭ
2.ስጦታ
3.በመለዋወጥ
4.ውርስ /በኑዛዜ/ ያለኑዛዜ
5.በፍርድ ቤት ውሳኔ /ያለሀራጅ ሽያጭ
6.በፍርድ ቤት ውሳኔ በሐራጅ ሲሸጥ
7.በባንክ በሀራጅ ሲሸጥ
8.ባንኮች በዋስትና የያዙትን ወደ ራሳቸው ስም ሲያዞሩ
1. አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ መታወቂያ በውክልና ከሆነ የወኪል የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ
2.ሊብሬ 3. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ መያዝ አለበት።
4.ለጠፋ ቦሎ ከሆነ ቦሎው ስለመጥፋቱ ከፖሊስ የተፆፈ ደብዳቤ ማስረጃ ማቅረብ።
5.ለተበላሸ ቦሎ ከሆነ የተበላሸውን ቦሎ ማቅረብ አለበት።
6.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
7. ፋይላችን ባለበት አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበን መስተናገድ እንችላለን።
1.የማመልከቻ ቅጹን ሞልቶ ማቅረብ፤
2.ባስገቡአቸዉና በገጣጠሙአቸዉ ተሸከርካሪዎች ልክዝርዝር ኦርጅናል መረጃዎችንና የኦርጅናሉን መረጃ
3.ኮፒውን ማቅረብ፤
4.ባለፋብርካዎች፤ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች በየዓመቱ አንድ ጊዜ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ፤
5.ባለቤቱ ከሆነ የታደሰ የቀበለ መታወቂያ ኮፒ ወይም የጸና ፓስፖርት ኮፒ ወይም
6.በወክል ከሆነ በዉልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ የውክልናና የታደሰ የቀበለ መታወቂያ ኮፒ፤
7.በየዓመቱ አንድ ጊዜ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ፤
8.ባለፋብርካዎች፤ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች አዲስ ሠሌዳ ለመዉሰድ በሚመጡበት ወቅት ከዚህ በፊት
9.የወሰዱአቸዉን ሠሌዳዎች በየተሸከርካሪዎቹ ላይ በአግባቡ መለጠፋቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ በተዘጋጀዉ ቅጽ መሰረት ሞልቶ ማቅረብ፤
10.የሚፈለረጉትን የሠሌዳ ብዛትና ለየተሸከርካሪዎቹ የሚገጥመዉን የሠሌዳ ዓይነት ለይቶ ጥያቄ ማቅረብ፤
11አስፈላጊውን የአገልግሎት ክፊያ በመፈጸም ሠሌዳዉ እንዲመረት ትዕዛዝ መስጠት፤
12ሠሌዳዉን በአካል ቀርቦ መረከብ ናቸዉ።
1. መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ከፓስፖርት ጋር
2. በውክልና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት
3. ከመስሪያ ቤቱ ወይም ከድርጅቱ የተወከለ ከሆነ የድርጅቱ የውክልና ደብዳቤና የድርጅቱ መታወቂያ
4. ኦርጅናል የጉምሩክ ዲክላራሲዮን
5. ሁለት ጉርድ ፎቶ ቲምብር (በውክልና ከሆነ ፎቶ አያስፈልግም)
6. የታደሰ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ እና የአስመጪነት ፈቃድ፣ የማስገቢያ ፈቃድ
7. የተሽከርካሪ መመርመሪያ ቅፅ (ሊብሬ ወረቀት)
8. ደረሰኝ (Invoice) በባለቤት ስም ከካሽ ሬጅስተር ጋር፤ የእጅ በእጅ ሽያጭ ከሆነ የደረሰኝ ህትመትና የማስተመሪያ ፈቃድ (ከባንክ ማህተም ጋር tt ካልሆነ ለቁጥር 5፣ 6፣ 7፣ 8 እና 9)
9. ከጉምሩክ በደረሰኝ መነሻ ቁጥር የተፈቀደበት ደብዳቤ
10. የሶስተኛ ወገን መድን የመንገድ ፈንድ
11. ከባንክ እና አስመጪ ማህተም ጋር የመጫኛ ሂሳብ
12. ከባንክ ማህተም ጋር የመነሻ የምስክር ወረቀት
13. ከባንክ ማህተም ጋር የቴክኒክ የምስክር ወረቀት
2. በጨረታ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ
1. ተሽከርካሪው ቀረጥ ያልከፈለና ዲክላራሲዮን የሌለው ከሆነ አዲስ በገዛው የተሰራ ዲክላራሲዮን ከገቢዎችና ጉምሩክ2. የጨረታ አሸናፊ ደብዳቤ
3. ጨረታ የወጣበት ቀን፣ ቁጥር፣ የጋዜጣው ስም፣ የአሸናፊው ስም፣ የተሽከርካሪው ቻሲና ሞተር ቁጥር፣ ጨረታውን ያሸነፈበት ዋጋ፣ የክፍያ ደረሰኝ
4. ድርጅት ከሆነ ከመንግስት መ/ቤት ውጭ ከሆነ ብቻ ድርጅቱ ስም ይመዘገባል
5. ከአገልግሎት ውጪ ከሆነ (ኢንሹራንስ) ባለቤቱ ይመዘገባል
6. የአመታዊ ቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ሰርተፊኬት ማምጣት
1.መኪናው ተመዝግቦ ካለበት ፅ/ቤት የዝውውር ቅፅ ተሞልቶ በፖስታ ታሽጎ ለተቀባይ ፅ/ቤት በፖስታ ማስላክ
2. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ
3.ተሽከርካሪውን ለፅ/ቤቱ ባለሙያ እይታ በአካል ማቅረብ፤
4.የተሽከርካሪውን ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ /ታርጋ/ ማስረከብ፤
5 ለአገልግሎት ክፍያ
6. ምትክ ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ -ታርጋ- መረከብ።
✅ የተቀባይ የፓስታው አድራሻ በአግባቡ መሟላት አለበት ፖስታው ከመላኩ በፊት የዝውውር ጥያቄው በትክክለኛ የዝውውር ቅፅ መሞላቱን ማረጋገጥ ይኖርበናል ምክንያት በትክክል ካልተሟላ ያላስፈላጊ እንግልት እንዳረጋለን።
✅የፋይል ዝውውር ቅፁ ከተሞላ 6 ወር ከሞላው ቅፁ ተቀባይነት ስለማይኖረው ቅፁ በተሞላ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቀባይ ፅ/ቤት በመቅረብ እና ጉዳያቸሰነሰ በ6 ወር ውስጥ ማከናወን አለብን።
✅ ከፖሊስ የተሰጠ የጠፋ ማስረጃ
✅ 3 ጉርድ ፎቶግራፍ
✅ የአገልግሎት ክፍያ ደረሰኝ
ፈቃዱን ለማውጣት ዋናውንና ኮፒውን (Original & Copy) ይዘው መቅረብ ያለብዎት ሰነዶች፦
1. 📜 አፕሩቫል ሰርተፍኬት (Approval Certificate)
2. 🪪 የመንጃ ፈቃድ
3. 🎓 የቅጥር ወይም የትምህርት ማስረጃ
4. ✉️ የማስተማሪያ ፈቃድ ይሰጥልኝ ደብዳቤ፦ ከሚያስተምሩበት የደረጃው ማሰልጠኛ ተቋም የተጻፈ መሆን አለበት።
5. 📄 ክሊራንስ (Clearance)
6. 🏆 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC)፦ በየደረጃው (Level) ላጠናቀቁት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ነው።
7. 💳 የአገልግሎት ክፍያ
💡 "ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመር 7766 ላይ መደወል ይችላሉ።"
1. 📝 የሃገሪቱ ትራንስፖርት ባለስልጣን የመንጃ ፈቃድ ትክክለኛነት ያረጋገጠበት ደብዳቤ።
2. 🏛️ በሃገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ / ኤምባሲ የሰነዱን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይኖርበታል።
3. 📜 የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰነዱን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለበት።
4. 🏢 ደብዳቤው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ መረጋገጥ ይኖርበታል።
5. 📸 6 ወር ያልሞላው ጉርድ ፎቶግራፍ ማቅረብ።
6. 💳 ኦሪጅናል የክፍያ ደረሰኝ እና የአገልግሎት ክፍያ።
7. 🪪 የእድሳት ዘመን ያላለፈበት የውጭ መንጃ ፈቃድ (ኦሪጅናል እና ኮፒ)።
8. 🛂 ፓስፖርት (ኦሪጅናል እና ኮፒ)።
9. 🏠 የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ግሪን ካርድ ኮፒ።
10. 👤 ግለሰቡ በአካል በመቅረብ ሂደቱን ማከናወን ይኖርበታል።
1. 🧾 የክፍያ ደረሰኝ እና የዝውውር ሰነድ፦ ከሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ 2% የተከፈለበት ደረሰኝ እና የስም ዝውውር ሰነድ።
2. 🛡️ የኢንሹራንስ ሰነድ፦ በኮፒ 03 በኮፒ 01 ከገዢዎች የተገኘ የሶስተኛ ወገን መድን (ኢንሹራንስ) ማስረጃ።
3. ⚖️ ህጋዊ ውክልና ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ፦ የፍርድ ቤት ውሳኔ (ከታዘዘ) ወይም በውክልና የመጣ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ሰነድ እና የቪዛ ማረጋገጫ (ቲምብር)።
4. 🏷️ የዘመኑ ቦሎ፦ የተሽከርካሪው የዘመኑ ቦሎ የተደረገ መሆን አለበት።
5. 👥 የሶስተኛ ወገን መገኘት/ማስረጃ።
ተሽከርካሪን ከቀረጥ ነፃ ለማድረግ (Tax-Free) የሚከተሉትን ዋና ዋና ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅብዎታል፦
1. 📖 ሊብሬ (የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ)
2. 🤝 በውክልና ከሆነ፦ ህጋዊ ውክልና (Power of Attorney) እና የባለቤቱ/የተወካዩ መታወቂያ
3. 📄 በባለንብረቱ ስም የተዘጋጀ ዜሮ ዲክላሬሽን (Zero Declaration) ከጉምሩክና ገቢዎች ቢሮ
4. 📸 ጉርድ ፎቶግራፍ
1.ኦርጅናል ካርታ መታወቂያ
2.በውክልና የሚንቀሳቀስከሆነ ውክልና እና የተወካይመታወቅያ
3.ጉርግ ፎቶ2
4. ካርታው እነ ከሆነ የሁሉም ፎቶ በአንድ በሰርቶ
5.የዘመኑንግብርየተከፈለበት ደረሰኝ 6.ለአገልግሎቱ የሚከፈል ክፍያ
1. በለይዞታው/ ተወካዩእጅ የሚገኘውን ካርታ ዋነውንና ፎቶ ኮፒውን
2.ማንነትን የሚገልፅጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይምመንጃፍቃድ ወይም የግበርከፋይነት መታወቂያዋናውን ከፒውን
3.ንብረቱ በውክልና የሚንቀሳቀስ/ የሚተዳደርከሆነ ውክልና ዋናውንና ኮፒውን
4.ከወረዳ ዳግብርአስከፋይጽ/ ቤት የተሰጠ የዘመኑ ግብርመከፈሉን የሚያረግጥደረሰኝ
ማሳሲያ ወረዳላይ ሳይወራረድናደረሰኝ ሳይዙ በባንክ ወይም በቴሌብር የተከፈለበት ስሊፕ ብቻ ለአገልግሎት ብቁ አያደርግም፡፡
5.የአገልግሎትና የዲጂታል ካርታ መውደጃ ብር 3000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
6.,በቤቱ ላይያለተነሳ የባንክ እዳ እገዳ ካለ ከባንክ የሚሰጥ የዕግድ ማስነሻ ደብዳቤዋናውን ማቅረብና 25000.00(ሁለት ሺ አምሰት መቶብር)የአገልግሎትክፍያ መክፈል
7. 2ብዛት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ(ካርታው ላይ በስም የተጠቀሰው ባለይዞታወይምየተጠቀሱት(እነ) ባለይዞታዎች ፎቶ
1.ኦርጅናል ካርታኮፒ
2.መታወቅያ የፓስፖርት መንጃ
3.የውክልና መረጃ ኮፒ
4.የሊዝውል በሪልእስቴቱእና በግለሰቡ የተዋዋሉበት መረጃ
5.የባንክ ብድር ካለበት ባንክ መፍቀድ ስላለበት ባንኩ የሚፈቀደበት መረጃ ከባንክ የተፃፈ መረጃ
6.ግንባታቸው 50% በላይ የሆናቸው
1.የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
2.ማንነትን የሚገልጽ የታደሰ መታዎቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣
3.ፓስፖርት ወይም ፋይዳ መታዎቂያ፣
4.ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣
5.ይዞታው በሊዝ የተገኘ ከሆነ የሊዝ ውል፣
6.የፍርድ ቤት ውሳኔ ካለ፣
7.ህጋዊ የውል ሰነዶች፡- የውክልና፤ የስጦታ፣ የውርስ ፤የሽያጭ ውል ካለ፣
1.የይዞታይረጋገጥልኝ ጥያቄ አቅራቢዉ ያቀረበዉሰነድየሃሰት ማስረጃመሆኑ ከተረጋገጠ፤
2.ማስረጃዉበግልጽ የማይነበብ ከሆነ፤
3.ማስረጃውስርዝ ድልዝ ሆኖ ከተገኘ፣
4.ግዜዉ ያለፈበት፣ያልተፈረመበትእና ማህተም ያላረፈበት ሰነድ ከሆነ ሰነዶቹ ተቀባይነትአይኖራቸውም
1 ይዞታው ዕገዳና ዋስትና የሌለበት መሆኑ ከማኀደሩ ውስጥ ሲረጋገጥ፡ 2. የታደሰ መታወቂያ 3. ከፖሊስ ጣቢያ ካርታው ስለመጥፋቱ ማስረጃ ሲያቀርብ፣ 4. የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የጠፋበት አካል በክ/ከተማዉ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሪከርድና ማህደር ክፍል ውስጥ በስመ የተመዘገበ ማህደር ሲኖረው እና በማህደሩ ውስጥ ያሉት ሰነዶች በህጋዊ መንገድ ቦታውን ስለማግኘቱ ማመልከት ሲችሉና የካርታ ኮፒ ሲኖር፣ 5.የባለይዞታው የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መጥፋቱ፡ በፍ/ቤት አማካኝነት ወይም በ ጋዜጣ ማስታወቂያ ወጥቶ በ20 ቀን ውስጥ ተቃዋሚ ካልቀረበ እና 6. ባለጉዳዩ አስፈላጊ የአገልግሎት እና ሌሎች ክፍያዎችን ሲከፍልና ይኸው ሁኔታ በወረዳው ወይም በክፍለ ከተማው ገቢዎች ጽ/ቤት ሲረጋገጥ፡ 7. ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ሲያቀርብ፡ 8. የቤቱ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ተወካይ መሆኑን ክወረዳው አስተዳደር ማረጋገጫ ሲያቀርብ፤ የጠፋው ካርታ በቅድሚያ -እንዲመክን በማድረግ ምትክ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቶ ይሰጣል።
2.የሻጭ እና የገዚ መታወቂያ
3.ሊብሬ
4. ከእዳ እገዳ ነፆ የሚገልፆ ደብዳቤ
5. የሻጭ የመሸጥ የመለወጥ መብት ስልጣን ህጋዊ ሰነድ(ውክልና)
5. የሻጭ የገባ-ያላገባ የገባ ከሆነ የትዳርአጋር የፍቃድ ስምምነት
6. የገዛችሁት ከማህበር ከሆነ የንግድ ምዝነባ መመስረቻ ፁሁፍ እና ቃለጉባኤ
7. 1-3 መኪናው ከቀረፆ ነፅ ከሆነ 10 ቢሞላውም ከግሙሩክ ከቀረፅ ነፆ ማስተላለፍ ደብዳብ ወይም ይህንን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠውን ማረጋገጫ ሰነድ
7. ከመንገድ ትራንስፖርት የሚሰጥ ወቅታዊ የመኪና ግምኝ
8 1-3 ከሆነ ከገቢዎየች የሚሰጥ የግብርክሪላስ (የታደሰ ንግድ ፍቃድ)
9. መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠውን የማረጋገጫ ሰነድ
2. እዳ እና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፤
3. የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ ፤
4. የስጦታ አድራጊውና የስጦታ ተቀባይ የነዋሪነት መታወቂያ፤
5. ስጦታ አድራጊው እና ስጦታ ተቀባይ ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
6. ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
7. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
8. የስጦታ አድራጊው ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋርየፈቃድ ስምምነት፤
9. ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የዋጋ ግምት፤
10. ለኮድ 1 እና 3 ከገቢዎች እና ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ ክሊራንስ፤
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ መቅረቡን፤
3, የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ መቅረቡን፣
4. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘ ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፡ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልፅ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
8. ሻጭ ግለሰብ ከሆነ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. የሚተላለፈው ንብረት ነባሩ ካርታ ከሆነ የጀርባ ማህተም መመታቱን፣
10 የንግድ ሥራ በተከናወነበት ድርጅት ቤት ስም የወጣ የንግድ ፈቃድ እና የገቢዎች ክሊራንስ መቅረቡን
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥርየያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ መቅረቡን፤
3. በጋራ የተመዘገብ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ (ካርታ) መቅረቡን፣
4. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘት ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልፅ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7.ንብረቱ እገዳ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዝገቢው አካል የተሰጠ ማስረጃ ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
8. የተዋዋይ ወገኖች ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳርአጋርየፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. የሚከፈለው የጋራ ንብረት ነባሩ ካርታ ከሆነ የጀርባ ማህተም መመታቱን፣
10. የሚከፈለው የጋራ ንብረት በሽያጭከሆነ የተጋሪው ቅድሚያ የመግዛት መብት መጠበቁን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ።
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥርየያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ መቅረቡን፤
3. ከፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ ወይም በፍ/ቤት የጸደቀ የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ መቅረቡን፣
4. ውሉ የሚደረገው በወራሾች መካከል መሆኑን እና የሚለቀቀው የድርሻ መብት ሙሉ በሙሉ
5. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም በፍርድ ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤
6. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
5. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም በፍርድ ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤
6. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
7. ፈራሚው ሌላ ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥርየያዘ መሆኑን፣
2. የዋስትና ውሉ የሚመሠረትበት የጸና መብትና ግዴታ የተቋቋመበት ውል መኖሩን፣
3. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ መቅረቡን፤
4. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን
5. ዋሱ የገባው የዋስትና ግዴታ የገንዘብ ልክ ወይም መጠን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑን፣
6. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን ፤
7. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃለፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
8. የተዋዋዮች ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋርየፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. ዋስትናው ንብረት በማስያዝ ከሆነ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ መቅረቡን፣
10. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዘጋቢው አካል ከተሰጠ ማስረጃ እና ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የአገልግሎት መስጫ ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይ መከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ መቅረቡን፤
3. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤
4. የብድር ስምምነቱ የውል ጊዜ ሰነዱ ሊረጋግጥ ከቀረበበት ቀን ወደኋላ የተደረገ አለመሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን ፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃለፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7. የተዋዋዮች ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋርየፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
8. የብድር ውሉ በመያዣ ከሆነ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ መቅረቡን፣
9. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዘጋቢው አካል ከተሰጠ ማስረጃ እና ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
10. መያዣው የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት ምስክሮች የቀረቡ መሆኑን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
1.የሽያጭውል
2.ኦርጅናልካርታ
3.ውክልና ካለውክልና
4.የታደሰ የቀበሌ መታወቅያ
5.ፎቶግራፍ
6.ወራሾች ከሆኑ የፍርድ ቤት የውርስ ወረቀት
1.በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ
2.የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፤
3.የሻጭና የገዥ መታወቂያ፤
4 ከእዳ እገዳ ነፆ መሆኑን የሚያገልፆ ደብደቤ
5. ሻጭ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ፤
6 .ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ ቃለጉባኤ፤
7. የሻጭ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
8. ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፤
9. ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
10. ለኮድ 1 እና 3 አስር ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ ወይም ይህን መነሻ በማድረግ መንገድ ትራንስፖርት የሚሰጠው የማረጋገጫ ሰነድ፤
11 . ለኮድ 5 11 እና 35 የመሳሰሉት ከሐይማኖት ተቋማት በስተቀርከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የማስተላለፍ የዕውቅና (የድጋፍ) ደብዳቤ፤
12. ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ የምስከር ወረቀት የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ስራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
1. 💻 የመስመር ላይ ሲስተም ቁጥር፦ የሚረጋገጠው የመመሥረቻ ጽሑፍ በኦንላይን (በተቋሙ የዓይሌ ሲስተም) ተሞልቶ የጉዳይ መከታተያ ቁጥር (Token Number) ሊኖረው ይገባል።
2. 📄 የተዘጋጀ መመስረቻ ጽሁፍ በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (PLC)
3. 🪪 የመታወቂያ ሰነድ፦ የሰነድ ፈራሚዎች በሙሉ ሕጋዊ መታወቂያ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
4. ✍️ የመፈረም ሥልጣን፦ ፈራሚው በሕግ፣ በውክልና ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ የመፈረም ሙሉ ሥልጣን ያለው መሆኑ ይረጋገጣል።
5. 🔤 የስም ፈቃድ ደብዳቤ፦ የንግድ ማኅበሩ ስም መያዙን የሚገልጽ ከሚመለከተው የመንግሥት መዝጋቢ አካል የተሰጠ ደብዳቤ መቅረብ አለበት።
6. 🏠 የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ፦ በንግድ ማኅበሩ ውስጥ በዓይነት (በንብረት) የሚደረግ መዋጮ ካለ፣ የንብረቱ ባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ነው።
7. 👥 የአባላት ብዛትና የካፒታል መጠን ገደብ፦ የማኅበሩ አባላት (ባለአክሲዮኖች) ብዛት ከሁለት (2) ያላነሰ እና ከኃምሳ (50) ያልበለጠ መሆን አለበት፤ እንዲሁም የማኅበሩ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ከ 15,000 (ከአሥራ አምስት ሺህ) ብር ያነሰ አለመሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል።
8. 👥 የቦርድ አባላት ብዛት ገደብ፦ የንግድ ማኅበሩ የሥራ አመራር ቦርድ (Board of Directors) ያለው ከሆነ፣ የቦርድ አባላቱ ብዛት ከሦስት (3) ያላነሰ እና ከሰባት (7) ያልበለጠ መሆኑ ይረጋገጫል።
9. 🪙 የአንድ አክሲዮን አነስተኛ ዋጋ፦ በማኅበሩ ውስጥ የሚቀመጠው የአንድ አክሲዮን (Share) ዋጋ ከ 100 (ከመቶ) ብር በታች አለመሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
10. 🔍 ንብረቱ ዕገዳ የሌለበት መሆኑ፦ ንብረቱ ዕገዳ የሌለበት መሆኑን ከንብረት መዝጋቢው አካል የተሰጠ ማስረጃና ከተቋሙ የመረጃ ዴስክ ዕገዳ አለመኖሩ መረጋገጥ አለበት።
11. 🏗️ የማይንቀሳቀስ ንብረት (ሕንፃ/መሬት) ከሆነ፦ መዋጮው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሆኖ በኢንቨስትመንት የተሰጠ ከሆነ፣ ንብረቱ ከሚገኝበት ክልል የኢንቨስትመንት ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ መቅረብ አለበት።
12. 📦 ከቀረጥ ነፃ የገባ ንብረት ከሆነ፦ መዋጮው ከቀረጥ ነፃ የገባ ንብረት ከሆነ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር ከቀረጥ ነፃ መሆኑ ከተገለጸው ውጭ ከሆነ የማስተላለፊያ ፈቃድ ደብዳቤ ወይም ዲክላራሲዮን መቅረብ ይኖርበታል።
13. 🏢 የሌላ የንግድ ማኅበር አባልነት፦ በንግድ ማኅበሩ ውስጥ ሌላ የንግድ ማኅበር በአባልነት የሚመዘገብ ከሆነ የመመሥረቻ ጽሑፍ፣ የንግድ ምዝገባ እና እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረብ አለበት።
14. 👶 ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች አባል ከሆኑ፦ በንግድ ማኅበሩ ውስጥ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው በአባልነት የሚመዘገብ ከሆነ፣ የልደት ሰርተፍኬት እንዲሁም የወላጆች የጋራ ፈቃድ ወይም በውክልና/በፍርድ ቤት የተሰጠ የሞግዚትነት ማስረጃ መቅረብ አለበት።
15. 🤝 የውህደት ማኅበር ከሆነ፦ የሚረጋገጠው የመመሥረቻ ጽሑፍ አዲስ የሚመሠረት የውህደት ማኅበር ከሆነ፣ የየማኅበራቱ የውህደት ውሳኔና ለውጥ ከሆነ የለውጥ ውሳኔውን የሚገልጽ ቃለ ጉባኤ ማቅረብና ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይመከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣
2. የሰነድ ፈራሚዎችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ መቅረቡን፤
3, የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ መቅረቡን፣
4. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘ ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣
5. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፡ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤
6. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበርከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክርወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልፅ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤
7. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
8. ሻጭ ግለሰብ ከሆነ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት መኖሩን፤
9. የሚተላለፈው ንብረት ነባሩ ካርታ ከሆነ የጀርባ ማህተም መመታቱን፣
10. የሚተላለፈው የጋራ ንብረት በሽያጭከሆነ የተጋሪው ቅድሚያ የመግዛት መብት መጠበቁን፣
11. ንብረት ገዢው የውጭ ሃገር ዜጋ ከሆነ የታደሰ በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ወይም ቢያንስ አሥር ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በሥራ ላይማዋሉን የሚገልጽ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን (ከሚመለከተው አካል) ማስረጃ እና የኢንቨስትመንት ፈቃድ መቅረቡን፣
12. ንብረት ገዢው የውጭ ሃገር ዜጋ ሌላ የመኖሪያ ቤት በስሙ የሌለ መሆኑን የሚገልጽ ከሚመለከተው የንብረት መዝጋቢ አካል ደብዳቤ መቅረቡን፣ ማጣራትና ማረጋገጥ።
📝 ሰነዶችን የማስተካከያ መመሪያ
• ወይም ወደ ስልክዎ Download በማድረግ ይጠቀሙ።
ለግለሰብ ነጋዴዎች፣ PLC፣ ለባለአንድ አባል PLC፣ አክሲዮን ማህበራት ለመመስረት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እና አጠቃላይ ትንታኔ።
📥 አዲሱ የንግድ ሕግ መመሪያ አውርዱየተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመላሽ የሚደረግበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1132/2018።
📥 መመሪያ ቁጥር 1132/2018 አውርድየጉምሩክ ዕቃዎችን በዋስትና (Security) ስለሚለቀቁበት ዝርዝር ሁኔታና ቅድመ ሁኔታዎች የወጣ መመሪያ።
📥 የዋስትና መመሪያውን አውርድየቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሥርዓት አፈፃፀምን የተመለከተ አዲስ እና ወቅታዊ መረጃ ዝርዝር መግለጫ።
📥 ወቅታዊ የቀረጥ ነጻ መረጃውን አውርድየጉምሩክ ዋጋ ዝርዝር መግለጫ (VDD - Valuation Details Declaration) ምንነትና አቀራረብ መመሪያ።
📥 የVDD መመሪያውን አውርድየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው አዲስ የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ ቁጥር FVD/01/2026። ከመደበኛ ባንክ ውጭ በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ዕቃ የሚያስገቡ አካላት ማወቅ ያለባቸው ወሳኝ ደንቦችና ትንታኔ።
📥 የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያውን አውርድየኢንቨስትመንት አዋጁን በተግባር ላይ ለማዋል የወጡ ዝርዝር አሰራሮችን፣ ማበረታቻዎችንና ደንቦችን የያዘው የኢንቨስትመንት ደንብ ሙሉ ሰነድ።
📥 የኢንቨስትመንት ደንቡን አውርድ (PDF)በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ለመምራትና ለማበረታታት የወጣው የኢንቨስትመንት አዋጅ ሙሉ ዝርዝር ሰነድ።
📥 የኢንቨስትመንት አዋጁን አውርድ (PDF)የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ይፋ ያደረገው አዲስ የ"ጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ" ረቂቅ መመሪያ (ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም)።
📥 ረቂቅ መመሪያውን በDocs አንብብ / አውርድየጉምሩክ አሰራርን ለማዘመን፣ የንግድ ፍሰቱን ለማቀላጠፍና ቁጥጥርን ለማጠናከር የተዘጋጀው አዲስ የጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አጭር መግለጫ ሙሉ ሰነድ (2018 ዓ.ም)።
📥 የማሻሻያ ረቂቅ መግለጫውን አውርድ (PDF)
No comments:
Post a Comment