-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

⚠️ የንግድ ፈቃድ ለማዘጋት ማወቅ ያለባችሁ ወሳኝ ነጥቦች!

💡 የመዝጊያ ክሊራንስ (Clearance) ስለወሰዳችሁ ብቻ ንግድ ፈቃዳችሁ ተዘግቷል ማለት አይደለም። ብዙዎች የሚሳሳቱበትና ወደፊት ለከፍተኛ ቅጣት የሚዳርጋቸው ትልቁ ስህተት ይህ ነው!

1. የ eTrade ስረዛ ግዴታ ነው!


የገቢዎች ክሊራንስ ከወሰዳችሁ በኋላ የግድ በስልካችሁ ወይም በኮምፒውተር eTrade ላይ ገብታችሁ ፈቃዱን መሰረዝ አለባችሁ። ካልተሰረዘ ወደፊት ንግድ ፍቃዳችሁ አልተዘጋም ልትባሉና ላልተፈለገ እንግልትና ወጪ ልትዳረጉ ትችላላችሁ።

2. የ 3 ወር ገደብ!


ከገቢዎች የሚሰጠው የመዝጊያ ክሊራንስ የሚያገለግለው ለ 3 ወር ብቻ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ eTrade ላይ ገብታችሁ ካልሰረዛችሁ ክሊራንሱ ሙሉ በሙሉ ዋጋ ያጣል።

3. መቼ ነው "ተዘጋ" የሚባለው?


ፈቃዱ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ የሚባለው eTrade ላይ ገብታችሁ 52 ብር ከፍላችሁ "የመዝጊያ ደብዳቤ" በእጃችሁ ሲገባ ብቻ ነው!

📋 ለማዘጋት የሚያስፈልጉ ሰነዶች

👤 ለግል (Sole Proprietorship)፦
• ከገቢዎች የተሰጠ የመዝጊያ ክሊራንስ (Clearance)።
• የመዝጊያ ደብዳቤ።
🏢 ለማህበር (Company)፦
• የኦዲት ሪፖርት።
• የግብር ክሊራንስ።
• የ canclation የመዝጊያ ቃለ-ጉባኤ (Minutes)።

📱 በስልክ እንዴት እንዘጋለን?

1️⃣ ወደ ድረ-ገጹ etrade.gov.et ብለው ይግቡ።
2️⃣ የቲን (TIN) ቁጥርዎን ያስገቡ።
3️⃣ የ Password (የይለፍ ቃል) ያስገቡ።
✍️ ፖስወርድ የማታውቁት ወይም ከረሳችሁት ወደ ስልክዎ የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) በመላክ መቀየር ይችላሉ። 4️⃣ "የስረዛ አገልግሎት" የሚለውን ይጠይቁ።
5️⃣ ሲስተሙ የሚጠይቀውን የገቢዎች ክሊራንስ ያስገቡ (Upload ያድርጉ)።
6️⃣ የ 52 ብር ክፍያ በመፈፀም የስረዛ ደብዳቤዎን ያውርዱ።
📞 በማንኛውም የንግድ ፈቃድ ስረዛ፣ አዲስ ማውጣት፣ ማሻሻል ወይም እድሳት ጥያቄ ካለዎት በነፃ የጥሪ ማዕከል 8588 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

No comments:

Post a Comment