-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

Heena Digital Market

🏢 P.L.C. ለመመስረት
ማወቅ ያለብን 14 ነጥቦች

1
የአባላት ቁጥር፦ አንድ P.L.C. ለመመስረት ቢያንስ 2 ሰዎች ያስፈልጋሉ፤ ቢበዛ ደግሞ እስከ 50 አባላት ሊኖሩት ይችላል።
2
የኃላፊነት ወሰን፦ ትልቁ ጥቅም ይሄ ነው! ማህበሩ እዳ ቢኖርበት፣ አባላቱ የሚጠየቁት ባዋጡት ካፒታል ልክ ብቻ ነው። የግል ንብረታቸው (ቤት፣ መኪና) አይነካም።
3
መነሻ ካፒታል፦ በኢትዮጵያ ህግ መሠረት አንድ P.L.C. ለመመስረት ቢያንስ 15,000 ብር ካፒታል ሊኖር ይገባል።
➡️ መነሻ ካፒታል ነው ብለን መመስረቻ ፁሁፉ ላይ ያሰፈረውን መነሻ ካፒታል የንግድ ምዝገባ እስከሚያወጡ ድረስ በዝግ አካውንት በማህበሩ ስም በተከፈተ አካውንት ውስጥ ማስቀመጥ አለበት። የንግድ ምዝገባ ካወጣ በኋላ ማውጣት ይቻላል።
4
የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ፦ ይሄ የማህበሩ "ህገ-መንግስት" ነው። አባላቱ እንዴት እንደሚተዳደሩና ትርፍ እንዴት እንደሚከፋፈሉ የሚወሰንበት ሰነድ ነው። በመንግስት ፊት የፀደቀ መመስረቻ ፀሁፍ ያስፈልጋል።
5
የስም ምርመራ፦ ስሙ በሌላ ድርጅት ያልተያዘ መሆኑን በ etrade.gov.et ወይም በ heena digital market website በኩል ማረጋገጥ አለብን።
➡️ ስም ስያሜ የሚፀደቀው የኪራይ ውል ባለበት ክፍለ ከተማ ነው።
6
የስራ አስኪያጅ ሹመት፦ ማህበሩን በበላይነት የሚመራ ስራ አስኪያጅ ሊኖረው ይገባል። ከአባላቱ አንዱ ወይም ከውጭ የተቀጠረ ሊሆን ይችላል።
7
የአክሲዮን ዝውውር፦ ድርሻሽን (Share) ለሌላ ሰው ለመሸጥ ቢፈልግ፣ በቅድሚያ ለሌሎቹ የማህበሩ አባላት ማቅረብ አለበት።
8
ኦዲትና ሪፖርት፦ በየዓመቱ ሂሳቡ በኦዲተር መመርመርና ለሚመለከተው የመንግስት አካል ሪፖርት መደረግ አለበት።
9
ስለ VAT፦ በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሰረት ሁሉም PLCዎች ደረጃ ''ሀ'' ምደባ ውስጥ በመሆናቸው VAT ተመዝጋቢዎች ሆነዋል።
10
ህጋዊ ሰውነት፦ P.L.C. ልክ እንደ አንድ ሰው የራሱ "ህጋዊ ሰውነት" አለው። የራሱ ስም፣ የባንክ አካውንትና TIN Number ይኖረዋል።
11
ጠቅላላ ጉባኤ፦ የሒሳብ ዓመት ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ባሉት አራት ወራት ውስጥ ቢያንስ አንድ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መደረግ አለበት።
12
የማህበርተኞች መብትና ግዴታ፦ መሥራች በገንዘብ ድርሻው ልክ የመምረጥ፣ ትርፍ የማግኘትና ኪሳራ የመጋራት ግዴታ አለበት።
13
የሥራ አስኪያጅ ተጠያቂነት፦ ሥራ አስኪያጁ ሕግ ወይም መመስረቻ ጽሑፍን በመተላለፍ ለሚያደርሰው ጉዳት ኃላፊ ነው። ድርጅቱ ቢከስር ስራ አስኪያጁ የማኅበሩን ዕዳ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲከፍል ፍርድ ቤት ሊወስን ይችላል።
14
ድርጅቱን የማፍረስ ሂደት፦ ማኅበሩ አስፈላጊ የሆነ የአስተዳደር አካል የሌለው እንደሆነ በባለአክሲዮን ወይም በገንዘብ ጠያቂ በሚቀርብ ጥያቄ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይፈርሳል።

💡 PLC ከመመስረትዎ በፊት ሊያውቁት የሚገባ "እውነት"

የነፃነት ዋጋ (Audit Liability)፦ በየዓመቱ ሂሳቡን የማስመርመር "ህጋዊ ግዴታ" አለበት።

የስራ ጥናት አስፈላጊነት፦ ስራ ካልተሰራ በየዓመቱ "ዜሮ ሪፖርት" (Zero Report) ማድረግ ይሰለቻል።

የመዝጋት ፈተና፦ ለማዘጋት ከመመስረቱ በላይ ረጅም ሂደትና ውጣ ውረድ አለው።

"Heena Digital Market የሚመክርዎ፦ በደንብ አጥኑ፣ ተዘጋጁ፣ ከዚያም በልበ ሙሉነት መስርቱ!"
➡️ ተጨማሪ ስለ PLC መመሪያዎች በቴሌግራም
Heena Digital Market
📌 HEENA DIGITAL

እንኳን ወደ ሄኖ ዲጂታል መረጃና ማርኬት በደህና መጡ!

💳 የመንግስት የአገልግሎት ክፍያዎች
🤝 ውልና ማስረጃ ክፍያ
📜 መንገድ ትራንስፖርት
⚠️ ማሳሰቢያ: ክፍያ ሲፈጽሙ የሚሰጥዎትን የክፍያ ትዕዛዝ ቁጥር ለደረሰኝ እንዲሆን በጥንቃቄ ይያዙ።
📇 QR ደረሰኝ ማረጋገጫ
🔍 የ QR ደረሰኝ ማረጋገጫ

የቲን (TIN) ቁጥርዎን ያስገቡ

🟡 ገና አልደረሰም
🟢 ደርሷል (Printed)
ወደ ውብሳይቱ 🚀

* መረጃው በቀጥታ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተወሰደ ነው

🚓 ፖሊስ መረጃ አገልግሎት 911
🚓 ፌደራል ፖሊስ 915
📺EBC 905
💡 መብራት ኃይል 905
💧 ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት 954
🔥 የእሳት አደጋ 912
🔥 ፀረ ሙስና 988
የእለት የውጭ ምንዛሬ
ከባንክ ያግኙ

Search This Blog