መንጃ ፍቃድ ለማውጣት+
መንጃ ፍቃድ ለማውጣት የሚያስፈልጉ ሰነዶች ፡
1.ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
የፅሁፍ እና የተግባር ፈተና ያለፈ።
2. ዕጩ አሽከርካሪው የቀጠሮ ወረቀት ማቅረብ
3. ከማሰልጠኛ ተቋሙ የሰልጣኝነት መታወቂያ ማቅረብ
4.የዕጩ አሽከርካሪው የመታወቂያ ኮፒ
5.ዕጩ አሽከርካሪው በአካል መገኘት
6.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
መንጃ ፈቃድ ለማደስ
+
መንጃ ፈቃድ ለማደስ
፡
1. ከባለጉዳይ የድሮውን የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃው መንጃ ፈቃድ
2.የጤና ማስረጃ ከተፈቀደላቸው ተቋማት
3.የአገልግሎት ክፍያ
4. ባአቅራቢያው ባለው የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርቧ ማደስ ይችላል ።
በጠፋ መንጃ ፈቃድ ምትክ ለማግኘት
+
በጠፋ መንጃ ፈቃድ ምትክ ለማግኘት
፡
1. የባለጉዳዩመታወቂያ
2.መንጃ ፈቃዱ ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ::
3.የአገልግሎት ክፍያ
4. ባአቅራቢያው ባለው የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርቧ የጠፍውን መንጃ ፍቃድ መውሰድ ይችላል ።
3.የአገልግሎት ክፍያ።
የጠፋ ሰሌዳ ና የተበላሸ+
ለጠፋ ሰሌዳ የተበላሸ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ፡
ተሽከርካሪ ሠሌዳ ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ለማሳተም ወደ ፐብሊክሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሄዱበት ጊዜ ምን መረጃ ማሟላት አለቦት?
✍️የተበላሸ ሰሌዳ|ታርጋ | ለመለወጥ የሚመጡ ከሆነ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች፦
1. የተሽከርካሪ ዋና ሊብሬ እና ኮፒ
2. የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ኮፒ
3. አገልግሎቱ በውክልና የሚሰጥ ከሆነ ዋናው ውክልና እና ኮፒ እንዲሁም የተወካይ መታወቂያ።
4. ከአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ሰሌዳ ምትክ እንዲታተም የተፈቀደበት ደብዳቤ።
5. ሊብሬውበባንክ በዕዳ የተያዘ ከሆነ የባንክ ደብዳቤና ሊብሬ ኮፒ በያዘው አካል በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ።
✍️የጠፋ ሰሌዳ /ታርጋ| ምትክ ለማሳተም የሚመጡ ተገልጋዬች ማሟላት የሚገባቸው መረጃዎች፦
1. ከአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ሰሌዳ ምትክ እንዲታተም የተፈቀደበት ደብዳቤ።
2. ሊብሬ ዋናና ኮፒ
3. የታደሰ መታወቂያ ዋናና ኮፒ
4. አገልግሎቱ በውክልና የሚሰጥ ከሆነ ዋናው ውክልና እና ኮፒ እንዲሁም የተወካይ መታወቂያ፡፡
5. ስለመጥፋቱ የተመዘገበበት የፖሊስ ደብዳቤ
6. ኘሬስ የተከፈለበት ዋናው ደረሰኝ
7. ሊብሬውበባንክ በዕዳ የተያዘ ከሆነ የባንክ ደብዳቤና ሊብሬ ኮፒ በያዘው አካል በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ።
ለጠፋ ወይም የተበላሸ ሊብሬ የሚያስፈልጉ ሰነዶች +
ለጠፋ ወይም የተበላሸ ሊብሬ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ፡
1. ባለቤት ከሆነ መታወቂያ ከሆነ ተወካይ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ::
2.ሊብሬው ስለመጥፋቱ የሚገልፆ የፖሊስ ደብዳቤ::
3. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
4. ክፍያ እና ሂደት በመፈፀም ሊብሬው ስለመጥፋቱ በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ማስወጣት::
5.ማስታወቂያው አየር ላይ ለ15 ቀን ከቆየ በኋላ ጋዜጣውን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማቅረብ::
6. የተበላሸ ከሆነ የተበላሸውን ሊብሬ
7.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
8. ፋይላችን ባለበት አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት
ቀርበን መስተናገድ እንችላለን።
ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራና ምዝገባ/ቦሎ/ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ሠነ ዶች
+
ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራና ምዝገባ/ቦሎ/ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ሠነ ዶች
፡
1የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ!
2ባለንብረት ወይም ህጋዊ ተወካይ
3. የምርመራ በሰርተፊኬት የቆይታ ጊዜ ተሽከርካሪው ከተመረመረበት ቀን ጀምሮ ቦሎ ለኢት ሰሌዳ 30 ቀን ለሎሌች ክልል ወይም ከተማ መስተዳድር 20 ቀን ያላለፈው
4.ምርመራ ቦታ መጥቶ የተመረመረ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ሙሉ ሰነድ እና ሲስተም ላይ ያለፈ መሆኑ ሲረጋገጥ
5.የመንገድ ፈንድ የከፈለበት ደረሰኝ
6.የ3ኛ ወገን እንሹራንስ የገባበት ዉል
7.ለኮድ ) እና 3 በሰሌዳ፣ ሞተርና ሻንሲ ቁጥሩ ተለይቶ የተፃፈ የግብር ክሊራንስ ፣ አዲስ ወይም የታደስ ንግድ ፍቃድ
8.(ለግለሰብ) ለድርጅት አገልግሎት ከሆነ በሰሌዳ : ሞተርና ሻንሲ ቁጥሩ ባይጠቀስም የግብር ክሊራንስና የንግድ ፈቃድ በድርጅቱ ስም ተጽፎ ከመጣ መስተናገድ
9.የመንገድ ፈንድ ክፋያ ማንኛውም ተሽከርካሪ ለቦሎ አድሳት ከመቅረቡ በፊት በታሪፉ መሰረት የመድን ደረሰኝ ይዞ መቅረብ አለበት። ተቋማት ይህንን ሳያረጋግጉ አገልግሎት መስጠት የለባቸውም።
10.የአገልግሎት ክፍያዎችን የመክፈሉ ተረጋግጦ
11.የታደሰ መታወቂያ በመያዝ የተሽከርካሪ ፋይል ባለበት ቅርንጫፍ አገልግሎት ያግኙ
የመኪና የስም ዝውውርህግ ነክ አገልግሎት +
የመኪና የስም ዝውውርህግ ነክ አገልግሎት
፡
የባለቤትነት መብቱን ከቀድሞው ባለንብረት ወደ አዲሱ መብቱ ወደተላለፈለት ሰው ስመንብረቱን መዝግበን የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ለመስጠት የባለቤትነት መብቱ እንዲተላለፍ ያደረገው ሰው ወይም አካል ህጋዊ የሆነ መብት ያለው መሆኑን መረጋገጥ አለብት።
ማንኛውም ሰው አንድን ተሽከርካሪ ለመሸጥ ለመለወጥ ወይም በስጦታ ወደ ሌላኛው ሰው ማስተላለፍ የሚችለው ተሽከርካሪው በስሙ ተመዝግቦ ሲገኝ ወይም ተሽከርካሪውን በተመለከተ ከባለንብረቱ ህጋዊ የሆነ ሙሉ ውክልና ሲኖረው ነው።
በተጨማሪም ፍ/ቤቶች አንድን ተሽከርካሪ በሃራጅ እንዲሸጥ ወይም ያለ ሃራጅ ሽያጭ ወደ ሌላ ሰው ወገን እንዲተላለፍ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
ባንኮች በዋስትና የያዙትን ለመሸጥ ወይም ወደ ራሳቸው ስም ለማዞር የሚችሉበት ህጋዊ ስልጣን አላቸው።
የስም ዝውውር ወይም የባለቤትነት መብት የሚተላለፍባቸው ህጋዊ መንገዶች
1.ሽያጭ
2.ስጦታ
3.በመለዋወጥ
4.ውርስ /በኑዛዜ/ ያለኑዛዜ
5.በፍርድ ቤት ውሳኔ /ያለሀራጅ ሽያጭ
6.በፍርድ ቤት ውሳኔ በሐራጅ ሲሸጥ
7.በባንክ በሀራጅ ሲሸጥ
8.ባንኮች በዋስትና የያዙትን ወደ ራሳቸው ስም ሲያዞሩ
በጠፋ ወይም በተበላሸ ቦሎ ምትክ ለማውጣት?
+
በጠፋ ወይም በተበላሸ ቦሎ ምትክ ለማውጣት?፡
1. አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ መታወቂያ በውክልና ከሆነ የወኪል የታደሰ መታወቂያ እና
በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ
2.ሊብሬ
3. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ መያዝ አለበት።
4.ለጠፋ ቦሎ ከሆነ ቦሎው ስለመጥፋቱ ከፖሊስ የተፆፈ ደብዳቤ ማስረጃ ማቅረብ።
5.ለተበላሸ ቦሎ ከሆነ የተበላሸውን ቦሎ ማቅረብ አለበት።
6.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
7. ፋይላችን ባለበት አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍ/ቁ/ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት
ቀርበን መስተናገድ እንችላለን።
ግለሰቦች፤ነጋዴዎች ባለፋብርካዎች፤ እና ሠሌዳ ለማግኘት ማቅረብ የሚገባቸው መረጃዎች +
ግለሰቦች፤ነጋዴዎች ባለፋብርካዎች፤ እና ሠሌዳ ለማግኘት ማቅረብ የሚገባቸው መረጃዎች
፡
1.የማመልከቻ ቅጹን ሞልቶ ማቅረብ፤
2.ባስገቡአቸዉና በገጣጠሙአቸዉ ተሸከርካሪዎች ልክዝርዝር ኦርጅናል መረጃዎችንና የኦርጅናሉን መረጃ
3.ኮፒውን ማቅረብ፤
4.ባለፋብርካዎች፤ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች በየዓመቱ አንድ ጊዜ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ፤
5.ባለቤቱ ከሆነ የታደሰ የቀበለ መታወቂያ ኮፒ ወይም የጸና ፓስፖርት ኮፒ ወይም
6.በወክል ከሆነ በዉልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ የውክልናና የታደሰ የቀበለ መታወቂያ ኮፒ፤
7.በየዓመቱ አንድ ጊዜ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ፤
8.ባለፋብርካዎች፤ ነጋዴዎች እና ግለሰቦች አዲስ ሠሌዳ ለመዉሰድ በሚመጡበት ወቅት ከዚህ በፊት
9.የወሰዱአቸዉን ሠሌዳዎች በየተሸከርካሪዎቹ ላይ በአግባቡ መለጠፋቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ በተዘጋጀዉ ቅጽ መሰረት ሞልቶ ማቅረብ፤
10.የሚፈለረጉትን የሠሌዳ ብዛትና ለየተሸከርካሪዎቹ የሚገጥመዉን የሠሌዳ ዓይነት ለይቶ ጥያቄ ማቅረብ፤
11አስፈላጊውን የአገልግሎት ክፊያ በመፈጸም ሠሌዳዉ እንዲመረት ትዕዛዝ መስጠት፤
12ሠሌዳዉን በአካል ቀርቦ መረከብ ናቸዉ።
አዲስ ተሽከርካሪ ምዝገባ
+
አዲስ ተሽከርካሪ ምዝገባ የሚያስፈለገው ሰነዶች
፡
1. መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ከፓስፖርት ጋር
2. በውክልና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት
3. ከመስሪያ ቤቱ ወይም ከድርጅቱ የተወከለ ከሆነ የድርጅቱ የውክልና ደብዳቤና የድርጅቱ መታወቂያ
4. ኦርጅናል የጉምሩክ ዲክላራሲዮን
5. ሁለት ጉርድ ፎቶ ቲምብር (በውክልና ከሆነ ፎቶ አያስፈልግም)
6. የታደሰ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ እና የአስመጪነት ፈቃድ፣ የማስገቢያ ፈቃድ
7. የተሽከርካሪ መመርመሪያ ቅፅ (ሊብሬ ወረቀት)
8. ደረሰኝ (Invoice) በባለቤት ስም ከካሽ ሬጅስተር ጋር፤ የእጅ በእጅ ሽያጭ ከሆነ የደረሰኝ ህትመትና የማስተመሪያ ፈቃድ (ከባንክ ማህተም ጋር tt ካልሆነ ለቁጥር 5፣ 6፣ 7፣ 8 እና 9)
9. ከጉምሩክ በደረሰኝ መነሻ ቁጥር የተፈቀደበት ደብዳቤ
10. የሶስተኛ ወገን መድን የመንገድ ፈንድ
11. ከባንክ እና አስመጪ ማህተም ጋር የመጫኛ ሂሳብ
12. ከባንክ ማህተም ጋር የመነሻ የምስክር ወረቀት
13. ከባንክ ማህተም ጋር የቴክኒክ የምስክር ወረቀት
2. በጨረታ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ
1. ተሽከርካሪው ቀረጥ ያልከፈለና ዲክላራሲዮን የሌለው ከሆነ አዲስ በገዛው የተሰራ ዲክላራሲዮን ከገቢዎችና ጉምሩክ
2. የጨረታ አሸናፊ ደብዳቤ
3. ጨረታ የወጣበት ቀን፣ ቁጥር፣ የጋዜጣው ስም፣ የአሸናፊው ስም፣ የተሽከርካሪው ቻሲና ሞተር ቁጥር፣ ጨረታውን ያሸነፈበት ዋጋ፣ የክፍያ ደረሰኝ
4. ድርጅት ከሆነ ከመንግስት መ/ቤት ውጭ ከሆነ ብቻ ድርጅቱ ስም ይመዘገባል
5. ከአገልግሎት ውጪ ከሆነ (ኢንሹራንስ) ባለቤቱ ይመዘገባል
6. የአመታዊ ቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ሰርተፊኬት ማምጣት
የተሽከርካሪ ታርጋ ከክልል ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር +
የተሽከርካሪ ታርጋ ከክልል ወደ አዲስ አበባ ለማዘዋወር
፡
1.መኪናው ተመዝግቦ ካለበት ፅ/ቤት የዝውውር ቅፅ ተሞልቶ በፖስታ ታሽጎ ለተቀባይ ፅ/ቤት በፖስታ ማስላክ
2. አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ
3.ተሽከርካሪውን ለፅ/ቤቱ ባለሙያ እይታ በአካል ማቅረብ፤
4.የተሽከርካሪውን ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ /ታርጋ/ ማስረከብ፤
5 ለአገልግሎት ክፍያ
6. ምትክ ሊብሬ፣ ቦሎ እና ሰሌዳ -ታርጋ- መረከብ።
✅ የተቀባይ የፓስታው አድራሻ በአግባቡ መሟላት አለበት ፖስታው ከመላኩ በፊት የዝውውር ጥያቄው በትክክለኛ የዝውውር ቅፅ መሞላቱን ማረጋገጥ ይኖርበናል ምክንያት በትክክል ካልተሟላ ያላስፈላጊ እንግልት እንዳረጋለን።
✅የፋይል ዝውውር ቅፁ ከተሞላ 6 ወር ከሞላው ቅፁ ተቀባይነት ስለማይኖረው ቅፁ በተሞላ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቀባይ ፅ/ቤት በመቅረብ እና ጉዳያቸሰነሰ በ6 ወር ውስጥ ማከናወን አለብን።
የጠፋ መንጃ ፍቃድ +
ለመንጃ ፍቃድ የሚያስፈልጉ፡
✅ ከፖሊስ የተሰጠ የጠፋ ማስረጃ
✅ 3 ጉርድ ፎቶግራፍ
✅ የአገልግሎት ክፍያ ደረሰኝ
የአሸከርካሪ አሰልጣኝነት ማስተማሪያ ፈቃድ ለማግኘት 7 ወሳኝ ቅድመ ሁኔታዎች +
የአሸከርካሪ አሰልጣኝነት ማስተማሪያ ፈቃድ ለማግኘት 7 ወሳኝ ቅድመ ሁኔታዎች
፡
ፈቃዱን ለማውጣት ዋናውንና ኮፒውን (Original & Copy) ይዘው መቅረብ ያለብዎት ሰነዶች፦
1. 📜 አፕሩቫል ሰርተፍኬት (Approval Certificate)
2. 🪪 የመንጃ ፈቃድ
3. 🎓 የቅጥር ወይም የትምህርት ማስረጃ
4. ✉️ የማስተማሪያ ፈቃድ ይሰጥልኝ ደብዳቤ፦ ከሚያስተምሩበት የደረጃው ማሰልጠኛ ተቋም የተጻፈ መሆን አለበት።
5. 📄 ክሊራንስ (Clearance)
6. 🏆 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC)፦ በየደረጃው (Level) ላጠናቀቁት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ነው።
7. 💳 የአገልግሎት ክፍያ
💡 "ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመር 7766 ላይ መደወል ይችላሉ።"
የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ ቅያሬ አገልግሎት ለማግኘት!!
+
የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ ቅያሬ አገልግሎት ለማግኘት!!
፡
1. 📝 የሃገሪቱ ትራንስፖርት ባለስልጣን የመንጃ ፈቃድ ትክክለኛነት ያረጋገጠበት ደብዳቤ።
2. 🏛️ በሃገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ / ኤምባሲ የሰነዱን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይኖርበታል።
3. 📜 የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰነዱን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለበት።
4. 🏢 ደብዳቤው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ መረጋገጥ ይኖርበታል።
5. 📸 6 ወር ያልሞላው ጉርድ ፎቶግራፍ ማቅረብ።
6. 💳 ኦሪጅናል የክፍያ ደረሰኝ እና የአገልግሎት ክፍያ።
7. 🪪 የእድሳት ዘመን ያላለፈበት የውጭ መንጃ ፈቃድ (ኦሪጅናል እና ኮፒ)።
8. 🛂 ፓስፖርት (ኦሪጅናል እና ኮፒ)።
9. 🏠 የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ግሪን ካርድ ኮፒ።
10. 👤 ግለሰቡ በአካል በመቅረብ ሂደቱን ማከናወን ይኖርበታል።
በአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሽከርካሪ "ስም ዝውውር" ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሰነዶች +
በአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሽከርካሪ "ስም ዝውውር" ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
፡
1. 🧾 የክፍያ ደረሰኝ እና የዝውውር ሰነድ፦ ከሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ 2% የተከፈለበት ደረሰኝ እና የስም ዝውውር ሰነድ።
2. 🛡️ የኢንሹራንስ ሰነድ፦ በኮፒ 03 በኮፒ 01 ከገዢዎች የተገኘ የሶስተኛ ወገን መድን (ኢንሹራንስ) ማስረጃ።
3. ⚖️ ህጋዊ ውክልና ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ፦ የፍርድ ቤት ውሳኔ (ከታዘዘ) ወይም በውክልና የመጣ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ሰነድ እና የቪዛ ማረጋገጫ (ቲምብር)።
4. 🏷️ የዘመኑ ቦሎ፦ የተሽከርካሪው የዘመኑ ቦሎ የተደረገ መሆን አለበት።
5. 👥 የሶስተኛ ወገን መገኘት/ማስረጃ።
ተሽከርካሪን ከቀረጥ ነፃ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሰነዶች +
ተሽከርካሪን ከቀረጥ ነፃ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
ተሽከርካሪን ከቀረጥ ነፃ ለማድረግ (Tax-Free) የሚከተሉትን ዋና ዋና ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅብዎታል፦
1. 📖 ሊብሬ (የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ)
2. 🤝 በውክልና ከሆነ፦ ህጋዊ ውክልና (Power of Attorney) እና የባለቤቱ/የተወካዩ መታወቂያ
3. 📄 በባለንብረቱ ስም የተዘጋጀ ዜሮ ዲክላሬሽን (Zero Declaration) ከጉምሩክና ገቢዎች ቢሮ
4. 📸 ጉርድ ፎቶግራፍ
No comments:
Post a Comment