-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

📋 ከግል ንግድ (Sole) ወደ PLC መሸጋገር

ማወቅ ያለባችሁ ሙሉ መረጃ!

ብዙዎች "የግል ንግድ ወደ PLC መቀየር ይቻላል" ሲሉ ይሰማሉ፣ ግን በሕጉ መሠረት "ቀጥታ መቀየር" (Conversion) የሚባል ነገር የለም። ሂደቱ እንደ አዲስ መጀመር ነው።

🛠️ ዋናው መንገድ (እንዴት ይደረጋል?)

1. የግል ንግዱን መዝጋት፦ መጀመሪያ የነበረውን የግል ንግድ ፈቃድ መዝጋት አለብን። ለዚህ ደግሞ ከገቢዎች "የታክስ ክሊራንስ" (Tax Clearance) ማምጣት ግዴታ ነው።

2. አዲስ PLC መመሥረት፦ የግል ንግዱ ሲዘጋ፣ እንደ አዲስ የድርጅት መመሥረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ በሰነዶች ማረጋገጫ ይጸድቃል።

3. አዲስ ፈቃድ ማውጣት፦ በጸደቀው ሰነድ መሠረት አዲስ የንግድ ፈቃድ በPLC ስም ይወጣል።

💡 ለምን በቀጥታ መቀየር አይቻልም?

ህጋዊ ሰውነት፦ የግል ንግድ አንድ ግለሰብን ይወክላል (Natural Person)።
✍️ PLC ግን ራሱን የቻለ "ሕጋዊ ሰው" (Juridical Person) ነው። ሰው ወደ ድርጅትነት "አይቀየርም"፤ ድርጅቱ እንደ አዲስ መፈጠር አለበት።

የዕዳ ኃላፊነት፦
✍️ በግል ንግድ ላይ ላለ ዕዳ በቤታችንና በንብረታችን እንጠየቃለን።
✍️ PLC ግን "ኃላፊነቱ የተወሰነ" ስለሆነ፣ ዕዳ ቢኖር እንኳን የሚጠየቀው በድርጅቱ ካፒታል ልክ ብቻ ነው። ይሄ ትልቅ ልዩነት ስለሆነ ሕጉ ሂደቱ እንዲለይ ያደርጋል።

⚠️ በጣም ወሳኝ ነጥብ!

ለPLC አዲስ የራሱ የሆነ TIN ቁጥር ይሰጠዋል። የግል ስንጠቀምበት የነበረውን TIN ቁጥር ለPLC መጠቀም አይቻልም!

🌟 የመሸጋገር እድሎች

1. ወደ መደበኛ PLC (ባለብዙ አባል)
አይቻልም! ❌ በሕጉ መሠረት ከግል ንግድ በቀጥታ ወደ መደበኛ PLC (ከሁለት ሰው በላይ ወደሚሆን) መሸጋገር አይቻልም።
መፍትሔው፦ የግል ንግዱን ዘግቶ፣ አጋር ፈልጎ፣ እንደ አዲስ PLC መመሥረት ነው።
2. ወደ "ባለ አንድ አባል PLC" (One Member PLC)
ይቻላል! ✅ ይሄ በአዲሱ የንግድ ሕግ የመጣ ትልቅ ዕድል ነው። የግል የንግዳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ ይቻላል።
እንዴት? በግል ንግድ የነበረውን መብትና ግዴታ (Asset and Liability) በሙሉ ወደ አዲሱ "ባለ አንድ አባል PLC" ማዛወር ይቻላል።

💎 የ"ባለ አንድ አባል PLC" ጥቅሞች

📍 ሙሉ ባለቤትነት፦ ማንም መጠየቅ ሳያስፈልግ ድርጅቱ ላይ መወሰን ይቻላል።
📍 የንብረት ጥበቃ፦ በግል ንግድ ጊዜ ዕዳ ቢኖርብን የግል ቤታችን ይያዛል። በ"ባለ አንድ አባል PLC" ግን ዕዳ ቢኖር እንኳን የሚጠየቀው ድርጅቱ ብቻ ነው፤ የእኛ የግል ንብረት አይነካም!

🚀 የውልና ማስረጃ ሂደቶች

ስለ PLC እና "ባለ አንድ አባል PLC" የውልና ማስረጃ ሂደቶች እና የታክስ ጉዳዮችን በዝርዝር ለማወቅ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment