-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

Heena Digital Market

⚠️ ውል ከመፈረማችሁ በፊት
ማወቅ ያለባችሁ 7 ወሳኝ ነጥቦች

ማንኛውንም የንግድ፣ የቤት ወይም የመኪና ሽያጭ ውል ከመፈረማችሁ በፊት እነዚህን ነጥቦች ማረጋገጥ ከወደፊት አላስፈላጊ ክርክር እና ኪሳራ ያድንዎታል።

1
የተዋዋይ ወገኖች ማንነትና ሕጋዊ ብቃት
በውሉ ላይ የተጠቀሱት ስሞች ከታደሰ መታወቂያ ጋር ትክክል መሆናቸውን ያረጋግጡ።
በፋይዳ፦ ቀጥታ ከቴሌብር ላይ እንዳለው ማረጋገጫ።
2
ተዋዋዩ ወገን ውል ለመዋዋል የሚያስችል የዕድሜ እና የአዕምሮ ጤንነት ደረጃ ላይ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
3
የንብረቱ ሕጋዊ ባለቤትነት
የሚሸጠው ንብረት (መኪናም ሆነ ቤት) በሻጩ ስም መሆኑን እና በባንክ ወይም በሌላ ዕዳ ያልታገደ መሆኑን ከሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

➡️ ሰነድ ኮፒ፦ ተቀብለን ፋይሉ ባለበት ክፍለ ከተማ ማረጋገጥ ይኖርብናል።
መኪና ከሆነ፦ በተመሳሳይ ፋይሉ ባለበት የአሽከርካሪ ተሽከርካሪዎች ጽ/ቤት በመሄድ ማረጋገጥ አለብን።

➡️ ተጨማሪ፦ መኪናው የንግድ ከሆነ ደግሞ የንግድ ፈቃድ እንዳለውና የታደሰ መሆኑን በ etrade.gov.com ወይም prife ባለው የetrade የንግድ ፈቃድ አገልግሎት ► የንግድ ፈቃድ ► 3ሰረዝ ► የንግድ ፈቃድ ማጣሪያ ► ቲን አስገብተው ያረጋግጡ።
ንግድ ፈቃድ ከሌለው "የለም" ይላል፤ ካለ ዝርዝር መረጃ ስትነኩ ፈቃዱ ያለበትን ሁኔታ (መታደሱንና አለመታደሱን) ይነግራችኋል። ይህ ማረጋገጣችን አንዳንድ ሰዎች Photoshop ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው አድርገው ስለሚሰሩ ለማወቅ ይረዳችኋል።
4
ያገባ / ያላገባ
ሻጭ ያላገባ ከሆነ "ያላገባ" ሰርተፊኬት፣ ካገባ ደግሞ የጋብቻ ሰርተፊኬት በተጨማሪ የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት እንደሚያቀርብ መስማማት አለበት። ካልሆነ በገዛነው ንብረት ላይ እገዳ ሊመጣ ይችላል።
5
የክፍያ ሁኔታ እና ማስረጃ
ገንዘቡ እንዴት ነው የሚከፈለው? በባንክ ወይስ በእጅ? የቅድመ ክፍያ ካለ በግልጽ በውሉ ላይ መታወቅ አለበት። ክፍያው በባንክ መሆኑ ለወደፊት እንደ ታማኝ ማስረጃ ያገለግላል።
6
የታማኝ ምስክሮች መኖር
ቢያንስ ሦስት ታማኝ ምስክሮች መኖራቸውን እና ስማቸው፣ አድራሻቸውና ፊርማቸው በውሉ ላይ በትክክል መስፈሩን ያረጋግጡ።
➡️ ምስክር ግዴታ ስለሆነ፦ ዝም ብሎ ያገኘነውን "ፈረሙልኝ" ከማለት የምናውቀውን ሰው ብናስፈርም የተሻለ ነው።
7
ግልጽ የሆኑ ግዴታዎች
ውሉ ቢፈርስ ምን ይሆናል? ካሳውስ እንዴት ነው የሚታሰበው? የሚሉትን ነጥቦች አስቀድሞ በውሉ ላይ ማስፈር ወደፊት ለሚመጣ አለመግባባት መፍትሔ ይሰጣል።
➡️ ውል ማፍረስ፦ አንዳንድ ውሎች በተለያዩ ምክንያቶች ይፈርሳሉ፤ ስለዚህ እናንተም ግልጽ ግዴታው መኖሩ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ።
📢 የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች: ወደ መንግሥት መሥሪያ ቤት ከመሄድዎ በፊት የእኛን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ!

No comments:

Post a Comment