1. ህጋዊ ሰውነት
P.L.C. ልክ እንደ አንድ ሰው የራሱ "ህጋዊ ሰውነት" አለው። ይህም ማለት ከባለቤቶቹ ተለይቶ የራሱ ስም፣ የባንክ አካውንት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና ንብረት የማፍራት መብት ይኖረዋል ማለት ነው።2. የድርጅት ስም ስያሜና ማጣራት
• ተግባራዊ ሂደት፦ የድርጅቱ ስም የሚመረጠውና የሚረጋገጠው በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ወይም ድርጅቱ በሚመሰረትበት ክፍለ ከተማ የንግድ ጽሕፈት ቤት ነው።• ማሳሰቢያ፦ የምትመርጠው ስም ከዚህ ቀደም በሌላ ድርጅት ያልተያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ ቢያንስ ሦስት አማራጭ ስሞችን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ይዞ መቅረብ ይመከራል።
3. የመመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ
ይህ የማህበሩ "ህገ-መንግስት" ነው። አባላቱ እንዴት እንደሚተዳደሩ፣ የስራ አስኪያጅ ስልጣን እና ትርፍ አከፋፈል የሚወሰንበት ሰነድ ነው።• ረቂቅ ዝግጅት፦ ለስም ማጣራት ሂደቱ ረቂቅ የመመስረቻ ጽሑፍ ያስፈልጋል።
• ማፅደቅ፦ ሰነዱ በፌዴራል ወይም በክልል የውልና ማስረጃ ማረጋገጫ ጽሕፈት ቤት (DARS) ቀርቦ በአባላቱ ፊት መፈረም እና መፅደቅ ይኖርበታል።
4. የቢሮ ኪራይ ውል
• በውልና ማስረጃ የተመዘገበ የኪራይ ውል (ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ) ማቅረብ ግዴታ ነው።• ማሳሰቢያ፦ የኪራይ ውሉ መታሰር ያለበት በፀደቀው የድርጅቱ ስም መሆን አለበት።
5. የንግድ ዓላማ (Business Objective)
• በመመስረቻ ጽሑፉ ላይ የምታወጡት የንግድ ፈቃድ ዘርፍ በግልጽ መሠፈር አለበት።
✍️ ምክር፦ የአሁኑን ብቻ ሳይሆን ወደፊት ልትሰሩባቸው የምታስቧቸውን ዘርፎች ቀድማችሁ ብታካትቱ በኋላ ላይ ለሚደረግ ማሻሻያ የሚወጣውን ወጪና ጊዜ ይቆጥባል።
6. ካፒታልና አባላት
• መነሻ ካፒታል፦ ቢያንስ 15,000 ብር ያስፈልጋል። የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከ100 ብር ማነስ የለበትም።• ዝግ አካውንት፦ ካፒታሉ በድርጅቱ ስም በሚከፈት "ዝግ የባንክ ሂሳብ" ውስጥ መቀመጥ አለበት።
• የአባላት ብዛት፦ አባላት ከ2 ያላነሱ እና ከ50 ያልበለጡ መሆን አለባቸው።
7. የስራ አስኪያጅ ሹመትና ስልጣን
• ማህበሩን በበላይነት የሚመራ ስራ አስኪያጅ ሊኖረው ይገባል።• ስልጣን መገደብ፦ የስራ አስኪያጁን ስልጣን በመመስረቻ ጽሑፉ ላይ መገደብ ይቻላል (ለምሳሌ፦ የጥምር ፊርማ ግዴታ)።
• ተጠያቂነት፦ ሥራ አስኪያጁ ሕግን በመተላለፍ ለሚያደርሰው ጉዳት በግል ንብረቱ ጭምር ተጠያቂ ሊሆን ይችላል።
8. አስፈላጊ ሰነዶችና የብቃት ማረጋገጫ
• የአባላት መታወቂያ፣ የTIN ቁጥር እና የዲጂታል መታወቂያ (Fayda)።• የስራ አስኪያጁ 2 ጉርድ ፎቶግራፍ።
• ለተወሰኑ ዘርፎች የብቃት ማረጋገጫ (Competency Certificate) ማቅረብ ያስፈልጋል።
9. ግብርና ኦዲት (VAT & Audit)
• VAT፦ በአዲሱ አዋጅ (1395/2017) መሠረት ሁሉም PLCዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።• 0 ሪፖርት፦ ስራ ባይኖርም "ዜሮ ሪፖርት" መደረግ አለበት። በአዲሱ አዋጅ 2.5% አጠቃላይ ገቢ ላይ ግብር የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
• ኦዲት፦ በየዓመቱ በውጭ ኦዲተር ተመርምሮ ሪፖርት መቅረብ አለበት።
10. የትርፍ ድርሻና አክሲዮን ዝውውር
• የትርፍ ግብር፦ የትርፍ ድርሻ (Dividend) ሲከፋፈሉ 15% ግብር ይከፈላል።• የአክሲዮን ዝውውር፦ ድርሻን ለመሸጥ ቅድሚያ ለማህበሩ አባላት ማቅረብ ግዴታ ነው።
No comments:
Post a Comment