-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

⚖️ የውክልና ጥንቃቄና
ሕጋዊ ማብራሪያዎች (ሙሉ)

1. የአስተዳደር ተግባር በፍ/ብ/ህ/ቁ 2204 ላይ የተተረጎመው ሲሆን የወካይ ሀብት የማስቀመጥ፣ የመጠበቅ ከ3 ዓመት ለማያልፍ ዘመን የማከራየት፣ በብድር የተሰጠውን ሀብት የመሰብሰብ፣ ከሀብቱ የሚመጣውን ገቢ ተቀብሎ የማስቀመጥና ለተከፈሉ እዳዎች ደረሰኝ የመስጠት ስራዎች ሁሉ እንደ አስተዳደር ተግባር ይቆጠራሉ።
2. ውክልና ሰጪዎች እኛ ባልና ሚስት ብለው ከማንኛውም ሠነድ የማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ውክልና ከሰጡ ተወካይ በውክልናው መሠረት አገልግሎት ፈልጎ ሲመጣ በድጋሚ የጋብቻ ማስረጃ እንዲያቀርቡ መጠየቅ ሳያስፈልግ መስተናገድ ይቻላል።
3. የንግድ ማህበራት በመመሰረቻ ጽሁፍ እና በመተዳደሪያ ደንባቸው ላይ ስራ አስኪያጁ ጠበቃ እንዲወክል ግልጽ ሥልጣን ባይሰጠውም ጠበቃ መወከል ይቻላል። ሆኖም የሽርክና ማህበር ሲሆን በመመስረቻ ጽሁፍ እና በመተዳደሪያ ደንባቸው ሥራ አስኪያጁ ጠበቃ እንዲወክል መፍቀድ አለባቸው።
4. በውክልና ሥልጣን ማስረጃው ላይ ባል ለሚስት ወይም ሚስት ለባሏ ለባለቤት ተብሎ በተሰጠ ውክልና ላይ እንዳቸው ለመገልገል ቢመጡ በድጋሚ የጋብቻ ማሰረጃ እንዲያቀርቡ አይጠይቅም።
5. ወካይ በሰሜ ንብረት ይግዛልኝ ብሎ በሰጠው ውክልና ተወካይ በግልጽ በጋራ ይግዛልኝ ካላለው በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር በወካይ ስም በጋራ መግዛት አይችልም።
6. እናት እና አባት ወይም ሞግዚት ሆነው የተሾሙ አባት ወይም እናት ለሆኑለት ልጅ የልደት ሠርተፍኬት እና ልዩ ልዩ ሰነዶች ማውጣትና መቀበልን ጨምሮ ንብረት ማስተዳደርን በተመለከተ ውክልና መስጠት ይችላሉ።
7. በፍ/ቤት የተሾመ ማንኛውም ሞግዚት ንብረት ማስተዳደርን በተመለከተ 3ኛ ወገን ለመወከል ቢፈልግ ይህንን የሚገልፅ ተጨማሪ ስልጣን ከፍ/ቤት ማምጣት አለበት።
8. ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ የውክልና ስልጣን በተቋሙ ቀርቦ መሻር/መተው ይቻላል።
9. ብዙ ሰዎች በአንድነት ውክልና ሰጥተው እያለ አንደኛው ወካይ ብቻውን መጥቶ ተወካዩን መሻር ከፈለገ በፍ/ብ/ህ/ቁ/2228 /2/ መሠረት ተወካዩን ለመሻር በቂ ምክንያት ነው ብሎ ያመነበትን በመሻሪያ ሰነዱ ውስጥ አካቶ መሻር ይችላል።
10. ተወካይ በውክልና ሰነዱ 3ኛ ወገን እንዲወክል የተፈቀደለት ቢሆንም በፍ/ሕ/ቁጥር 2215 (3) ላይ በተቀመጠው መሰረት ድንገተኛ መሰናክል የገጠመው መሆኑን ገልፆ ለአስተዳደራዊ ተግባራት ብቻ 3ተኛ ወገን ሊወክል ይችላል።
11. በፊርማ ናሙና ብቻ የሚሰጡ ውክልናዎች በመጀመሪያ በሚሰጡበት ሰዓት ወካይ ከውል ወይም ከህግ የመነጨ ስልጣን ያላቸው ለመሆኑ በአግባቡ ሊታይ ይገባል።
12. በጠበቃ ውክልና ላይ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 63ን በመጥቀስ እንዲሁም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2204 መሰረት የጉዳይ ማስፈፀም ውክልና ሊሰጥ ይችላል።
13. እኛ ወካዮች ብለው በአንድነት ውክልና የሚሰጡ ሰዎች ውክልና መስጠት የሚችሉት የጋራ በሚያደርጋቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ እንጂ የየግል ጉዳያቸውን አካተው መስጠት አይችሉም።
14. Country Director የሚል የተሰጠ ሰነድ መሠረት አገልግሎት ለማግኘት በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ግለሰብ ያለው ሥልጣን እና የድርጅቱ ህጋዊ እውቅና በደንብ ሊረጋገጥ ይገባል።
15. በውክልና ማስረጃ ላይ ተወካይ ምን ምን ጉዳዮችን እንደሚያከናውን በዝርዝርና በግልጽ እስከተሰጠው ድረስ የህግ ቁጥር ቢሳሳትም ውክልናው አያገለግልም ማለት አይቻልም።
16. ንብረት ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ በውክልና ላይ በግልጽ መቀመጥ አለበት። መሸጥ ከተፈቀደ መግዛት ይችላል የሚል ትርጓሜ አይወሰድም።
17. ተወካይ ውል እንዲያፈርሥ ሥልጣን ባይሰጠውም፣ ተወካዩ በወካዩ ስም የተዋዋላቸውን ውሎች ማፍረስ ይችላል።
18. ንብረት እንዲያስተዳድርልኝ ወይም እንዲያከራይልኝ የተሰጠ ውክልና፣ ወካይ ከሌላ ሰው የተከራየውን ንብረት ጭምር ተወካይ ለ3ኛ ወገን ለማከራየት ያስችለዋል።
19. ተዋዋዮች ወኪላቸው አንድ ሰው ቢሆንም ተወካዩ ውሉን በሁለቱም ወገን ሆኖ ማድረግ አይከለከልም።
20. ወካይ ንብረቴን አስይዘህ ተበደርልኝ ካለ፣ ተወካይ ያለመያዣ የብድር ውል መዋዋል አይችልም።
21. ወካይ ራሱ በአካል ቀርቦ ማውጣት ያለበትን እንደ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ እንዲያወጡልኝ ብሎ ውክልና ለመስጠት አይችልም።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment