-->
የአገልግሎት ማውጫ📑 ⬇️
ሰላም የሀገሬ ነጋዴዎች ባለጉዳዮች! 🇪🇹
ከቲክቶክ ለምትመጡ ሙሉ መረጃ እንዲከፍትላቹ ከላይ ... ነክታችሁ Open in Browser በሉ | ወይም Google ላይ "Heena Digital Market" ብላችሁ ፈልጉ
እንኳን ደህና መጡ!

HEENA DIGITAL MARKET

የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና ባለጉዳዮች በአንድ ቦታ!!!

🏢 አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

አዲስ ንግድ ፍቃደ ለማውጣት

🏢 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር1395/2017

🏢 ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

ውልና ማስረጃ ቀጠሬ ለማስያዝ

🏢 መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

መንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ አስፈፃሚ አገደ

🏫

QR ደረሰኝ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ

🏠 የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ኪራይ ውል ጋር በተያያዘ ትኩረትና ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች

1
የማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይ ውል ሰነድ ይረጋገጥልኝ አገልግሎት ጥያቄ ለማስተናገድ አገልግሎታቸው ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆኑ ማለትም ለቅያጤ፣ ለድርጅት፣ ለኢንዱስትሪ ወ.ዘ.ተ. እና ባለ አንድ ፎቅ (G+1) ከዚያ በላይ ለሆኑት ከመኖሪያ ውጭ ያሉ ህንጻዎች የህንጻዎች የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የህንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ የምስክር ወረቀት መቅረቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
2
የኪራይ ውልን ወደ ኋላ ተመልሶ ለማፅደቅ እንደምታ ወደ ኋላ የሚወሰደው ጊዜ በበጀት ዓመቱ ውስጥ መሆን አለበት። በተጨማሪም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ወይም ዴስክ ኃላፊ ሊመራበት ይገባል።
3
የመንግስት ተቋም አገልግሎት ሲጠይቅ ተቋሙ በሕግ የተቋቋመ መሆኑንና ፈራሚው የተቋሙ ኃላፊ ሆኖ የተሾመበት ደብዳቤ መቅረቡን፣ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና የተሰጠው መሆኑን ማረጋገጥ።
4
ለማከራየት የቀረበው ንብረት፦
  • በውርስ የተገኘና የውርስነት ማስረጃ እና በፍ/ቤት የተረጋገጠ የውርስ አጣሪ ሪፖርት ከቀረበ።
  • ውል ለማቀያል ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የሽያጭ ወይም የስጦታ ውል ሰነድ ከቀረበ።
  • በሰነድ አልባ ይዞታ የተመዘገበ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ከቀረበ።
  • በፍርድ አፈጻጸም የጨረታ ሽያጭ የተገኘና ስም እንዲዞር በፍ/ቤት የተሰጠ ውሳኔ ከቀረበ።
  • በባንክ በብድር መያዣ ምክንያት የቀረበ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ከቀረበ፤ ካርታው ወደ ባለሀብቱ ያልዞረ ቢሆንም ከንብረት መዝጋቢው አካል ስም ለማዞር በሂደት ላይ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲቀርብ ስመ ንብረቱ ወደ ባለሀብቱ እስከሚዞር ለአንድ ዓመት ብቻ የሚቆይ የኪራይ ውል ሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ አገልግሎት መስጠት ይቻላል።
5
ካርታው በባንክ ወይም በሌሎች የፋይናንስ ተቋማት የተያዘ ከሆነ ባንኩ ወይም የፋይናንስ ተቋሙ በአድራሻ ለተቋሙ በመደበኛ በሚልከው ስድስት ወር ያላለፈው ደብዳቤ እና የካርታ ኮፒ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ለውስጥ አገልግሎት ይውላል።
6
የንብረት ማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከማሸኛ ደብዳቤ ጋር የሚያመጡ ተገልጋዮች ከመደበኛ ባንኮች ውጭ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት መሰል ማስረጃ ሲያመጡ ተቋማቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወይም በፌዴራል ህብረት ሥራ ኮሚሽን ህጋዊ እውቅና ያላቸው ስለመሆኑ በማስረጃ መረጋገጥ አለበት።
7
የተመሰከረው የባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም ደብዳቤ የሚያገለግለው ባንኩ ወይም የፋይናንስ ተቋሙ ደብዳቤውን ከጻፈበት ቀን ጀምሮ ለ6 ወር ጊዜ ብቻ ይሆናል።
8
የጋራ ይዞታ ንብረት የኪራይ ውል ሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ የሚቻለው በንብረቱ ላይ ከማሽ በላይ ድርሻ ያላቸው ተጋሪዎች ከቀረቡ ወይም ውክልና የሰጡ የቀሩትን ተጋሪዎች ጥቅም በተመለከተ ኃላፊነት እንደሚወስዱ በውሉ ውስጥ ያካተቱ ከሆነ ብቻ ነው። (የፍ/ብ/ህ/ቁ/1265/2)
9
የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤት ኪራይን በተመለከተ ልክ እንደሌላው የንግድ ድርጅት ቤት ኪራይ የሚስተናገድ ይሆናል።
10
የንግድ ማህበር ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው በማህበሩ ስም ተመዝግቦ የሚገኝን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማከራየት ግልጽ ስልጣን ሊኖረው ይገባል። ነገር ግን ሥራ አስኪያጁ ግልጽ ስልጣን ባይሰጠውም የማህበሩ የንግድ ዓላማ ውስጥ ከተካተተ ማከራየት ይችላል።
11
በተሰጠ የውክልና ሰነድ ላይ የንግድ ድርጅቱን ያስተዳድርልኝ፣ ንግድ ፍቃድ ያውጣልኝ፣ ያድስልኝ የሚል ሃሳብ ያለው የንግድ ሥራውን ዓይነት በመጥቀስ ለንግድ የሚሆን ቤት መከራየት ይቻላል።
12
المንግስት የልማት ድርጅቶች ለመከራየት በሚመጡበት ጊዜ የኃላፊነት ምደባ ደብዳቤ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት መቅረቡ መረጋገጥ አለበት።
13
የኮንዶሚኒየም የቤት ኪራይ ውል ከቤቱ የአገልግሎት ዓይነት ወይም ዓላማ ጋር የተያያዘ መሆን አለበት። ማለትም የንግድ ለንግድ፣ የመኖሪያ ለመኖሪያ ብቻ።
14
የሃይማኖት ተቋማት አስተዳዳሪዎች ቤት ለማከራየት ሲመጡ አስተዳዳሪው ሆነው የተሾሙበት ደብዳቤ እና ከሃይማኖት ተቋሙ የአስተዳደር ኮሚቴ (የሰበካ ጉባኤ) የማከራየት ስልጣን የተሰጣቸው ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ አለበት።
🏠 ወደ ዋናው ገጽ ተመለስ

No comments:

Post a Comment