-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🏫 መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት

የአቋቋም፣ የአስተዳደርና የቁጥጥር መመሪያዎች

1. ጠቅላላ ደንቦች

መንግሥታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት (የግል፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የውጭ ማኅበረሰብ፣ የሃይማኖት ወዘተ...) የሚከተሉትን ደንቦች ማክበር ይኖርባቸዋል፦

📍 ምዝገባ፦ ለትምህርት ቤትነት የሚያበቁ መስፈርቶችን አሟልተው የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
📍 ነጻ አስተዳደር፦ የራሳቸው የገንዘብ ምንጭና ነጻ አስተዳደር ሊኖራቸው ይገባል።
📍 እኩልነት፦ ተማሪዎች አካዳሚያዊ መስፈርትና ክፍያ እስካሟሉ ድረስ ማናቸውንም ልዩነትና መድልዎ መፈጸም የተከለከለ ነው።
📍 የክፍያ ጣሪያ፦ ትምህርት ቤቶች ሊያስከፍሉ የሚገባቸውን የክፍያ ጣሪያ በተመለከተ ሚኒስቴሩ መመሪያ ሊያወጣ ይችላል።

2. የግል ትምህርት ቤት ማቋቋም የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች

የሚከተሉት ግለሰቦች ወይም የንግድ ማኅበራት ትምህርት ቤት ማቋቋም አይችሉም፦
❌ በፍርድ የመክሰር ውሳኔ የተሰጠበት ወይም ዕዳ መክፈል ባለመቻሉ ከባለገንዘቦች ጋር ለመደራደር ያመለከተ ሰው።
❌ የአመልካቹ ድርጅት ወሳኝ አባላት በወሲባዊ ጥቃት ወይም በሕፃናት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆናቸው በፍርድ ቤት የተረጋገጠ።

3. ለማቋቋም መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  • ✅ ፈቃድ ያላቸው መምህራን መኖር።
  • ✅ በክልል ወይም በሚኒስቴር የጸደቀ ሥርዓተ ትምህርት (Curriculum)።
  • ✅ የጤና፣ የሕንፃና የአካባቢ ደህንነት ደረጃን የጠበቀ ቅጥር ግቢ።
  • የፋይናንስ ዋስትና፦ የመምህራንና የሠራተኞችን የ6 ወር ደመወዝ መሸፈን የሚችል በዝግ የባንክ ሒሳብ የተቀመጠ ገንዘብ።
  • ✅ የሕንፃው ኪራይ ከሆነ ቢያንስ ለሁለት ዓመት የሚያገለግል የኪራይ ውል።

4. የትምህርት ቤት አስተዳደርና ኮሚቴ

እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሚከተሉትን አባላት የያዘ የትምህርት ቤት ኮሚቴ ሊኖረው ይገባል፦
• የወላጆች ተወካዮች
• የመምህራን ተወካዮች
• የተማሪዎች ተወካዮች (ለ2ኛ ደረጃ)
• የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ተወካዮች
✍️ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የኮሚቴው ጸሐፊ ሆኖ ያገለግላል። ኮሚቴው ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችንና የወላጆችን ስጋት ይመረምራል።

⚠️ የሕግ ተገዢነትና ቅጣት

ትምህርት ቤቶች አዋጁን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን መተላለፋቸው ሲረጋገጥ እንደ ጥፋቱ ክብደት እስከ ፈቃድ መሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment